መጽሐፈ ምሳሌ 12
12
1ተግሣጽን የሚወድድ ዕውቀትን ይወድዳል፤
ተግሣጽን የሚጠላ ግን ሰነፍ ነው።
2የተሻለ ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን ያገኛል።
ዐመፀኛ ሰው ግን ቸል ይባላል።
3ከዐመፃ የማይርቅ ሰው ይጠፋል፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሰው በዐመፃ አይበለጽግም” ይላል።
የጻድቃን ሥር ግን አይነቀልም።
4ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት፤
ክፉ ሴት ግን ነቀዝ እንጨትን እንደሚበላ እንዲዚሁ ባሏን ትጐዳለች።
5የጻድቃን አሳብ ቅን ነው፤
ኃጥኣን ግን ሽንገላን ያስተምራሉ።
6የኃጥኣን ምክር ተንኮል ነው።
የቅኖች አፍ ግን ይታደጋቸዋል።
7ኀጢአተኛ በተገለበጠበት ይጠፋል፥
የጻድቃን ቤቶች ግን ጸንተው ይኖራሉ።
8የብልህ ሰው አንደበት በሰው ሁሉ ዘንድ ይመሰገናል፤
ልበ ጠማማ የሆነ ሰው ግን ይናቃል።
9ለራሱ ባሪያ ሆኖ የተጠቃ ሰው
እንጀራ ጐድሎት ራሱን ካከበረው ሰው ይሻላል።
10ጻድቅ ሰው ለእንስሳው ነፍስ ይራራል፤
የኃጥኣን ምሕረት ግን አለመመጽወት ነው።
11ምድሩን የሚያርሳት ሰው እንጀራን ይጠግባል፤
ቦዘኔነትን የሚከተል ግን የአእምሮ ድህነትን ይሰበስባል።
በወይን ግብዣ ራሱን ደስ የሚያሰኝ ሰው#በዕብራይስጥ የለም።
በሰውነቱ ውርደትን ያመጣል።
12የኃጥኣን ምኞት ክፋት ናት።
የጻድቃን ሥር ግን የጸና ነው።
13ኀጢአተኛ ሰው በከንፈሩ ኀጢአት ወደ ወጥመድ ይወድቃል፤
ጻድቅ ግን ከእርሱ ያመልጣል።
አስፍቶ የሚመለከት ሰው ብዙ ምሕረትን ያገኛል።
ድንገት በበር የሚገናኝ ግን ነፍሳትን ያስጨንቃል።
14የሰው ነፍስ ከአፉ ፍሬ መልካም ነገርን ትጠግባለች፥
ሰውም የከንፈሩን ዋጋ ይቀበላል።
15የሰነፎች መንገድ በፊታቸው የቀናች ናት፤
ጠቢብ ግን ምክርን ይሰማል።
16ሰነፍ ቍጣውን በየቀኑ ይናገራል፤
ብልህ ሰው ግን ነውርን ይሰውራል።
17ጻድቅ ሰው የተገለጠ እውነትን ያስተምራል፤
የክፉዎች ምስክርነት ግን ውሸት ነው።
18በሐሰት የሚመሰክሩ በሰይፍ ይገድላሉ፤
በአፋቸው ሰይፍ አለና።#ግሪክ ሰባ. ሊ. ከግእዙ ይለያል።
የጠቢባን ምላስ ግን የቈሰለውን ይፈውሳል።
19የጻድቃን ከንፈሮች ምስክርነትን ያቀናሉ፥
የሚቸኩል ምስክር ግን ክፉ አንደበት አለው።
20ክፉን በሚያስብ ልብ ውስጥ ማታለል አለ፤
ሰላምን የሚወዱ ግን ደስ ይላቸዋል፥
21ጻድቅን ምንም ክፉ ነገር ደስ አያሰኘውም፤
ክፉዎች ግን ክፋትን የተሞሉ ናቸው።
22ሐሰተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤
እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው።
23ብልህ ሰው የጥበብ መንበር ነው፤
የሰነፎች ልብ ግን መርገምን ያገኛል።
24የተመረጡ ሰዎች እጅ ፈጥኖ ይገዛል፤
ሐሰተኞች ሰዎች ግን ለምርኮ ይሆናሉ።
25የሚያስደነግጥ ቃል የጻድቅ ሰው ልቡናን ያውካል፤
መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል።
26ራሱን የሚያውቅ ሰው ለራሱ ጻድቅ ነው፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ወዳጅ” ይላል።
የክፉዎች ሥራ ግን መልካም አይደለም።
የሚበድሉ ሰዎችን ክፉ ይከተላቸዋል፥
የኃጥኣን መንገዳቸውም ታስታቸዋለች።
27ታካች ሰው አድኖ አይዝም።
ንጹሕ ሰው ግን ክቡር ሀብት ነው።
28በጽድቅ መንገድ ሕይወት አለ፥
ክፉን የሚያስቡ ሰዎች መንገዶች ግን ወደ ሞት ያወርዳሉ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 12: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ