ኦሪት ዘኍልቍ 15
15
የመሥዋዕት ሕግ
1እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 2“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ወደምሰጣችሁ ወደ መኖሪያችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ 3በፈቃዳችሁም ቢሆን በበዓላችሁም ቢሆን ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ይሆን ዘንድ ስእለቱን አብዝታችሁ በአመጣችሁ ጊዜ ከላም ወይም ከበግ የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም መሥዋዕት የሚሆን የእሳት ቍርባን ለእግዚአብሔር አቅርቡ። 4ቍርባኑን ለእግዚአብሔር የሚያቀርብ የኢፍ መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ#የፈሳሽ መስፈሪያ። ዐሥረኛ እጅ የሆነ የመልካም ዱቄት መሥዋዕት ያመጣል። 5ለመጠጥ ቍርባንም የኢን መስፈሪያ የሆነ መልካም ዱቄት አራተኛ እጅ በሚቃጠለው መሥዋዕት ወይም በእህሉ ቍርባን ላይ ያደርጋል፤ ለእያንዳንዱ ጠቦት ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው መሥዋዕት ይሆን ዘንድ ይህን ያህል ያድርግ። 6ለአንዱም አውራ በግ የሚቃጠል ቍርባን ወይም መሥዋዕት ባደረጋችሁ ጊዜ የኢን መስፈሪያ ሢሶ በሆነ ዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት ለእህል ቍርባን ታዘጋጃላችሁ። 7ለመጠጥ ቍርባንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን የኢን መስፈሪያ ሦስተኛ እጅ ወይን ታቀርባለህ። 8ለሚቃጠልም መሥዋዕት፥ ወይም ለሌላ መሥዋዕት፥ ወይም ስእለትን ለመፈጸም፥ ወይም ለደኅንነት መሥዋዕት ከላም ወገን ለእግዚአብሔር ብታዘጋጅ፥ 9በላሙ ላይ የኢን መስፈሪያ ግማሽ በሆነ ዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ መልካም ዱቄት ለእህል ቍርባን ታቀርባለህ። 10ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን በእሳት ለተደረገ ቍርባን፥ የኢን መስፈሪያ ግማሽ ወይን ለመጠጥ ቍርባን ታቀርባለህ።
11“እንዲሁ ለእያንዳንዱ ወይፈን፥ ወይም ለእያንዳንዱ አውራ በግ፥ ወይም ለእያንዳንዱ ተባት የበግ ወይም የፍየል ጠቦት ይደረጋል። 12እንዳዘጋጃችሁት ቍጥር፥ እንዲሁ እንደ ቍጥራቸው ለእያንዳንዱ ታደርጋላችሁ። 13የሀገር ልጅ ሁሉ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን ቍርባን ባቀረበ ጊዜ እንዲሁ ያደርጋል። 14መጻተኛም ከእናንተ ጋር ቢቀመጥ፥ ወይም በትውልዳችሁ መካከል ማንም ሰው ቢኖር፥ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን ቍርባን በእሳት ቢያቀርብ እናንተ የምታደርጉትን እርሱ እንዲሁ ያደርጋል። 15ለእናንተ፥ በእናንተም መካከል ለሚኖሩ መጻተኞች አንድ ሥርዐት ይሆናል፤ ለልጅ ልጃችሁም የዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል፤ እናንተ እንደ ሆናችሁ እንዲሁ በእግዚአብሔር ፊት መጻተኛ ይሆናል። 16ለእናንተና ከእናንተ ጋር ለሚኖር መጻተኛ አንድ ሕግና አንድ ፍርድ ይሆናል።”
17እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ፤ ተናገረው፦ 18“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ 19ወደማመጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ እናንተ የምድሪቱን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ለእግዚአብሔር የተለየ ቍርባን ታደርጋላችሁ። 20መጀመሪያ ከምታደርጉት ሊጥ አንድ እንጎቻ ለይታችሁ ቍርባን ታቀርባላችሁ፤ ከአውድማውም እንደምትለዩት ቍርባን እንዲሁ ትለያላችሁ። 21መጀመሪያም ከምታደርጉት ሊጥ የተለየ#ዕብ. “የማንሣት” ይላል። ቍርባን እስከ ልጅ ልጃችሁ ለእግዚአብሔር ትሰጣላችሁ።
ስላልታወቀው ኀጢአት የሚቀርብ መሥዋዕት
22“ብትበድሉም፥ እግዚአብሔር ለሙሴ ያዘዛቸውን እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ ባታደርጉ፥ 23እግዚአብሔር ካዘዘበት ከፊተኛው ቀን ጀምሮ ወደ ፊትም እስከ ልጅ ልጃችሁ እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንደ አዘዛችሁ ባታደርጉ፥ 24በማኅበሩም ፊት ያልታወቀ ኀጢአት ቢኖር፥ ማኅበሩ ሁሉ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን ከመንጋዎች አንድ ንጹሕ ወይፈን ያቀርባሉ። የእህሉ ቍርባንና የመጠጡ ቍርባንም እንደ ሕጉ ነው፤ ለኀጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ያቀርባሉ። 25ካህኑም ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ያስተሰርይላቸዋል፤ ባለማወቅ ነበርና ይሰረይላቸዋል፤ እነርሱም ስለ ኀጢአታቸውና ስላለማወቃቸው ቍርባናቸውንና መሥዋዕታቸውን ለእግዚአብሔር ያቀርባሉ። 26በሕዝቡም ሁሉ ዘንድ ያለ ዕውቀት ተደርጎአልና ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ወደ እናንተም ለሚመጣ መጻተኛ ስርየት ይደረግላቸዋል።
27“አንድ ሰው ሳያውቅ ኀጢአት ቢሠራ፥ ስለ ኀጢአት አንዲት የአንድ ዓመት እንስት ፍየል ያቀርባል። 28ካህኑም ባለማወቅ ስለ በደለው ያስተሰርያል፤ ባለማወቅም በእግዚአብሔር ፊት ኀጢአት ስለ ሠራው ሰው ያስተሰርይለታል። 29ትውልዱ በእስራኤል ልጆች መካከል ቢሆን፥ ወይም በመካከላቸው የሚኖር መጻተኛ ቢሆን፥ ሳያውቅ ኀጢአትን ለሚሠራ ሁሉ ሕጉ አንድ ይሆንለታል። 30የሀገር ልጅ ቢሆንም ወይም መጻተኛ ቢሆን፥ በእጁ ትዕቢትን የሚያደርግ ሰው እግዚአብሔርን ሰድቦአል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋል። 31የእግዚአብሔርን ቃል ስለናቀ፥ ትእዛዙንም ስለ ሰበረ፥ ያ ሰው ፈጽሞ ይጥፋ፤ ኀጢአቱ በራሱ ላይ ነው።”
ሰንበትን ስለ ሻረ የተቀጣው ሰው
32የእስራኤልም ልጆች በምድረ በዳ ነበሩ፤ አንድ ሰውም በሰንበት ቀን ዕንጨት ሲለቅም አገኙ። 33በሰንበት ቀን ዕንጨት ሲለቅም ያገኙትም ሰዎች ወደ ሙሴና ወደ አሮን፥ ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ አመጡት። 34እንዴት እንደሚያደርጉት አልፈረዱምና በግዞት ቤት አዋሉት። 35እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “ሰውዬው ይገደል፤#ዕብ. “ከሰፈሩ ውጭ” ይላል። ማኅበሩም ሁሉ በድንጋይ ይውገሩት” አለው። 36ማኅበሩም ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ አወጡት፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው በድንጋይ ወገሩት።
በልብስ ላይ ስለሚደረግ ዘፈር
37እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 38“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፦ እነርሱም በትውልዳቸው ሁሉ በልብሳቸው ጫፍ ዘርፍ ያደርጉ ዘንድ፥ በዘርፉም ሁሉ ላይ ሰማያዊ ፈትል ያደርጉ ዘንድ እዘዛቸው። 39እርሱም በዘርፉ ይሁንላችሁ፤ ትመለከቱታላችሁም፤ የእግዚአብሔርንም ትእዛዛት ታስባላችሁ፤ ታደርጉአቸውማላችሁ፤ እነርሱን በመከተል ያመነዘራችሁባትን የሕሊናችሁንና የዐይኖቻችሁን ፈቃድ አትከተሉ። 40ትእዛዙን ታስቡና ታደርጉ ዘንድ፥ ለአምላካችሁም ቅዱሳን ትሆኑ ዘንድ፤ 41እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ አምላክ እሆናችሁ ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘኍልቍ 15: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ