የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ፊል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች 3

3
ስለ​ሚ​ያ​በ​ረ​ታታ ትም​ህ​ርት
1አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ በጌ​ታ​ችን ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ እኔም ስጽ​ፍ​ላ​ችሁ ቸል አል​ልም፤ ያበ​ረ​ታ​ች​ኋ​ልና። 2ከው​ሾች ተጠ​በቁ፤ ከክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎ​ችም ተጠ​በቁ፤ ሥጋ​ቸ​ውን ብቻ በመ​ቍ​ረጥ ተገ​ዝ​ረ​ናል ከሚ​ሉም ተጠ​በቁ። 3ግዙ​ራ​ንስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ን​ፈስ የም​ና​ገ​ለ​ግ​ለ​ውና የም​ና​መ​ል​ከው እኛ ነን፤ እኛም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እን​መ​ካ​ለን እንጂ በሥ​ጋ​ችን የም​ን​መካ አይ​ደ​ለም። 4እኔም ግዝ​ረት ሳለኝ በግ​ዝ​ረት አል​መ​ካም፤ በግ​ዝ​ረት መመ​ካ​ትን የሚ​ያ​ስብ ካለም እኔ እር​ሱን እበ​ል​ጠ​ዋ​ለሁ።#ግሪኩ “እኔ በሥጋ ደግሞ የም​ታ​መ​ን​በት አለኝ፤ ሌላ ሰው ማንም ቢሆን በሥጋ የሚ​ታ​መ​ን​በት እን​ዳ​ለው ቢመ​ስ​ለው እኔ እበ​ል​ጠ​ዋ​ለሁ” ይላል። 5#የሐዋ. 23፥6፤ 26፥5፤ ሮሜ 11፥1። በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን የተ​ገ​ዘ​ርሁ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ከብ​ን​ያም ነገድ ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ዕብ​ራዊ ነኝ፤ በኦ​ሪ​ትም ፈሪ​ሳዊ ነበ​ርሁ። 6#የሐዋ. 8፥3፤ 22፥4፤ 26፥9-11። በኦ​ሪት ጽድ​ቅም ያለ ነውር ሆኜ በቅ​ን​ዐት ምእ​መ​ና​ንን አሳ​ድድ ነበር። 7ነገር ግን ስለ ክር​ስ​ቶስ ያን ጥቅ​ሜን ላጣው ወደ​ድሁ። 8ክር​ስ​ቶ​ስን አገ​ለ​ግ​ለው ዘንድ፥ ሁሉን የተ​ው​ሁ​ለት፥ እንደ ጕድ​ፍም ያደ​ረ​ግ​ሁ​ለት የጌ​ታ​ዬን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ኀይ​ልና ገና​ና​ነት ስለ​ማ​ውቅ ሁሉን እንደ ኢም​ንት ቈጠ​ር​ሁት። 9በእ​ር​ሱም እጸና ዘንድ፥ ዛሬ የኦ​ሪት ጽድቅ ሳይ​ኖ​ረኝ ክር​ስ​ቶ​ስን በማ​መን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገኝ ጽድቅ አለኝ እንጂ። 10በእ​ር​ሱም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ የመ​ነ​ሣ​ቱ​ንም ኀይል በሕ​ማሙ እሳ​ተ​ፈ​ዋ​ለሁ፤ በሞ​ቱም እመ​ስ​ለ​ዋ​ለሁ። 11ይኸ​ውም ሙታን በሚ​ነሡ ጊዜ ምና​ል​ባት በዚህ አገ​ኘው እንደ ሆነ ብዬ ነው።
ዋጋን ስለ መጠ​ባ​በቅ
12ነገር ግን ይህን ፈጽሜ የተ​ቀ​በ​ልሁ አይ​ደ​ለም፤ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስለ እርሱ እኔን የመ​ረ​ጠ​በ​ትን አገኝ ዘንድ እሮ​ጣ​ለሁ እንጂ። 13ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እኔ ግን ፍጻ​ሜ​ዬን ገና ያገ​ኘሁ አይ​መ​ስ​ለ​ኝም። 14የኋ​ላ​ዬን እረ​ሳ​ለ​ሁና፥ ወደ ፊቴም ፈጥኜ እገ​ሠ​ግ​ሣ​ለ​ሁና፤ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ከፍ ከፍ ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የጥሪ ዋጋ ለማ​ግ​ኘት ወደ ግቡ እፈ​ጥ​ና​ለሁ።
ስለ ፍጹ​ማን ምእ​መ​ናን
15ፍጹ​ማን የሆ​ና​ችሁ ሁላ​ችሁ ይህን አስቡ፤ ሌላ የም​ታ​ስ​ቡት ቢኖ​ርም፥ እር​ሱን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገ​ል​ጥ​ላ​ች​ኋል። 16ነገር ግን በደ​ረ​ስ​ን​በት ሥራ በአ​ን​ድ​ነት እን​በ​ርታ። 17#1ቆሮ. 4፥16፤ 11፥1። ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እኔን ምሰሉ፤ እን​ዲህ ባለ መን​ገድ የሚ​ሄ​ዱ​ት​ንም እኛን ታዩ እንደ ነበ​ረ​በት ጊዜ ተጠ​ባ​በ​ቋ​ቸው። 18ዘወ​ትር እን​ደ​ም​ነ​ግ​ራ​ችሁ፥ ልዩ አካ​ሄድ የሚ​ሄዱ ብዙ​ዎች አሉና፤ አሁ​ንም እነ​ርሱ የክ​ር​ስ​ቶስ የመ​ስ​ቀሉ ጠላ​ቶች እንደ ሆኑ በግ​ልጥ እያ​ለ​ቀ​ስሁ#“እያ​ለ​ቀ​ስሁ” የሚ​ለው በግ​እዙ የለም። እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ። 19እነ​ዚ​ህም ፍጻ​ሜ​ያ​ቸው ለጥ​ፋት የሆነ፥ ሆዳ​ቸ​ውን የሚ​ያ​መ​ልኩ፥ ክብ​ራ​ቸ​ውም ውር​ደት የሆ​ነ​ባ​ቸው፥ ምድ​ራ​ዊ​ዉ​ንም የሚ​ያ​ስቡ ናቸው። 20እኛስ ሀገ​ራ​ችን በሰ​ማይ ያለ​ችው ናት፤ ከዚ​ያም እር​ሱን ጌታ​ችን መድ​ኀ​ኒ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን እን​ጠ​ባ​በ​ቃ​ለን። 21እር​ሱም እንደ ከሃ​ሊ​ነቱ ረዳ​ት​ነት መጠን የተ​ዋ​ረ​ደ​ውን ሥጋ​ች​ንን የሚ​ያ​ድ​ሰው፥ ክቡር ሥጋ​ዉ​ንም እን​ዲ​መ​ስል የሚ​ያ​ደ​ር​ገው፥ የሚ​ያ​ስ​መ​ስ​ለ​ውም፥ ሁሉም የሚ​ገ​ዛ​ለት ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ