የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 13

13
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1ሰነፍ በልቡ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አም​ላክ” ይላል። የለም” ይላል።
በሥ​ራ​ቸው ረከሱ፥ ጐሰ​ቈ​ሉም፤
በጎ ነገ​ርን የሚ​ሠ​ራት የለም። አን​ድም እንኳ የለም።
2የሚ​ያ​ስ​ተ​ውል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ፈ​ልግ እን​ዳለ ያይ ዘንድ
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ የሰው ልጆ​ችን ተመ​ለ​ከተ።
3ሁሉ ተስ​ተ​ካ​ክሎ በአ​ን​ድ​ነት ዐመፀ፤
በጎ ነገ​ርን የሚ​ሠ​ራት የለም፤ አን​ድም እንኳ የለም።
4ጕሮ​ሮ​ኣ​ቸው እንደ መቃ​ብር የተ​ከ​ፈተ ነው፥#መዝ. 13 ከቍ. 4 እስከ 6 ያለው በዕብ. የለም።
በም​ላ​ሳ​ቸው ሸነ​ገሉ፤
5ከከ​ን​ፈ​ራ​ቸው በታች የእ​ባብ መርዝ አለ፤
አፋ​ቸው መራራ ነው፥ መር​ገ​ም​ንም ተሞ​ል​ቶ​አል፤
6ደምን ለማ​ፍ​ሰስ እግ​ራ​ቸው ፈጣን ነው፤
ጥፋ​ትና ጕስ​ቍ​ልና በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው አለ፥
የሰ​ላ​ምን መን​ገድ አላ​ወ​ቁ​አ​ት​ምና፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት በዐ​ይ​ና​ቸው ፊት የለም።
7ሕዝ​ቤን እንደ እን​ጀራ የሚ​በሉ፥
ኀጢ​አ​ትን የሚ​ሠሩ ሁሉ አያ​ው​ቁም።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አይ​ጠ​ሩ​ትም።
8በዚ​ያም ፈሩ፥ የማ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ውም አስ​ፈ​ራ​ቸው።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጻ​ድ​ቃን ትው​ልድ ዘንድ ነውና።
9የድ​ሆ​ችን ምክር አሳ​ፈ​ራ​ችሁ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ተስ​ፋ​ቸው ነው።
10ከጽ​ዮን መድ​ኀ​ኒ​ትን ለእ​ስ​ራ​ኤል ማን ይሰ​ጣል?
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሕ​ዝ​ቡን ምርኮ በመ​ለሰ ጊዜ፥
ያዕ​ቆብ ደስ ይለ​ዋል፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋል።#በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. መዝ. 13 ቍ. 7 ላይ ያበ​ቃል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ