መዝሙረ ዳዊት 1
1
የጻድቃንና የኃጥኣን ትርጓሜ
1ምስጉን ነው፥ በዝንጉዎች ምክር ያልሄደ፥
በኀጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥
በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ ሰው።
2የእግዚአብሔር ሕግ ብቻ ፈቃዱ የሆነ፥
ሕጉንም በቀንና በሌሊት የሚያስብ፥
3እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥
ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥
ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤
የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
4ኃጥኣን እንዲህ አይደሉም፥ እንዲህ አይደሉም።
ነገር ግን ነፋስ ከገጸ ምድር ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ ናቸው።
5ስለዚህ ዝንጉዎች በፍርድ፥
ኃጥኣንም በጻድቃን ምክር አይቆሙም።
6እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፥
የኃጥኣን መንገድ ግን ትጠፋለች።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 1: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ