መጽሐፈ ምሳሌ 18
18
1ከወዳጆቹ መለየትን የሚወድድ ሰው ምክንያትን ይፈልጋል፥
ሁልጊዜም ለሽሙጥ ይሆናል።
2የዕውቀት ድሃ ጥበብን አይወድድም፤
ነገር ግን ስንፍና ይገዛዋል።
3ኀጢአተኛ ወደ ጥፋት ጥልቅ በመጣ ጊዜ ቸል ይላል፥
ውርደትና ሽሙጥም በላዩ ይመጣል።
4ቃል በብልህ ሰው ልብ ውስጥ የጠለቀ ውኃ ነው፥
የሚፈልቅም የሕይወት ምንጭና ፈሳሽ ወንዝ ነው።
5የኃጥኣንን ፊት ማድነቅ መልካም አይደለም።
በፍርድ ጊዜም እውነትን ማራቅ መልካም አይደለም፥
6አላዋቂን ከንፈሮቹ ወደ ክፉ ያደርሱታል፥
የችኩል አፍም ሞትን ይጠራል።
7የአላዋቂ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥
ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው።
8ፍርሀት ሰነፎችን ይጥላል፥
የተቸገሩ ሰዎች ሰውነትም ይራባል።
9በሥራው ራሱን የማያድን፥
ራሱን ለሚያጠፋ ወንድም ነው።
10የእግዚአብሔር ስም ታላቅ ኀይል ነው፤
ጻድቃንም እርሱን በመከተል ከፍ ከፍ ይላሉ።
11የባለጠጋ ሰው ሀብቱ የጸናች ከተማ ናት፥
ክብሯም እንደ ትልቅ ጥላ ታጠላለች።
12ከመውደቅ በፊት የሰው ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥
ሳይከብርም ይዋረዳል።
13ሳይሰማ ነገርን የሚመልስ
ስንፍናና እፍረት ይሆንበታል።
14ብልህ አገልጋይ የጌታውን ቍጣ ያበርዳል፥
አእምሮ የጐደለውን ሰው ማን ይችለዋል?
15የብልህ ልብ ዕውቀትን ገንዘብ ያደርጋል፥
የጠቢባን ጆሮም ዕውቀትን ትፈልጋለች።
16ሀብት ሰውን ከፍ ከፍ ያደርጋል፥
ከመኳንንት ጋርም ያኖረዋል።
17ከፍርድ በፊት ራሱን የሚከስስ ጻድቅ ነው፥
ያመጣው ባላጋራውም ይገሠጻል።
18ዕጣ ክርክርን ያስተዋል፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዝምተኛ ክርክርን ያስተዋል” ይላል።
በኀያላንም መካከል ይለያል።
19ወንድሙን የሚረዳ ወንድም እንደ ጸናችና ከፍ እንዳለች ከተማ ነው።
በጽኑ መሠረትም እንደ ታነጸ ሕንጻ የጸና ነው።
20ሰው ሆዱን ከአፉ ፍሬ ይሞላል፥
ከከንፈሩም ፍሬ ይጠግባል።
21ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤
የሚያጸኑአትም ፍሬዋን ይበላሉ።
22ደግ ሚስትን ያገኘ ሞገስን አገኘ፥
ከእግዚአብሔርም ደስታን ተቀበለ።
ደግ ሴትን የፈታ ደስታን አጣ፥
አመንዝራዪቱንም የሚያኖር አላዋቂና ኀጢአተኛ ነው።#ዕብ. ምዕ. 18 ላይ 23 እና 24 ቍጥር ይጨምራል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 18: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ምሳሌ 18
18
1ከወዳጆቹ መለየትን የሚወድድ ሰው ምክንያትን ይፈልጋል፥
ሁልጊዜም ለሽሙጥ ይሆናል።
2የዕውቀት ድሃ ጥበብን አይወድድም፤
ነገር ግን ስንፍና ይገዛዋል።
3ኀጢአተኛ ወደ ጥፋት ጥልቅ በመጣ ጊዜ ቸል ይላል፥
ውርደትና ሽሙጥም በላዩ ይመጣል።
4ቃል በብልህ ሰው ልብ ውስጥ የጠለቀ ውኃ ነው፥
የሚፈልቅም የሕይወት ምንጭና ፈሳሽ ወንዝ ነው።
5የኃጥኣንን ፊት ማድነቅ መልካም አይደለም።
በፍርድ ጊዜም እውነትን ማራቅ መልካም አይደለም፥
6አላዋቂን ከንፈሮቹ ወደ ክፉ ያደርሱታል፥
የችኩል አፍም ሞትን ይጠራል።
7የአላዋቂ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥
ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው።
8ፍርሀት ሰነፎችን ይጥላል፥
የተቸገሩ ሰዎች ሰውነትም ይራባል።
9በሥራው ራሱን የማያድን፥
ራሱን ለሚያጠፋ ወንድም ነው።
10የእግዚአብሔር ስም ታላቅ ኀይል ነው፤
ጻድቃንም እርሱን በመከተል ከፍ ከፍ ይላሉ።
11የባለጠጋ ሰው ሀብቱ የጸናች ከተማ ናት፥
ክብሯም እንደ ትልቅ ጥላ ታጠላለች።
12ከመውደቅ በፊት የሰው ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥
ሳይከብርም ይዋረዳል።
13ሳይሰማ ነገርን የሚመልስ
ስንፍናና እፍረት ይሆንበታል።
14ብልህ አገልጋይ የጌታውን ቍጣ ያበርዳል፥
አእምሮ የጐደለውን ሰው ማን ይችለዋል?
15የብልህ ልብ ዕውቀትን ገንዘብ ያደርጋል፥
የጠቢባን ጆሮም ዕውቀትን ትፈልጋለች።
16ሀብት ሰውን ከፍ ከፍ ያደርጋል፥
ከመኳንንት ጋርም ያኖረዋል።
17ከፍርድ በፊት ራሱን የሚከስስ ጻድቅ ነው፥
ያመጣው ባላጋራውም ይገሠጻል።
18ዕጣ ክርክርን ያስተዋል፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዝምተኛ ክርክርን ያስተዋል” ይላል።
በኀያላንም መካከል ይለያል።
19ወንድሙን የሚረዳ ወንድም እንደ ጸናችና ከፍ እንዳለች ከተማ ነው።
በጽኑ መሠረትም እንደ ታነጸ ሕንጻ የጸና ነው።
20ሰው ሆዱን ከአፉ ፍሬ ይሞላል፥
ከከንፈሩም ፍሬ ይጠግባል።
21ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤
የሚያጸኑአትም ፍሬዋን ይበላሉ።
22ደግ ሚስትን ያገኘ ሞገስን አገኘ፥
ከእግዚአብሔርም ደስታን ተቀበለ።
ደግ ሴትን የፈታ ደስታን አጣ፥
አመንዝራዪቱንም የሚያኖር አላዋቂና ኀጢአተኛ ነው።#ዕብ. ምዕ. 18 ላይ 23 እና 24 ቍጥር ይጨምራል።