መጽሐፈ ምሳሌ 13
13
1ዐዋቂ ልጅ የአባቱን ተግሣጽ ይሰማል፤
የማይሰማ ልጅ ግን ይጠፋል።
2ደግ ሰው ከጽድቅ ፍሬ መልካምን ይበላል፤
የዐመፀኞች ነፍሳት ግን በጨርቋነታቸው ይጠፋሉ።
3አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤
በከንፈሩ የሚቸኩል ግን ራሱን ይጥላል።
4የማይሠራ ሁሉ በምኞት ይኖራል።
የደጋጎች እጅ ግን ይተጋል።
5ጻድቅ የሐሰትን ቃል ይጠላል፤
ኀጢአተኛ ግን ያፍራል፥ ተገልጦም አይመጣም።
6መንገዳቸው ቀና የሆነውን የዋሃንን ጽድቅ ትጠብቃቸዋለች፤
ኀጢአተኞችን ግን ኀጢአታቸው በደለኛ ታደርጋቸዋለች።
7ምንም ሳይኖራቸው ራሳቸውን ባለጠጎች የሚያደርጉ አሉ፥
ባለጠግነታቸው ብዙ ሲሆን ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉም አሉ።
8ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፤
ድሃ ግን ቍጣን አይቃወምም።
9ለጻድቃን ሁልጊዜ ብርሃን ነው፤
የኃጥኣን መብራት ግን ትጠፋለች።
የሐሰተኞች ነፍሳት በኀጢአት ይስታሉ።
ጻድቃን ግን ይራራሉ፥ ይመጸውታሉም።
10ክፉ ሰው ከመሳደብ ጋር ክፋትን ይሠራል፤
ራሳቸውን የሚያውቁ ግን ብልሆች ናቸው።
11በኀጢአት በችኮላ የሚገኝ ሀብት ይጐድላል፥
በእውነት ለራሱ የሚሰበስብ ግን ይበዛለታል።
ጻድቅ ይራራል፥ ያበድራልም።
12ከሚበለጽግና በተስፋ ከሚቈይ ሰውነቱን ሊረዳ የሚጀምር ይሻላል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከልብ ሊረዳ የሚጀምር ተስፋ ከሚሰጥና ሌላውን ወደ ተስፋ ከሚመራ ይሻላል” ይላል።
መልካም ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ናት።
13የእግዚአብሔርን ሥራ የሚያቃልለውን እርሱ ያቃልለዋል፥
ትእዛዙን የሚሰማ ግን በእርሱ በሕይወት ይኖራል።
ለውሸተኛ ልጅ ምንም ደግነት የለም፥
ለብልህ አገልጋይ ግን ሥራው መልካም ይሆናል።
መንገዱም ይቃናል።
14የብልህ ሰው ሕግ የሕይወት ምንጭ ነው።
ማስተዋል የሌለው ግን በኀጢአት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በወጥመድ” ይላል። ይሞታል።
15መልካም ዕውቀት ሞገስንና ጥበብን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሕግን ማወቅ መልካም ማስተዋል ነው” ይላል። ይሰጣል፤
የቸለልተኞች መንገድ ግን በጥፋት ውስጥ ነው።
16ብልህ ሁሉ በዕውቀት ይሠራል፤
ሰነፍ ግን ክፋቱን ይገልጣል።
17ሰነፍ መልእክተኛ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ክፉ ንጉሥ” ይላል። በክፉ ላይ ይወድቃል፤
ብልህ መልእክተኛ ግን ራሱን ያድናል።
18ትምህርት ድህነትንና ጕስቍልናን ያስወግዳል፤
ተግሣጽን የሚጠብቅ ግን ይከብራል።
19የደጋግ ሰዎች ምኞት ነፍስን ያድናል፤
የሰነፎች ሥራ ግን ከዕውቀት የራቀ ነው።
20ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤
ከአላዋቂዎች ጋር የሚሄድ ግን አላዋቂ ይሆናል።
21በደለኞችን ክፉ ነገር ይከተላቸዋል፤
ጻድቃንን ግን መልካም ነገር ያገኛቸዋል።
22ደግ ሰው ለልጅ ልጅ ያወርሳል፥
የኀጢአተኞች ብልጽግና ግን ለጻድቃን ይደልባል።
23ጻድቃን ለብዙ ዓመት በብልጽግና ይኖራሉ፤
ዐመፀኞች ግን ፈጥነው ይጠፋሉ።
24በበትር ከመምታት የሚራራ ሰው ልጁን ይጠላል፤
ልጁን የሚወድድ ግን በጥንቃቄ ይቀጣዋል።
25ጻድቅ ሰውነቱ እስክትጠግብ ድረስ ይበላል፤
የኃጥኣን ሰውነት ግን ትቸገራለች።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 13: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ምሳሌ 13
13
1ዐዋቂ ልጅ የአባቱን ተግሣጽ ይሰማል፤
የማይሰማ ልጅ ግን ይጠፋል።
2ደግ ሰው ከጽድቅ ፍሬ መልካምን ይበላል፤
የዐመፀኞች ነፍሳት ግን በጨርቋነታቸው ይጠፋሉ።
3አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤
በከንፈሩ የሚቸኩል ግን ራሱን ይጥላል።
4የማይሠራ ሁሉ በምኞት ይኖራል።
የደጋጎች እጅ ግን ይተጋል።
5ጻድቅ የሐሰትን ቃል ይጠላል፤
ኀጢአተኛ ግን ያፍራል፥ ተገልጦም አይመጣም።
6መንገዳቸው ቀና የሆነውን የዋሃንን ጽድቅ ትጠብቃቸዋለች፤
ኀጢአተኞችን ግን ኀጢአታቸው በደለኛ ታደርጋቸዋለች።
7ምንም ሳይኖራቸው ራሳቸውን ባለጠጎች የሚያደርጉ አሉ፥
ባለጠግነታቸው ብዙ ሲሆን ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉም አሉ።
8ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፤
ድሃ ግን ቍጣን አይቃወምም።
9ለጻድቃን ሁልጊዜ ብርሃን ነው፤
የኃጥኣን መብራት ግን ትጠፋለች።
የሐሰተኞች ነፍሳት በኀጢአት ይስታሉ።
ጻድቃን ግን ይራራሉ፥ ይመጸውታሉም።
10ክፉ ሰው ከመሳደብ ጋር ክፋትን ይሠራል፤
ራሳቸውን የሚያውቁ ግን ብልሆች ናቸው።
11በኀጢአት በችኮላ የሚገኝ ሀብት ይጐድላል፥
በእውነት ለራሱ የሚሰበስብ ግን ይበዛለታል።
ጻድቅ ይራራል፥ ያበድራልም።
12ከሚበለጽግና በተስፋ ከሚቈይ ሰውነቱን ሊረዳ የሚጀምር ይሻላል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከልብ ሊረዳ የሚጀምር ተስፋ ከሚሰጥና ሌላውን ወደ ተስፋ ከሚመራ ይሻላል” ይላል።
መልካም ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ናት።
13የእግዚአብሔርን ሥራ የሚያቃልለውን እርሱ ያቃልለዋል፥
ትእዛዙን የሚሰማ ግን በእርሱ በሕይወት ይኖራል።
ለውሸተኛ ልጅ ምንም ደግነት የለም፥
ለብልህ አገልጋይ ግን ሥራው መልካም ይሆናል።
መንገዱም ይቃናል።
14የብልህ ሰው ሕግ የሕይወት ምንጭ ነው።
ማስተዋል የሌለው ግን በኀጢአት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በወጥመድ” ይላል። ይሞታል።
15መልካም ዕውቀት ሞገስንና ጥበብን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሕግን ማወቅ መልካም ማስተዋል ነው” ይላል። ይሰጣል፤
የቸለልተኞች መንገድ ግን በጥፋት ውስጥ ነው።
16ብልህ ሁሉ በዕውቀት ይሠራል፤
ሰነፍ ግን ክፋቱን ይገልጣል።
17ሰነፍ መልእክተኛ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ክፉ ንጉሥ” ይላል። በክፉ ላይ ይወድቃል፤
ብልህ መልእክተኛ ግን ራሱን ያድናል።
18ትምህርት ድህነትንና ጕስቍልናን ያስወግዳል፤
ተግሣጽን የሚጠብቅ ግን ይከብራል።
19የደጋግ ሰዎች ምኞት ነፍስን ያድናል፤
የሰነፎች ሥራ ግን ከዕውቀት የራቀ ነው።
20ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤
ከአላዋቂዎች ጋር የሚሄድ ግን አላዋቂ ይሆናል።
21በደለኞችን ክፉ ነገር ይከተላቸዋል፤
ጻድቃንን ግን መልካም ነገር ያገኛቸዋል።
22ደግ ሰው ለልጅ ልጅ ያወርሳል፥
የኀጢአተኞች ብልጽግና ግን ለጻድቃን ይደልባል።
23ጻድቃን ለብዙ ዓመት በብልጽግና ይኖራሉ፤
ዐመፀኞች ግን ፈጥነው ይጠፋሉ።
24በበትር ከመምታት የሚራራ ሰው ልጁን ይጠላል፤
ልጁን የሚወድድ ግን በጥንቃቄ ይቀጣዋል።
25ጻድቅ ሰውነቱ እስክትጠግብ ድረስ ይበላል፤
የኃጥኣን ሰውነት ግን ትቸገራለች።