ኦሪት ዘሌ​ዋ​ው​ያን 12

12
ሴት ከወ​ለ​ደች በኋላ ከሕ​ርስ ስለ​ም​ት​ነ​ጻ​በት ጊዜ
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 2“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ ሴት ብታ​ረ​ግዝ ወንድ ልጅም ብት​ወ​ልድ፥ ሰባት ቀን ያህል የረ​ከ​ሰች ናት፤ 3እንደ ግዳ​ጅዋ ወራት ትረ​ክ​ሳ​ለች። በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ልጁ ከሥ​ጋው ሸለ​ፈት ይገ​ረዝ። 4ከደ​ም​ዋም እስ​ክ​ት​ነጻ ሠላሳ ሦስት ቀን ትቈይ፤ የመ​ን​ጻቷ ቀንም እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ የተ​ቀ​ደ​ሰን ነገር አት​ንካ፤ ወደ መቅ​ደ​ስም አት​ግባ። 5ሴት ልጅም ብት​ወ​ልድ እንደ ግዳ​ጅዋ ወራት ሁለት ሳም​ንት ያህል የረ​ከ​ሰች ናት፤ ከደ​ም​ዋም እስ​ክ​ት​ነጻ ድረስ ስድሳ ስድ​ስት ቀን ትቈይ።
6“የመ​ን​ጻቷ ወራ​ትም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥ ለወ​ንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ፥ የአ​ንድ ዓመት ጠቦት ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ የር​ግ​ብም ግል​ገል ወይም ዋኖስ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ታመ​ጣ​ለች። 7ካህ​ኑም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል፤ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ት​ማል፤ ከደ​ም​ዋም ፈሳሽ ትነ​ጻ​ለች። ወንድ ወይም ሴት ለም​ት​ወ​ልድ ሴት ሕጉ ይህ ነው። 8ጠቦት ለማ​ም​ጣት የሚ​በቃ ገን​ዘብ በእ​ጅዋ ባይ​ኖ​ራት ሁለት ዋኖ​ሶች፥ ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች፥ አን​ዱን ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ሌላ​ው​ንም ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ለች፤ ካህ​ኑም ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ታል፤ እር​ስ​ዋም ትነ​ጻ​ለች።”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ