ኦሪት ዘኍልቍ 28
28
የዘወትር መሥዋዕት
(ዘፀ. 29፥38-46)
1እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 2“የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ ቍርባኔን፥ መባዬንና የበጎ መዓዛ መሥዋዕቴን በበዓላት ቀኖች ታቀርቡልኝ ዘንድ ጠብቁ። 3እንዲህም በላቸው፦ በእሳት ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት ቍርባን ይህ ነው፤ ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ዕለት ዕለት ታቀርባላችሁ። 4አንዱን ጠቦት በማለዳ፥ ሌላውንም ጠቦት በማታ አቅርቡ፤ 5ለእህልም ቍርባን የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ፥ ተወቅጦ በተጠለለ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ ዐሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት ታቀርባላችሁ። 6በእሳት ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን የቀረበ፥ በሲና ተራራ የተሠራ ለዘወትር የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። 7የመጠጡም ቍርባን ለአንድ ጠቦት የኢን መስፈሪያ አራተኛው እጅ ነው፤ በመቅደሱ ውስጥ ለእግዚአብሔር ለመጠጥ ቍርባን መጠጥ ታፈስሳላችሁ። 8ሌላውንም ጠቦት በማታ ጊዜ ታቀርባላችሁ፤ የእህሉን ቍርባንና የመጠጡን ቍርባን በማለዳ እንዳቀረባችሁ በእሳት ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን ታቀርቡታላችሁ።
የሰንበት መሥዋዕት
9“በሰንበትም ቀን ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ ለእህልም ቍርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት፥ የመጠጡንም ቍርባን ታቀርባላችሁ። 10በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕት ሌላ፥ ከመጠጡም ቍርባን ሌላ፥ በየሰንበቱ ሁሉ የምታቀርቡት የሚቃጠለው መሥዋዕት ይህ ነው።
በመባቻ የሚቀርብ መሥዋዕት
11“በወሩም መባቻ ለእግዚአሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ከላሞች ሁለት፥ አንድ አውራ በግ፥ ነውርም የሌለባቸውን ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ 12ለእያንዳንዱም ወይፈን ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ መልካም ዱቄት፥ ለአውራው በግ ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ፥ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት፥ 13ለእያንዳንዱም ጠቦት ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ፥ ከመስፈሪያው ዐሥረኛ እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን በእሳት ታቀርባላችሁ። 14የመጠጥ ቍርባናቸውም ለአንድ ወይፈን የኢን ግማሽ፥ ለአውራው በግም የኢን ሲሦ፥ ለአንዱም ጠቦት የኢን አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ይሆናል፤ ይህ ለዓመቱ የወር መባቻ ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። 15ለእግዚአብሔርም ስለኀጢአት መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል ታቀርባላችሁ፤ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከመጠጡ ቍርባን ሌላ ይቀርባል።
በፋሲካና በበዓለ ናዕት የሚቀርብ መሥዋዕት
(ዘሌ. 23፥5-14)
16“በመጀመሪያው ወር ከወሩም በዐሥራ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው። 17በዚህም ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን በዓል ይሆናል፤ ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ። 18የመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ይሁንላችሁ፤ በእርሱም የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት። 19በእሳትም የተደረገውን ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ከላሞች ሁለት በሬዎች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ነውር የሌለባቸው ይሁኑላችሁ። 20የእህል ቍርባናቸውንም በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ለአንድ ወይፈን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአውራውም በግ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ፥ 21ለሰባቱም ጠቦቶች ለእያንዳንዱ ጠቦት ከመስፈሪያው ዐሥረኛ እጅ ታቀርባላችሁ። 22ማስተስረያ የሚሆንላችሁን ከፍየሎች አንድ አውራ ፍየል ለኀጢአት መሥዋዕት ታቀርባላችሁ። 23ማልዶ ከሚቀርበው በዘወትር ከሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ እነዚህን ታቀርባላችሁ። 24ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን በእሳት የሚደረገውን ቍርባንና መሥዋዕት ሰባት ቀን በየዕለቱ እንዲሁ ታቀርባላችሁ፤ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከመጠጡ ቍርባን ሌላ ይቀርባል። 25ሰባተኛውም ቀን የተቀደሰ ይሁንላችሁ፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት።
በበዓለ ሠዊት የሚቀርብ መሥዋዕት
(ዘሌ. 23፥15-22)
26“በበዓለ ሠዊት ቀን በሰንበታት በዓላችሁ አዲሱን የእህል ቍርባን ለእግዚአብሔር ባቀረባችሁ ጊዜ፥ የተቀደሰ ቀን ይሆንላችኋል፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት። 27ለእግዚአብሔርም በጎ መዓዛ እንዲሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ከላሞች ሁለት በሬዎች፥ አንድ አውራ በግ፥ ሰባት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች፥ 28ለእህል ቍርባናቸው በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ለእያንዳንዱ ወይፈን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ፥ ለአንዱም አውራ በግ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ፥ 29ለሰባቱም ጠቦቶች ለእያንዳንዱ ጠቦት ከመስፈሪያው ዐሥረኛ እጅ ታቀርባላችሁ። 30ማስተስረያ የሚሆንላችሁን ከፍየሎች አንድ አውራ ፍየል ለኀጢአት መሥዋዕት ታቀርባላችሁ። 31በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ሌላ እነርሱንና የመጠጥ ቍርባናቸውን ታቀርባላችሁ፤ ነውርም የሌለባቸው ይሁኑ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘኍልቍ 28: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ