የማ​ቴ​ዎስ ወን​ጌል 27:27-31

የማ​ቴ​ዎስ ወን​ጌል 27:27-31 አማ2000

በዚያን ጊዜ የገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ውስጥ ወሰዱት፤ ጭፍራውንም ሁሉ ወደ እርሱ አከማቹ። ልብሱንም ገፈው ቀይ ልብስ አለበሱት፤ ከእሾህም አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፤ በፊቱም ተንበርክከው “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን፤” እያሉ ዘበቱበት፤ ተፉበትም፤ መቃውንም ይዘው ራሱን መቱት። ከዘበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፤ ልብሱንም አለበሱት፤ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።