የሉ​ቃስ ወን​ጌል 8:16-18

የሉ​ቃስ ወን​ጌል 8:16-18 አማ2000

“መብ​ራ​ትን አብ​ርቶ፥ ዕቃም ከድኖ ከአ​ልጋ በታች የሚ​ያ​ኖ​ራት የለም፤ ነገር ግን የሚ​መ​ላ​ለ​ሱት ብር​ሃ​ንን ያዩ ዘንድ በመ​ቅ​ረዝ ላይ ያኖ​ራ​ታል። የማ​ይ​ገ​ለጥ የተ​ሰ​ወረ የለ​ምና፤ የማ​ይ​ታ​ይም ወደ ግል​ጥም የማ​ይ​መጣ የተ​ከ​ደነ የለም፤ እን​ግ​ዲህ እን​ዴት እን​ደ​ም​ት​ሰሙ አስ​ተ​ውሉ፤ ላለው ይሰ​ጠ​ዋል፤ ከሌ​ለው ግን ያው ያለው የሚ​መ​ስ​ለው እንኳ ይወ​ሰ​ድ​በ​ታል።”