የሉ​ቃስ ወን​ጌል 11:9-13

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 11:9-13 አማ2000

እኔም እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ለምኑ፥ ይሰ​ጣ​ች​ኋ​ልም፤ ፈልጉ፥ ታገ​ኛ​ላ​ች​ሁም፤ ደጅ ምቱ፥ ይከ​ፈ​ት​ላ​ች​ኋ​ልም። የሚ​ለ​ምን ሁሉ ይሰ​ጠ​ዋ​ልና፤ የሚ​ፈ​ል​ግም ያገ​ኛ​ልና፤ ደጅ ለሚ​መ​ታም ይከ​ፈ​ት​ለ​ታ​ልና። ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ልጁ ዳቦ የሚ​ለ​ም​ነው አባት ቢኖር ድን​ጋይ ይሰ​ጠ​ዋ​ልን? ዓሣ ቢለ​ም​ነ​ውስ በዓሣ ፋንታ እባ​ብን ይሰ​ጠ​ዋ​ልን? ወይስ ዕን​ቍ​ላል ቢለ​ም​ነው በዕ​ን​ቍ​ላል ፋንታ ጊንጥ ይሰ​ጠ​ዋ​ልን? እና​ንተ ክፉ​ዎች ስት​ሆኑ ለል​ጆ​ቻ​ችሁ መል​ካም ስጦ​ታን መስ​ጠ​ትን የም​ታ​ውቁ ከሆነ፥ የሰ​ማይ አባ​ታ​ች​ሁማ ለሚ​ለ​ም​ኑት መል​ካ​ሙን ሀብተ መን​ፈስ ቅዱስ እን​ዴት አብ​ዝቶ ይሰ​ጣ​ቸው ይሆን?”