ኦሪት ዘኍልቍ 31
31
በምድያማውያን ላይ የተደረገ ጦርነት
(ዘዳ. 3፥12-22)
1እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 2“የእስራኤልን ልጆች በቀል ምድያማውያንን ተበቀል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ወገኖችህ ትጨመራለህ።” 3ሙሴም ለሕዝቡ እንዲህ ብሎ ነገራቸው፥ “ከእናንተ መካከል ሰዎችን አስታጥቁ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምድያምን ይበቀሉ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ከምድያም ጋር ይሰለፉ። 4ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ ሰው ወደ ጦርነት ስደዱ፤” 5ከእስራኤልም አእላፋት፥ ከየነገዱ አንድ አንድ ሺህ ቈጠሩ፤ ለጦርነት የተሰለፉትም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሆኑ። 6ሙሴም ከየነገዱ አንድ ሺህ ከሠራዊታቸውና ከካህኑ ከአሮን ልጅ ከአልዓዛር ልጅ ከፊንሐስ ጋር ሰደደ፤ ንዋያተ ቅድሳቱና ምልክት መስጫ መለከቶችም በእጆቻቸው ነበሩ። 7እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘ ከምድያም ጋር ተዋጉ፤ ወንዶችንም ሁሉ ገደሉ። 8የምድያምንም ነገሥታት በዚያው ጦርነት በአንድነት ገደሉአቸው፤ አምስቱም የምድያም ነገሥታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥ ሑር፥ ሮባቅ ነበሩ፤ የቢዖርንም ልጅ በለዓምን ደግሞ በዚያው ጦርነት በሰይፍ ገደሉት። 9የምድያምንም ሴቶችና ልጆቻቸውን#“ልጆቻቸውን” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ማረኩ፤ እንስሶቻቸውንና ዕቃቸውን፥ ንብረታቸውንና ኀይላቸውን በዘበዙ።
10የተቀመጡባቸውን ከተሞቻቸውን ሁሉ፥ ሰፈሮቻቸውንም ሁሉ በእሳት አቃጠሉ። 11ከሰው እስከ እንስሳ ምርኮአቸውንና ብዝበዛቸውን ሁሉ ወሰዱ። 12የማረኩትን ምርኮውንና የዘረፉትን ወደ ሙሴና ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፥ ወደ እስራኤልም ልጆች፥ በዮርዳኖስም አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ወዳለው ሰፈር አመጡ።
የሠራዊቱ ከጦርነት መመለስ
13ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም፥ የማኅበሩም አለቆች ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ ሊገናኙአቸው ወጡ። 14ሙሴም ከዘመቻ በተመለሱት በጭፍራ አለቆች፥ በሻለቆችና በመቶ አለቆች ላይ ተቈጣ። 15ሙሴም አላቸው፥ “ሴቶችን ሁሉ ለምን አዳናችኋቸው? 16እነርሱ በበለዓም ምክር በፌጎር ምክንያት የእስራኤልን ልጆች የሚያስቱ፥ የእግዚአብሔርንም ቃል እንዲስቱ የሚያደርጉ ዕንቅፋቶች ናቸውና፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ማኅበር ላይ መቅሠፍት ሆኖአል፤ 17አሁንም እንግዲህ#ዕብ. “ከልጆቹ” ይላል። ወንዱን ሁሉ በአለበት ግደሉ፥ ወንድንም የምታውቀውን ሴት ሁሉ ግደሉ። 18ወንድን የማያውቁትን ሴቶች ልጆችን ሁሉ ግን#ዕብ. “ለራሳችሁ” ይላል። አድኑአቸው። 19እናንተም ከሰፈሩ ውጭ ሰባት ቀን ስፈሩ፤ ሰውን የገደለ ሁሉ፥ የተገደለውንም የዳሰሰ ሁሉ፥ እናንተና የማረካችኋቸውም በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሰውነታችሁን ንጹሕ አድርጉ። 20ልብስንም፥ ከቁርበትም የተዘጋጀውን ሁሉ፥ ከፍየልም ጠጕር፥ ከዕንጨትም የተሠራውን ሁሉ ንጹሕ አድርጉ።”
21ካህኑም አልዓዛር ከሰልፍ የመጡትን ሰዎች አላቸው፥ “እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘው የሕጉ ሥርዐት ይህ ነው፤ 22ወርቁና ብሩ፥ ናሱም፥ ብረቱም፥ ቆርቆሮውም፥ እርሳሱም፥ 23በእሳት ለማለፍ የሚችለው ነገር ሁሉ፥ #ዕብ. “በእሳት ታሳልፉታላችሁ” ይላል። ንጹሕ ይሆናል፤ ነገር ግን በማንጻት ውኃ ደግሞ ይጠራል። በእሳትም ለማለፍ የማይችለውን በውኃ ታሳልፉታላችሁ። 24በሰባተኛውም ቀን ልብሳችሁን እጠቡ፤ ንጹሓንም ትሆናላችሁ፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ትቀርባላችሁ።”
ምርኮ እንደ ተካፈሉ
25እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 26“አንተና ካህኑ አልዓዛር፥ የማኅበሩም አባቶች አለቆች የተማረኩትን ሰውና እንስሳ ቍጠሩ። 27ምርኮውንም በተዋጉትና ወደ ሰልፍ በወጡት፥ በማኅበሩም ሁሉ መካከል ትከፍላላችሁ። 28ከእነዚያም ከተዋጉት፥ ወደ ሰልፍም ከወጡት ሰልፈኞች ዘንድ ከሰዎችም፥ ከበሬዎችም፥ ከበጎችም፥ ከአህዮችም፥ ከአምስት መቶ አንድ ለእግዚአብሔር ግብር ታወጣላችሁ። 29ከድርሻቸው እኩሌታ ወስደህ የእግዚአብሔርን ቀዳምያት ለካህኑ ለአልዓዛር ትሰጠዋለህ። 30ከእስራኤልም ልጆች ድርሻ እኩሌታ፥ ከሰዎችም፥ ከበሬዎችም፥ ከበጎችም፥ ከአህዮችም፥ ከእንስሶችም ሁሉ ከአምሳ አንድ ትወስዳለህ፤ የእግዚአብሔርንም ድንኳን ሥርዐት ለሚጠብቁ ለሌዋውያን ትሰጣለህ።” 31ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።
32ወደ ሰልፍ የወጡ ሰዎችም ከወሰዱት ብዝበዛ የቀረው ምርኮ እንዲህ ሆነ፤ ስድስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ በጎች፤ 33ሰባ ሁለት ሺህ በሬዎች፥ 34ስድሳ አንድ ሺህ አህዮች፥ 35ወንድ ከማያውቁ ሴቶችም ሠላሳ ሁለት ሺህ ነፍስ። 36በዘመቻም ለነበሩ ሰዎች ድርሻ የሆነ እኩሌታ ከበግ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ሺህ አምስት መቶ በጎች ነበሩ፤ 37ከበጎችም የእግዚአብሔር ግብር ስድስት መቶ ሰባ አምስት ነበረ። 38በሬዎችም ሠላሳ ስድስት ሺህ ነበሩ፤ የእግዚአብሔርም ግብር ሰባ ሁለት ነበረ። 39አህዮቹም ሠላሳ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ፤ የእግዚአብሔርም ግብር ስድሳ አንድ ነበረ። 40ሰዎቹም ዐሥራ ስድስት ሺህ ነበሩ ፤ የእግዚአብሔርም ግብር ሠላሳ ሁለት ነበረ። 41እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ሙሴ፦ ለእግዚአብሔር የለዩትን ግብር ለካህኑ ለአልዓዛር ሰጠው።
42ከእስራኤል ልጆች እኩሌታም፥ ወደ ሰልፍ ከወጡት ወንዶች ላይ ሙሴ የለየው፥ 43የማኅበሩ ድርሻ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ሺህ አምስት መቶ በጎች፥ 44ሠላሳ ስድስት ሺህ በሬዎች፤ 45ሠላሳ ሺህ አምስት መቶ አህዮች፥ 46ዐሥራ ስድስት ሺህ ሰዎች ነበሩ። 47ሙሴ ከእስራኤል ልጆች ድርሻ ከሰውና ከእንስሳ ከሃምሳ አንድ ወሰደ፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ድንኳን ሥርዐት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ሰጠ።
48በሠራዊት አእላፋት ላይ የተሾሙት አለቆች፥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች ወደ ሙሴ ቀረቡ፤ ሙሴንም እንዲህ አሉት፦ 49“ባሪያዎችህ ወደ ሰልፍ የወጡትን ከእጃችን በታች ያሉትን ቈጠሩ፤ ከእኛም አንድ አልጐደለም። 50ሰውም ሁሉ ከአገኘው ከወርቅ ዕቃ፥ ከእግር አልቦም፥ ከአምባርም፥ ከቀለበትም ከጕትቻም፥ ከድሪውም ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ታስተሰርዩልን ዘንድ ለእግዚአብሔር መባ አምጥተናል” አሉት። 51ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም ወርቁንና በልዩ ልዩ የተሠራውን ዕቃ ሁሉ ከእጃቸው ተቀበሉ። 52ከሻለቆችና ከመቶ አለቆች ለእግዚአብሔር የለዩትና ያቀረቡት ወርቅ ሁሉ ዐሥራ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ አምሳ ሰቅል ነበረ። 53ወደ ሰልፍ የወጡ ሰዎች ሁሉ የማረኩትን ለየራሳቸው ወሰዱ። 54ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም ወርቁን ከሻለቆችና ከመቶ አለቆች ወሰዱ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ ወደ ምስክሩ ድንኳን አገቡት።
Currently Selected:
ኦሪት ዘኍልቍ 31: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ