መዝሙረ ዳዊት 20
20
ለመዘምራን አለቃ የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ በኀይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል፤
በማዳንህም እጅግ ሐሤትን ያደርጋል።
2የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው፥
የከንፈሮቹንም ልመና አልከለከልኸውም።
3በበጎ በረከት ደርሰህለታልና፤
ከክቡር ዕንቍ የሆነ ዘውድንም በራሱ ላይ አኖርህ።
4ሕይወትን ለመነህ፥ ሰጠኸውም፥
ለረዥም ዘመን ለዘለዓለሙ።
5በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው፤
ክብርንና ምስጋናን ጨመርህለት።
6የዘለዓለም በረከትን ሰጥተኸዋልና፥
በፊትህም ደስታ ደስ ታሰኘዋለህ።
7ንጉሥ በእግዚአብሔር ተማምኖአልና፥
በልዑልም ምሕረት አይናወጥም።
8እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ታግኛቸው፥
ቀኝህም የሚጠሉህን ሁሉ ታግኛቸው።
9ፊትህ በተቈጣ ጊዜ እንደ እሳት እቶን አድርጋቸው፤
አቤቱ፥ በቍጣህ አውካቸው፥ እሳትም ትብላቸው።
10ፍሬያቸውን ከምድር፥
ዘራቸውንም ከሰው ልጆች አጥፋ።
11ክፋትን በአንተ ላይ ዘርግተዋልና፥
መወሰን የማይቻላቸውንም ምክር ዐሰቡ።
12ወደ ኋላቸው ትመልሳቸዋለህ፤
ፊታቸውን ለመዓትህ ጊዜ#ዕብ. “ፍላጻን በፊታቸው ላይ..” ይላል። ታዘጋጃለህ።
13አቤቱ፥ በኀይልህ ከፍ ከፍ አልህ፤
ጽናትህንም እናመሰግናለን፤ እንዘምርማለን።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 20: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 20
20
ለመዘምራን አለቃ የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ በኀይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል፤
በማዳንህም እጅግ ሐሤትን ያደርጋል።
2የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው፥
የከንፈሮቹንም ልመና አልከለከልኸውም።
3በበጎ በረከት ደርሰህለታልና፤
ከክቡር ዕንቍ የሆነ ዘውድንም በራሱ ላይ አኖርህ።
4ሕይወትን ለመነህ፥ ሰጠኸውም፥
ለረዥም ዘመን ለዘለዓለሙ።
5በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው፤
ክብርንና ምስጋናን ጨመርህለት።
6የዘለዓለም በረከትን ሰጥተኸዋልና፥
በፊትህም ደስታ ደስ ታሰኘዋለህ።
7ንጉሥ በእግዚአብሔር ተማምኖአልና፥
በልዑልም ምሕረት አይናወጥም።
8እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ታግኛቸው፥
ቀኝህም የሚጠሉህን ሁሉ ታግኛቸው።
9ፊትህ በተቈጣ ጊዜ እንደ እሳት እቶን አድርጋቸው፤
አቤቱ፥ በቍጣህ አውካቸው፥ እሳትም ትብላቸው።
10ፍሬያቸውን ከምድር፥
ዘራቸውንም ከሰው ልጆች አጥፋ።
11ክፋትን በአንተ ላይ ዘርግተዋልና፥
መወሰን የማይቻላቸውንም ምክር ዐሰቡ።
12ወደ ኋላቸው ትመልሳቸዋለህ፤
ፊታቸውን ለመዓትህ ጊዜ#ዕብ. “ፍላጻን በፊታቸው ላይ..” ይላል። ታዘጋጃለህ።
13አቤቱ፥ በኀይልህ ከፍ ከፍ አልህ፤
ጽናትህንም እናመሰግናለን፤ እንዘምርማለን።