የማቴዎስ ወንጌል 20
20
የወይን አትክልት ሠራተኞች ምሳሌ
1“መንግሥተ ሰማያት ለወይኑ አትክልት ሠራተኞችን ሊቀጥር ማልዶ የወጣ ባለቤት ሰውን ትመስላለችና። 2ሠራተኞችንም በቀን አንድ ዲናር ተስማምቶ ወደ ወይኑ አትክልት ሰደዳቸው። 3በሦስት ሰዓትም ወጥቶ ሥራ የፈቱ ሌሎችን በአደባባይ ቆመው አየ፤ 4እነዚያንም ‘እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ፤ የሚገባውንም እሰጣችኋለሁ፤’ አላቸው። እነርሱም ሄዱ። 5ደግሞም በስድስትና በዘጠኝ ሰዓት ወጥቶ እንዲሁ አደረገ። 6በአሥራ አንደኛውም ሰዓት ወጥቶ ሌሎችን ቆመው አገኘና ‘ሥራ ፈትታችሁ ቀኑን ሁሉ በዚህ ስለ ምን ትቆማላችሁ?’ አላቸው። 7‘የሚቀጥረን ስለ አጣን ነው፤’ አሉት። እርሱም ‘እናንተ ደግሞ ወደ ወይኔ አትክልት ሂዱ የሚገባውንም ትቀበላላችሁ፤’ አላቸው። 8በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ጌታ አዛዡን ‘ሠራተኞችን ጥራና ከኋለኞች ጀምረህ እስከ ፊተኞች ድረስ ደመወዝ ስጣቸው፤’ አለው። 9በአሥራ አንደኛው ሰዓትም የገቡ መጥተው እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ። 10ፊተኞችም በመጡ ጊዜ አብዝተው የሚቀበሉ መስሎአቸው ነበር፤ እነርሱም ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ። 11-12ተቀብለውም ‘እነዚህ ኋለኞች አንድ ሰዓት ሠሩ፤ የቀኑንም ድካምና ትኩሳት ከተሸከምን ከእኛ ጋር አስተካከልሃቸው፤’ ብለው በባለቤቱ ላይ አንጕኦራጕኦሩ። 13እርሱ ግን መልሶ ከእነርሱ ለአንዱ እንዲህ አለው ‘ወዳጄ ሆይ! አልበደልሁህም በአንድ ዲናር አልተስማማኸኝምን? 14ድርሻህን ውሰድና ሂድ፤ እኔ ለዚህ ለኋለኛው እንደ አንተ ልሰጠው እወዳለሁ፤ በገንዘቤ የወደድሁትን አደርግ ዘንድ መብት የለኝምን? 15ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንሁ ዐይንህ ምቀኛ ናትን? 16እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።’ ”
ኢየሱስ ስለ ሞቱና ስለ ትንሣኤው ለሦስትኛ ጊዜ እንደተናገረ
(ማር. 10፥32-34፤ ሉቃ. 18፥31-34)
17ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ሊወጣ ሳለ፥ በመንገድ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ብቻቸውን ወደ እርሱ አቅርቦ 18“እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች ይሰጣል፤ የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል፤ 19ሊዘባበቱበትም ሊገርፉትም ሊሰቅሉትም ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል፤” አላቸው።
ስለ ዘብዴዎስ ልጆች
(ማር. 10፥35-45)
20በዚያን ጊዜ የዘብዴዎስ ልጆች እናት ከልጆችዋ ጋር እየሰገደችና አንድ ነገር እየለመነች ወደ እርሱ ቀረበች። 21እርሱም “ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት። እርስዋም “እነዚህ ሁለቱ ልጆቼ አንዱ በቀኝህ አንዱም በግራህ በመንግሥትህ እንዲቀመጡ እዘዝ፤” አለችው። 22ኢየሱስ ግን መልሶ “የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ ልጠጣው ያለውን ጽዋ ልትጠጡ እኔም የምጠመቀውን ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን?” አለ። “እንችላለን” አሉት። 23እርሱም “ጽዋዬንስ ትጠጣላችሁ፤ በቀኝና በግራ መቀመጥ ግን ከአባቴ ዘንድ ለተዘጋጀላቸው ነው እንጂ እኔ የምሰጥ አይደለሁም፤” አላቸው። 24ዐሥሩም ሰምተው በሁለቱ ወንድማማች ተቍኦጡ። 25ኢየሱስ ግን ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው “የአሕዛብ አለቆች እንዲገዙአቸው ታላላቆቹም በላያቸው እንዲሠለጥኑ ታውቃላችሁ። 26በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፤ 27ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የእናንተ ባሪያ ይሁን፤ 28እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”
ስለ ሁለቱ ዐይነ ስውራን
(ማር. 10፥46-52፤ ሉቃ. 18፥35-43)
29ከኢያሪኮም ሲወጡ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት። 30እነሆም፥ ሁለት ዕውሮች በመንገድ ዳር ተቀምጠው፥ ኢየሱስ እንዲያልፍ በሰሙ ጊዜ “ጌታ ሆይ! የዳዊት ልጅ፥ ማረን” ብለው ጮኹ። 31ሕዝቡም ዝም እንዲሉ ገሠጹአቸው፤ እነርሱ ግን “ጌታ ሆይ! የዳዊት ልጅ፥ ማረን” እያሉ አብዝተው ጮኹ። 32ኢየሱስም ቆሞ ጠራቸውና “ምን ላደርግላችሁ ትወዳላችሁ?” አለ። 33“ጌታ ሆይ! ዐይኖቻችን ይከፈቱ ዘንድ” አሉት። 34ኢየሱስም አዘነላቸውና ዐይኖቻቸውን ዳሰሰ፤ ወዲያውም አዩና ተከተሉት።
Currently Selected:
የማቴዎስ ወንጌል 20: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ