የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 11

11
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ ስለ ስም​ን​ተኛ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አቤቱ፥ አድ​ነኝ፥ ደግ ሰው አል​ቆ​አ​ልና፥
ከሰው ልጆ​ችም መተ​ማ​መን ጐድ​ሎ​አ​ልና።
2እርስ በር​ሳ​ቸው ከንቱ ነገ​ርን ይና​ገ​ራሉ፤
በሽ​ን​ገላ ከን​ፈር ሁለት ልብ ሆነው ይና​ገ​ራሉ።
3የሽ​ን​ገ​ላን ከን​ፈ​ሮች ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፥
ታላቅ ነገ​ርን የም​ት​ና​ገ​ረ​ው​ንም ምላስ፤
4“ምላ​ሳ​ች​ንን እና​በ​ረ​ታ​ለን፤
ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ችን የእኛ ናቸው፥ ጌታ​ችን ማን ነው?” የሚ​ሉ​ትን።
5“ስለ ድሆች መከራ፥ ስለ እስ​ረ​ኞ​ችም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ችግ​ረ​ኞች” ይላል። ጩኸት
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይላል፥ አሁን እነ​ሣ​ለሁ፤
መድ​ኀ​ኒ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ፥ በእ​ር​ሱም እገ​ል​ጣ​ለሁ።”
6በም​ድር ላይ እንደ ተፈ​ተነ፥ ሰባት ጊዜም እንደ ተጣራ ብር
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ንጹሕ ቃል ነው።
7አቤቱ፥ አንተ ጠብ​ቀን፥
ከዚ​ህ​ችም ትው​ልድ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታደ​ገን።
8ዝን​ጉ​ዎች በዙ​ሪ​ያው ይመ​ላ​ለ​ሳሉ።
እንደ ገና​ና​ነ​ትህ መጠን የሰው ልጆ​ችን አጸ​ና​ሃ​ቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ