የሉቃስ ወንጌል 11
11
ስለ ጸሎት
1ከዚህም በኋላ በአንዲት ቦታ ጸለየ፤ ጸሎቱን በጨረሰ ጊዜም ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፥ “ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ለደቀ መዛሙርቱ እንደ አስተማራቸው ጸሎት አስተምረን” አለው። 2እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “በምትጸልዩበት ጊዜ እንዲህ በሉ፦ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነ እንዲሁም በምድር ይሁን። 3የዕለት ምግባችንን በየዕለቱ ስጠን። 4እኛም የበደለንን ሁሉ ይቅር እንድንል በደላችንን ይቅር በለን፤ አቤቱ፥ ወደ ፈተና አታግባን፤ ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ።”
5እንዲህም አላቸው፥ “ከመካከላችሁ ወዳጅ ያለው ሰው ቢኖር በመንፈቀ ሌሊትም ወደ እርሱ ሄዶ እንዲህ ቢለው፦ ‘ወዳጄ ሆይ ሦስት እንጀራ አበድረኝ። 6ወዳጄ ከመንገድ መጥቶብኛልና የማቀርብለት የለኝም።’ 7ያ ወዳጁም ከውስጥ ሆኖ፦ ‘አትዘብዝበኝ፤ ደጁን አጥብቀን ዘግተናል፤ ልጆችም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ ተኝተዋል፤ እሰጥህ ዘንድ መነሣት አልችልም’ ይለዋልን? 8ወዳጁ ስለሆነ ሊሰጠው ባይነሣ እንኳ እንዳይዘበዝበው ተነሥቶ የወደደውን ያህል ይሰጠዋል። 9እኔም እላችኋለሁ፦ ለምኑ፥ ይሰጣችኋልም፤ ፈልጉ፥ ታገኛላችሁም፤ ደጅ ምቱ፥ ይከፈትላችኋልም። 10የሚለምን ሁሉ ይሰጠዋልና፤ የሚፈልግም ያገኛልና፤ ደጅ ለሚመታም ይከፈትለታልና። 11ከእናንተ መካከል ልጁ ዳቦ የሚለምነው አባት ቢኖር ድንጋይ ይሰጠዋልን? ዓሣ ቢለምነውስ በዓሣ ፋንታ እባብን ይሰጠዋልን? 12ወይስ ዕንቍላል ቢለምነው በዕንቍላል ፋንታ ጊንጥ ይሰጠዋልን? 13እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታን መስጠትን የምታውቁ ከሆነ፥ የሰማይ አባታችሁማ ለሚለምኑት መልካሙን ሀብተ መንፈስ ቅዱስ#በግሪክ “መንፈስ ቅዱስን” ይላል። እንዴት አብዝቶ ይሰጣቸው ይሆን?”
ደንቆሮ ጋኔን ስለ ያዘው ሰው
14ዲዳና ደንቆሮ#“ደንቆሮ” የሚለው በግሪኩ የለም። ጋኔንንም ያወጣ ነበር፤ ጋኔኑም በወጣ ጊዜ ዲዳና ደንቆሮ የነበረው ተናገረ፤ ሰዎችም አደነቁ። 15#ማቴ. 9፥34፤ 10፥25። ነገር ግን ከመካከላቸው፥ “በአጋንንት አለቃ በብዔል ዜቡል አጋንንትን ያወጣቸዋል” ያሉ ነበሩ፤ እርሱም መልሶ፥ “ሰይጣን ሰይጣንን ማውጣት እንደምን ይቻለዋል?” አላቸው።#“እርሱም መልሶ ሰይጣን ሰይጣንን ማውጣት እንደምን ይቻለዋል” የሚለው በግሪኩ የለም። 16#ማቴ. 12፥38፤ 16፥1፤ ማር. 8፥11። ሌሎችም ሊፈትኑት ከእርሱ ዘንድ ከሰማይ ምልክትን ይፈልጉ ነበር። 17እርሱ ግን የሚያስቡትን ዐወቀባቸውና እንዲህ አላቸው፥ “እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁሉ ትጠፋለች፤ ቤትም እርስ በርሱ ቢለያይ ያ ቤት ይወድቃል። 18ሰይጣንስ እርስ በርሱ ከተለያየ መንግሥቱ እንዴት ይጸናል? በአጋንንት አለቃ በብዔል ዜቡል አጋንንትን ያወጣል ትላላችሁና። 19እኔ በብዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆነ፥ ልጆቻችሁ በምን ያወጡአቸዋል? ስለዚህ እነርሱ ይፋረዱአችኋል።#በግሪኩ “ይፈርዱባችኋል” ይላል። 20እኔ በእግዚአብሔር ጣት አጋንንትን የማወጣ ከሆነ እንግዲህ አሁን የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች። 21ኀይለኛ ሰው በጦር መሣሪያ ቤቱን የጠበቀ እንደ ሆነ ገንዘቡ ሁሉ ደኅና ይሆናል። 22ከእርሱ የሚበረታው ቢመጣና ቢያሸንፈው ግን፥ ይታመንበት የነበረውን የጦር መሣሪያውን ይገፈዋል፤ የማረከውንና የዘረፈውን#“የዘረፈውን” የሚለው በግሪኩ እና በአንዳንድ የግእዝ ዘርዕ አይገኝም። ገንዘቡንም ይወስዳል። 23#ማር. 9፥40። ከእኔ ጋር ያልሆነ ባለጋራዬ ነው፤ ከእኔ ጋር የማይሰበስብም ይበትንብኛል።
24“ክፉ ጋኔንም ከሰው በወጣ ጊዜ ውኃ ወደሌለበት ምድረ በዳ ይሄዳል፤ የሚያርፍበትንም መኖሪያ ይሻል፤ ያላገኘ እንደ ሆነም ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ ይላል። 25በመጣም ጊዜ ተጠርጎ አጊጦም ያገኘዋል። 26ከዚህም በኋላ ይሄድና ከእርሱ የሚከፉ ሌሎች ባልንጀሮቹን#“ባልንጀሮቹን” የሚለው በግሪኩ እና በአንዳንድ የግእዝ ዘርዕ አይገኝም። ሰባት አጋንንት ያመጣል፤ ገብተውም በዚያ ሰው ያድሩበታል፤ ለዚያ ሰውም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው የከፋ ይሆንበታል።”
በአሕዛብ መካከል አሰምታ ስለ ተናገረችው ሴት
27ከዚህም በኋላ ይህን ሲናገር ከሕዝቡ መካከል አንዲት ሴት ድምፅዋን አሰምታ፥ “የተሸከመችህ ማኅፀን ብፅዕት ናት፤ የጠባሃቸው ጡቶችም ብፁዓት ናቸው” አለችው። 28እርሱም፥ “ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁ ናቸው” አላት።
ምልክትን ስለሚጠይቁ ሰዎች
29 #
ማቴ. 16፥4፤ ማር. 8፥12። ብዙ ሰዎችም ተሰብስበው ሳሉ እንዲህ ይላቸው ጀመረ ፥ “ይቺ ትውልድ ክፉ ናት፤ ምልክትም ትሻለች፤ ነገር ግን ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጣትም። 30#ዮና. 3፥4። ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደ ሆናቸው የሰው ልጅም ለዚች ትውልድ እንዲሁ ምልክት ይሆናታል። 31የአዜብ ንግሥት በፍርድ ቀን ከዚች ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፋረዳቸዋለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ልትሰማ ከምድር ዳርቻ መጥታለችና፤ እነሆ፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ በዚህ አለ። 32የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚች ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፋረዱአታል፤#በግሪኩ “ይፈርዱባታል” ይላል። ያሳፍሩአታልም፤#“ያሳፍሩአታልም” የሚለው በግሪኩ እና በአንዳንድ የግእዝ ዘርዕ አይገኝም። ዮናስ በሰበከላቸው ጊዜ ንስሓ ገብተዋልና፤ እነሆ፥ ከዮናስ የሚበልጥ በዚህ አለ።
33“በስውር ቦታ ወይም ከዕንቅብ በታች ሊያኖራት መብራትን የሚያበራ የለም፤ የሚመላለሱ ሁሉ ብርሃንን ያዩ ዘንድ በመቅረዝዋ ላይ ያኖራታል እንጂ። 34የሰውነትህ መብራት ዐይንህ ነው፤ ዐይንህ ብሩህ ከሆነ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ነው፤ ዐይንህ ታማሚ ቢሆን ግን፤ ሰውነትህ ሁሉ ጨለማ ነው። 35እንግዲህ ብርሃንህ ጨለማ እንዳይሆን ተጠንቀቅ። 36ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ከሆነ በአንተም ላይ ምንም ጨለማ ባይኖርብህ የመብረቅ ብርሃን እንደሚያበራልህ ሁለንተናህ ብሩህ ይሆናል።”
ጌታችን ኢየሱስን ወደ ምሳ ስለ ጠራው ፈሪሳዊ
37ይህንም ሲነግራቸው አንድ ፈሪሳዊ በእርሱ ዘንድ ምሳ እንዲበላ ለመነው፤ ገብቶም ለምሳ ተቀመጠ። 38ፈሪሳዊዉም አይቶ አደነቀ፤ ምሳ ለመብላት እጁን አልታጠበም ነበርና። 39ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “እናንተ ፈሪሳውያን፥ ዛሬ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭውን ታጥቡታላችሁ፤ ታጠሩታላችሁም፤ ውስጡ ግን ቅሚያንና ክፋትን የተመላ ነው። 40እናንተ ሰነፎች፥ የውጭውን የፈጠረ የውስጡንስ የፈጠረ አይደለምን? 41ነገር ግን የሚወደደውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ፤ ሁሉም ንጹሕ ይሆንላችኋል። 42#ዘሌ. 27፥30። የእንስላልና የጤና አዳም፥ ከአትክልትም ሁሉ ዐስራት የምታገቡ ፍርድንና የእግዚአብሔርን ፍቅር ቸል የምትሉ እናንተ ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ወዮላችሁ! ይህንም ልታደርጉ ይገባችኋል፥ ያንም አትተዉ። 43እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ወዮላችሁ! በምኵራብ ፊት ለፊት መቀመጥን፥ በገበያም እጅ መነሣትን ትወዳላችሁና። 44እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ወዮላችሁ! ሰዎች ሳያውቁ በላዩ እንደሚመላለሱበት እንደ ተሰወረ መቃብር ናችሁና።”
45ከሕግ ዐዋቂዎችም አንዱ መልሶ፥ “መምህር ሆይ፥ ይህን ስትል እኛን እኮ መስደብህ ነው” አለው። 46እርሱም እንዲህ አለው፤ “ለእናንተ ለሕግ ዐዋቂዎች ወዮላችሁ! ሰውን ከባድ ሸክም ታሸክሙታላችሁ፤ እናንተ ግን ያን ሸክም በአንዲት ጣታችሁ እንኳን አትነኩትም። 47እናንተ ጻፎችና ፈሪሳውያን፥#“ጻፎችና ፈሪሳውያን” የሚለው በግሪኩ እና በአንዳንድ የግእዝ ዘርዕ አይገኝም። ወዮላችሁ! አባቶቻችሁ የገደሉአቸውን የነቢያትን መቃብር ትሠራላችሁና። 48የአባቶቻችሁም ሥራ ደስ አሰኝቶአችኋል፤ የምትመሰክሩባቸውም እናንተ ራሳችሁ ናችሁ፤ እነርሱ የገደሉአቸውን መቃብራቸውን እናንተ ትሠራላችሁና። 49ስለዚህ የእግዚአብሔር ጥበቡ እንዲህ አለች፦ እነሆ፥ እኔ ነቢያትንና ሐዋርያትን ወደ እነርሱ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ይገድላሉ፤ ያሳድዳሉም። 50ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከዚህች ትውልድ ድረስ ስለ ፈሰሰው ስለ ነቢያት ሁሉ ደም ይበቀላቸው ዘንድ፥ 51ከአቤል ደም ጀምሮ በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ መካከል እስከ ገደሉት እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ እውነት እላችኋለሁ ከዚች ትውልድ ይፈለጋል። 52እናንተ ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ወዮላችሁ! የጽድቅንና የዕውቀትን መክፈቻ ወስዳችሁ ትሰውራላችሁና፤ እናንተም አትገቡምና፤ የሚገቡትንም መግባትን ትከለክሉአቸዋላችሁ።” 53በሕዝቡም ሁሉ ፊት ይህን ሲነግራቸው ጻፎችና ፈሪሳውያን አጽንተው ይጣሉት፥ ይቀየሙትም ጀመር። 54በአነጋገሩም ሊያስቱትና ሊያጣሉት ያደቡበት ነበር።
Currently Selected:
የሉቃስ ወንጌል 11: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ