የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 33

33
ከግ​ብፅ እስከ ሞዐብ የተ​ደ​ረገ ጕዞ
1በሙ​ሴና በአ​ሮን እጅ ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ከግ​ብፅ ከወጡ በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የሰ​ፈ​ሩ​በት ይህ ነው። 2ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ እንደ ተጓዙ የሰ​ፈ​ሩ​በ​ትን ጻፈ፥ እየ​ተ​ጓዙ ያደ​ሩ​በት ይህ ነው። 3በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን ከራ​ምሴ ተጓዙ፤ ከፋ​ሲካ በኋላ በነ​ጋው የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን ሁሉ ፊት ከፍ ባለች እጅ ወጡ። 4በዚ​ያም ጊዜ ግብ​ፃ​ው​ያን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የገ​ደ​ላ​ቸ​ውን በኵ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ይቀ​ብሩ ነበር፤ በአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈረ​ደ​ባ​ቸው።
5የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከራ​ምሴ ተጕ​ዘው በሱ​ኮት ሰፈሩ። 6ከሱ​ኮ​ትም ተጕ​ዘው በም​ድረ በዳ ዳርቻ ባለች በኤ​ታም ሰፈሩ። 7ከኤ​ታ​ምም ተጕ​ዘው በኤ​ል​ሴ​ፎን ፊት ወደ ነበ​ረች በኤ​ሮት በር፤ በመ​ግ​ደሎ ፊት ለፊት ሰፈሩ። 8ከኤ​ሮ​ትም ፊት ለፊት ተጕ​ዘው በባ​ሕሩ መካ​ከል ወደ ምድረ በዳ ተሻ​ገሩ፤ በኤ​ታ​ምም በረሃ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ሄደው በም​ረት ሰፈሩ። 9ከም​ረ​ትም ተጕ​ዘው ወደ ኤሊም መጡ፤ በኤ​ሊ​ምም ዐሥራ ሁለት የውኃ ምን​ጮች፥ ሰባ ዘን​ባ​ቦ​ችም ነበሩ፤ በዚ​ያም በውኃ አጠ​ገብ ሰፈሩ። 10ከኤ​ሊ​ምም ተጕ​ዘው በኤ​ር​ትራ ባሕር ዳር ሰፈሩ። 11ከኤ​ር​ት​ራም ባሕር ተጕ​ዘው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ። 12ከሲና ምድረ በዳም ተጕ​ዘው በራ​ፋቃ ሰፈሩ። 13ከራ​ፋ​ቃም ተጕ​ዘው በኤ​ሉስ ሰፈሩ። 14ከኤ​ሉ​ስም ተጕ​ዘው በራ​ፊ​ድን ሰፈሩ፤ በዚ​ያም ሕዝቡ የሚ​ጠ​ጡት ውኃ አል​ነ​በ​ረም። 15ከራ​ፊ​ድ​ንም ተጕ​ዘው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ። 16ከሲና ምድረ በዳም ተጕ​ዘው በም​ኞት መቃ​ብር ሰፈሩ። 17ከም​ኞት መቃ​ብ​ርም ተጕ​ዘው በአ​ቤ​ሮት ሰፈሩ። 18ከአ​ቤ​ሮ​ትም ተጕ​ዘው በራ​ታማ ሰፈሩ። 19ከራ​ታ​ማም ተጕ​ዘው በሬ​ሞት ዘፋ​ሬስ ሰፈሩ። 20ከሬ​ሞት ዘፋ​ሬ​ስም ተጕ​ዘው በል​ብና ሰፈሩ። 21ከል​ብ​ናም ተጕ​ዘው በሪሳ ሰፈሩ። 22ከሪ​ሳም ተጕ​ዘው በመ​ቄ​ላት ሰፈሩ። 23ከመ​ቄ​ላ​ትም ተጕ​ዘው በሳ​ፋር ሰፈሩ። 24ከሳ​ፋ​ርም ተጕ​ዘው በካ​ሬ​ደት ሰፈሩ። 25ከካ​ሬ​ደ​ትም ተጕ​ዘው በመ​ቄ​ሎት ሰፈሩ። 26ከመ​ቄ​ሎ​ትም ተጕ​ዘው በቀ​ጠ​አት ሰፈሩ። 27ከቀ​ጠ​አ​ትም ተጕ​ዘው በተ​ሪት ሰፈሩ። 28ከተ​ሪ​ትም ተጕ​ዘው በሚ​ትቃ ሰፈሩ። 29ከሚ​ት​ቃም ተጕ​ዘው በኤ​ሴ​ምና ሰፈሩ። 30ከኤ​ሴ​ም​ናም ተጕ​ዘው በመ​ሱ​ሩት ሰፈሩ። 31ከመ​ሱ​ሩ​ትም ተጕ​ዘው በብ​ን​ያ​ቅን ሰፈሩ። 32ከብ​ን​ያ​ቅ​ንም ተጕ​ዘው በገ​ድ​ገድ ተራራ ሰፈሩ። 33ከገ​ድ​ገ​ድም ተጕ​ዘው በአ​ጤ​ቤት ሰፈሩ። 34ከአ​ጤ​ቤ​ትም ተጕ​ዘው በኤ​ብ​ሮና ሰፈሩ። 35ከኤ​ብ​ሮ​ናም ተጕ​ዘው በጋ​ስ​ዮ​ን​ጋ​ቤር ሰፈሩ። 36ከጋ​ስ​ዮ​ን​ጋ​ቤ​ርም ተጕ​ዘው በጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ። ከጺን ምድረ በዳም ተጕ​ዘው በፋ​ራን ምድረ በዳ ሰፈሩ። ይህ​ችም ቃዴስ ናት። 37ከቃ​ዴ​ስም ተጕ​ዘው በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድር ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ ሰፈሩ።
38ካህ​ኑም አሮን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፤ በዚ​ያም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በአ​ር​ባ​ኛው ዓመት፥ በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር፥ ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ሞተ። 39አሮ​ንም በሖር ተራራ ላይ በሞተ ጊዜ ዕድ​ሜው መቶ ሃያ ሦስት ዓመት ነበረ።
40በከ​ነ​ዓን ምድ​ርም ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረው ከነ​ዓ​ና​ዊው የዓ​ራድ ንጉሥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እንደ መጡ ሰማ። 41እነ​ር​ሱም ከሖር ተራራ ተጕ​ዘው በሴ​ል​ሞና ሰፈሩ። 42ከሴ​ል​ሞ​ናም ተጕ​ዘው በፌኖ ሰፈሩ። 43ከፌ​ኖም ተጕ​ዘው በአ​ቦት ሰፈሩ። 44ከአ​ቦ​ትም ተጕ​ዘው በሞ​ዓብ ዳርቻ ባለው በጋይ ሰፈሩ። 45ከጋ​ይም ተጕ​ዘው በዲ​ቦ​ን​ጋድ ሰፈሩ። 46ከዲ​ቦ​ን​ጋ​ድም ተጕ​ዘው በጌ​ል​ሞ​ን​ዲ​ብ​ላ​ታ​ይም ሰፈሩ። 47ከጌ​ል​ሞ​ን​ዲ​ብ​ላ​ታ​ይ​ምም ተጕ​ዘው በና​ባው ፊት ባሉት በአ​ባ​ሪም ተራ​ሮች ላይ ሰፈሩ። 48በና​ባው ፊት ካሉት ከአ​ባ​ሪም ተራ​ሮ​ችም ተጕ​ዘው በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል ባለው በሞ​ዓብ ምዕ​ራብ ሰፈሩ። 49በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም አጠ​ገብ በሞ​ዓብ ምዕ​ራብ ከአ​ሲ​ሞት መካ​ከል እስከ አቤ​ል​ሰ​ጢም ድረስ ሰፈሩ።
እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ዮር​ዳ​ኖ​ስን ከመ​ሻ​ገ​ራ​ቸው በፊት የተ​ሰ​ጣ​ቸው መመ​ሪያ
50እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ በኩል በሞ​ዓብ ምዕ​ራብ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው። 51“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ወደ ከነ​ዓን ምድር ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤ 52በዚ​ያ​ችም ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ከፊ​ታ​ችሁ አጥ​ፉ​አ​ቸው፤ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ት​ንም ድን​ጋ​ዮ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ ታጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ ታጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ በኮ​ረ​ብታ ላይ ያሉ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ታፈ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤ 53በዚ​ያች ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም አጥ​ፍ​ታ​ችሁ በው​ስ​ጥዋ ኑሩ። ምድ​ሪ​ቱን ለእ​ና​ንተ ርስት አድ​ርጌ ሰጥ​ቼ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና። 54ምድ​ሪ​ቱ​ንም ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ች​ሁም ትከ​ፋ​ፈ​ሏ​ታ​ላ​ችሁ፤ ለብ​ዙ​ዎች ድር​ሻ​ቸ​ውን አብ​ዙ​ላ​ቸው፤ ለጥ​ቂ​ቶ​ችም ድር​ሻ​ቸ​ውን ጥቂት አድ​ርጉ፤ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሁሉ ዕጣ እንደ ወደ​ቀ​ለት በዚያ ርስቱ ይሆ​ናል፤ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ነገ​ዶች ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ። 55የሀ​ገ​ሩ​ንም ስዎች ከፊ​ታ​ችሁ ባታ​ሳ​ድዱ፥ ያስ​ቀ​ራ​ች​ኋ​ቸው ለዐ​ይ​ና​ችሁ እንደ እሾህ፥ ለጐ​ና​ች​ሁም እንደ አሜ​ከላ ይሆ​ኑ​ባ​ች​ኋል፤ በም​ት​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም ምድር ያስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ች​ኋል። 56እኔም በእ​ነ​ርሱ አደ​ር​ገው ዘንድ ያሰ​ብ​ሁ​ትን በእ​ና​ንተ አደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ