መዝሙረ ዳዊት 143
143
ስለ ጎልያድ የዳዊት መዝሙር።
1ለእጆቼ ጠብን፥ ለጣቶቼም ሰልፍን
ያስተማራቸው አምላኬ እግዚአብሔር ይመስገን፤
2የሚምረኝ፥ መሸሸጊያዬ፥ መጠጊያዬና አዳኜ፤
መታመኛዬም፤ እርሱን ታመንሁ፤
ሕዝቡንም#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ሕዝቤን” ይላል። ከእኔ በታች የሚያስገዛልኝ።
3አቤቱ፥ ለእርሱ ትገለጥለት ዘንድ ሰው ምንድን ነው?
ታስበው ዘንድስ የሰው ልጅ ምንድን ነው?
4ሰው ከንቱ ነገርን ይመስላል፤
ዘመኑም እንደ ጥላ ያልፋል።
5አቤቱ፥ ሰማዮችህን ዝቅ ዝቅ አድርጋቸው፥ ውረድም፤
ተራሮችን ዳስሳቸው፥ ይጢሱም።
6መብረቆችህን ብልጭ አድርጋቸው፥ በትናቸውም፤
ፍላጾችህን ላካቸው፥ አስደንግጣቸውም።
7እጅህን ከአርያም ላክ፥
ከብዙ ውኃም አድነኝ፤
ከባዕድ ልጆችም እጅ፥
8አፋቸው ከንቱ ነገርን ከሚናገር፥
ቀኛቸውም የዐመፃ ቀኝ ከሆነ አስጥለኝ።
9አቤቱ፥ በአዲስ ምስጋና አመሰግንሃለሁ፤
ዐሥር አውታር ባለው በገናም እዘምርልሃለሁ።
10ለነገሥታት መድኀኒትን የሚሰጥ፥
ባሪያው ዳዊትን ከክፉ ጦር የሚያድነው እርሱ ነው።
11አፋቸውም ከንቱ ነገርን ከሚናገር፥
ቀኛቸውም የዐመፃ ቀኝ ከሆነ፥
ከባዕድ ልጆች እጅ አድነኝ፥ አስጥለኝም።
12ልጆቻቸው በጐልማስነታቸው እንደ አዲስ ተክል#ግእዝ “ተክለ ዘይት” ይላል። የሆኑ፥
ሴቶች ልጆቻቸውም እንደ እልፍኝ ያማሩና ያጌጡ፤
13ዕቃ ቤቶቻቸውም በያይነቱ ዕቃ የተሞሉ ናቸው፥
በጎቻቸውም ብዙ የሚወልዱ፥
በመሰማርያቸውም የሚበዙ፥
14ላሞቻቸውም የሰቡ፤
ለቅጥራቸውም መፍረስ የሌለው፥
የሚገባባቸውም የሌለ፥
በአደባባዮቻቸውም ዋይታ የሌለባቸው፤
15እንደዚህ ያለውን ሕዝብ አመስግኑት፤
እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ ብፁዕ ነው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 143: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 143
143
ስለ ጎልያድ የዳዊት መዝሙር።
1ለእጆቼ ጠብን፥ ለጣቶቼም ሰልፍን
ያስተማራቸው አምላኬ እግዚአብሔር ይመስገን፤
2የሚምረኝ፥ መሸሸጊያዬ፥ መጠጊያዬና አዳኜ፤
መታመኛዬም፤ እርሱን ታመንሁ፤
ሕዝቡንም#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ሕዝቤን” ይላል። ከእኔ በታች የሚያስገዛልኝ።
3አቤቱ፥ ለእርሱ ትገለጥለት ዘንድ ሰው ምንድን ነው?
ታስበው ዘንድስ የሰው ልጅ ምንድን ነው?
4ሰው ከንቱ ነገርን ይመስላል፤
ዘመኑም እንደ ጥላ ያልፋል።
5አቤቱ፥ ሰማዮችህን ዝቅ ዝቅ አድርጋቸው፥ ውረድም፤
ተራሮችን ዳስሳቸው፥ ይጢሱም።
6መብረቆችህን ብልጭ አድርጋቸው፥ በትናቸውም፤
ፍላጾችህን ላካቸው፥ አስደንግጣቸውም።
7እጅህን ከአርያም ላክ፥
ከብዙ ውኃም አድነኝ፤
ከባዕድ ልጆችም እጅ፥
8አፋቸው ከንቱ ነገርን ከሚናገር፥
ቀኛቸውም የዐመፃ ቀኝ ከሆነ አስጥለኝ።
9አቤቱ፥ በአዲስ ምስጋና አመሰግንሃለሁ፤
ዐሥር አውታር ባለው በገናም እዘምርልሃለሁ።
10ለነገሥታት መድኀኒትን የሚሰጥ፥
ባሪያው ዳዊትን ከክፉ ጦር የሚያድነው እርሱ ነው።
11አፋቸውም ከንቱ ነገርን ከሚናገር፥
ቀኛቸውም የዐመፃ ቀኝ ከሆነ፥
ከባዕድ ልጆች እጅ አድነኝ፥ አስጥለኝም።
12ልጆቻቸው በጐልማስነታቸው እንደ አዲስ ተክል#ግእዝ “ተክለ ዘይት” ይላል። የሆኑ፥
ሴቶች ልጆቻቸውም እንደ እልፍኝ ያማሩና ያጌጡ፤
13ዕቃ ቤቶቻቸውም በያይነቱ ዕቃ የተሞሉ ናቸው፥
በጎቻቸውም ብዙ የሚወልዱ፥
በመሰማርያቸውም የሚበዙ፥
14ላሞቻቸውም የሰቡ፤
ለቅጥራቸውም መፍረስ የሌለው፥
የሚገባባቸውም የሌለ፥
በአደባባዮቻቸውም ዋይታ የሌለባቸው፤
15እንደዚህ ያለውን ሕዝብ አመስግኑት፤
እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ ብፁዕ ነው።