የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ፊል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች 4

4
1አሁ​ንም የተ​ወ​ደ​ዳ​ች​ሁና የም​ና​ፍ​ቃ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ደስ​ታ​ች​ንና አክ​ሊ​ላ​ችን ናችሁ፤ ወዳ​ጆ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ዲህ ቁሙ፤ በጌ​ታ​ች​ንም ጽኑ። 2ኤዎ​ድ​ያና ስን​ጣ​ክን#“ኤዎ​ድ​ያና ስን​ጣ​ክን” በግ​ሪኩ ሴቶች መሆ​ና​ቸው ተገ​ል​ጦ​አል። ሆይ፥ በአ​ንድ ልብ ጌታ​ች​ንን ለማ​ገ​ል​ገል ታስቡ ዘንድ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ። 3ወን​ድ​ሜና አጋዤ ስት​ሪካ#“ስት​ሪካ” የሚ​ለው በግ​እዝ ብቻ ነው። ሆይ፥ እን​ድ​ት​ረ​ዳ​ቸው አን​ተ​ንም እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ወን​ጌ​ልን በማ​ስ​ተ​ማር ከቀ​ሌ​ም​ን​ጦ​ስና ሥራ​ቸው ከተ​ባ​በረ፥ ስማ​ቸ​ውም በሕ​ይ​ወት መጽ​ሐፍ ከተ​ጻ​ፈ​ላ​ቸው ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ሁሉ ጋር ከእ​ኔም ጋር ደክ​መ​ዋ​ልና።
4ዘወ​ትር በጌ​ታ​ችን ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ደግሜ እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ደስ ይበ​ላ​ችሁ። 5ፍጹ​ም​ነ​ታ​ች​ሁም#ግሪኩ “ገር​ነ​ታ​ችሁ” ይላል። በሰው ሁሉ ዘንድ ይታ​ወቅ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅርብ ነው፤ 6በም​ንም አት​ጨ​ነቁ፤ ነገር ግን በሁሉ ነገር ጸልዩ ማል​ዱም፤ እያ​መ​ሰ​ገ​ና​ች​ሁም ልመ​ና​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግለጡ። 7ሁሉ የሚ​ገ​ኝ​ባት፥ ከል​ቡ​ናና ከአ​ሳብ ሁሉ በላይ#“ሁሉ የሚ​ገ​ኝ​ባት ... ከአ​ሳ​ብም ሁሉ በላይ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። የም​ት​ሆን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰላም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ልባ​ች​ሁ​ንና አሳ​ባ​ች​ሁን ታጽ​ናው።
8አሁ​ንም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እው​ነ​ትን ሁሉ፥ ቅን​ነ​ት​ንም ሁሉ፥ ጽድ​ቅ​ንም ሁሉ፥ ንጽ​ሕ​ና​ንም ሁሉ፥ ፍቅ​ር​ንና ስም​ም​ነ​ት​ንም ሁሉ፥ በጎ​ነ​ትም ቢሆን፥ ምስ​ጋ​ናም ቢሆን፥ እነ​ዚ​ህን ሁሉ አስቡ። 9ከእኔ የተ​ማ​ራ​ች​ሁ​ት​ንና የተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁ​ትን፥ የሰ​ማ​ች​ሁ​ት​ንና ያያ​ች​ሁ​ት​ንም እነ​ዚ​ህን አድ​ርጉ፤ የሰ​ላም አም​ላ​ክም ከሁ​ላ​ችሁ ጋር ይሆ​ናል።
የፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ምእ​መ​ናን ስላ​ደ​ረ​ጉት አስ​ተ​ዋ​ፅኦ ምስ​ጋና
10በጌ​ታ​ችን እጅግ ደስ አለኝ፤ ቢሳ​ና​ችሁ እንኳ አሁ​ንም እን​ደ​ም​ታ​ስ​ቡ​ልኝ፥ ከዱሮ ጀምሮ ለእኔ ችግር ታስቡ፥ ትተ​ጉም ነበ​ርና። 11ይህ​ንም የምል ስለ አጣሁ አይ​ደ​ለም፤ ያለኝ እን​ደ​ሚ​በ​ቃኝ አው​ቃ​ለ​ሁና። 12እኔ ችግ​ሩ​ንም፥ ምቾ​ቱ​ንም እች​ላ​ለሁ፤ ራቡ​ንም፥ ጥጋ​ቡ​ንም፥ ማዘ​ኑ​ንም፥ ደስ​ታ​ው​ንም፥#“ማዘ​ኑ​ንም ደስ​ታ​ው​ንም” በሚ​ለው ፈንታ ግሪኩ “ማጣ​ት​ንም ማግ​ኘ​ት​ንም” ይላል። ሁሉን በሁሉ ለም​ጀ​ዋ​ለሁ፤ 13በሚ​ያ​ስ​ች​ለኝ በክ​ር​ስ​ቶስ ሁሉን እች​ላ​ለሁ። 14ነገር ግን በመ​ከ​ራዬ ጊዜ ተባ​ባ​ሪ​ዎች መሆ​ና​ችሁ መል​ካም አደ​ረ​ጋ​ችሁ። 15#2ቆሮ. 11፥9። እና​ንተ የፊ​ል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ትም​ህ​ርት ከመ​ቄ​ዶ​ንያ ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ፥ ከእ​ና​ንተ ብቻ በቀር ሌላ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በመ​ስ​ጠ​ትም ቢሆን፥ በመ​ቀ​በል ከእኔ ጋር እን​ዳ​ል​ተ​ባ​በሩ እና​ንተ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። 16#የሐዋ. 17፥1። በተ​ሰ​ሎ​ን​ቄም ሳለሁ ደግሞ፥ አንድ ጊዜና ሁለት ጊዜ ለች​ግሬ ላካ​ች​ሁ​ልኝ። 17ይህ​ንም የማ​ነ​ሣ​ሣው ስጦ​ታ​ች​ሁን ፈልጌ አይ​ደ​ለም፤ በእ​ና​ንተ ላይ የጽ​ድቅ ፍሬ ይበዛ ዘንድ ፈልጌ ነው እንጂ። 18#ዘፀ. 29፥18። ነገር ግን ሁሉ አለኝ፤ ይበ​ዛ​ል​ኝ​ማል፤ የመ​ዓዛ ሽታና የተ​ወ​ደደ መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን ስጦ​ታ​ች​ሁን ከአ​ፍ​ሮ​ዲጡ ተቀ​ብዬ አሟ​ል​ቻ​ለሁ። 19ፈጣ​ሪዬ እንደ ባለ​ጸ​ግ​ነቱ መጠን፥ በክ​ብር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የም​ት​ሹ​ትን ሁሉ ይፈ​ጽ​ም​ላ​ች​ኋል። 20ለአ​ባ​ታ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ ምስ​ጋና ይሁን አሜን። 21በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ቅዱ​ሳ​ንን ሁሉ ሰላም በሉ፤ በእኔ ዘንድ ያሉ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ሰላ​ምታ ያቀ​ር​ቡ​ላ​ች​ኋል። 22ቅዱ​ሳ​ንም ሁሉ፥ ይል​ቁ​ንም ከቄ​ሣር ቤተ ሰብእ የሆኑ ሰላ​ምታ ያቀ​ር​ቡ​ላ​ች​ኋል። 23የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።
በሮሜ ተጽፋ በጢ​ሞ​ቴ​ዎ​ስና በአ​ፍ​ሮ​ዲጡ እጅ ወደ ፊል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች የተ​ላ​ከች መል​እ​ክት ተፈ​ጸ​መች።
ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን አሜን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ