የማቴዎስ ወንጌል 3
3
የመጥምቁ ዮሐንስ ስብከት
(ማር. 1፥1-8፤ ሉቃ. 3፥1-18፤ ዮሐ. 1፥19-28)
1-2በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ። 3በነቢዩ በኢሳይያስ
“ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጥርጊያውንም አቅኑ’ እያለ
በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ”
የተባለለት ይህ ነውና። 4ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፤ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሓ ማር ነበረ። 5ያን ጊዜ ኢየሩሳሌም ይሁዳም ሁሉ በዮርዳኖስም ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይወጡ ነበር፤ 6ኀጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።
7ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው “እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ? 8እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤ 9በልባችሁም ‘አብርሃም አባት አለን’ እንደምትሉ አይምሰላችሁ፤ እላችኋለሁና ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል። 10አሁንስ ምሳር በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቍኦረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።
11እኔስ “ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤ 12መንሹም በእጁ ነው፤ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፤ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መጠመቅ
(ማር. 1፥9-11፤ ሉቃ. 3፥21-22)
13ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። 14ዮሐንስ ግን “እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል፤ አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?” ብሎ ይከለክለው ነበር። 15ኢየሱስም መልሶ “አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና” አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት። 16ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኀ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤ 17እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” አለ።
Currently Selected:
የማቴዎስ ወንጌል 3: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ