የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 21

21
ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ ስለ ንጋት ኀይል የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1አም​ላኬ፥ አም​ላኬ፥ ተመ​ል​ከ​ተኝ፥ ለምን ተው​ኸኝ?
የኀ​ጢ​አቴ ቃል እኔን ከማ​ዳን የራቀ ነው።#ዕብ. “እኔን ከማ​ዳ​ንና ከጩ​ኸቴ ቃል የራ​ቅህ ነህ” ይላል።
2አም​ላኬ፥ በቀን ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለሁ፥ አል​ሰ​ማ​ኸ​ኝም።
በሌ​ሊ​ትም በፊ​ትህ አላ​ሰ​ብ​ከ​ኝም።
3በእ​ስ​ራ​ኤል የተ​መ​ሰ​ገ​ንህ አንተ ግን በቅ​ዱ​ሳ​ንህ ትኖ​ራ​ለህ።
4አባ​ቶ​ቻ​ችን አን​ተን አመኑ፥
አመኑ፥ አን​ተም አዳ​ን​ሃ​ቸው።
5ወደ አንተ ጮኹ፥ ዳኑም፥
አን​ተ​ንም አመኑ፥ አላ​ፈ​ሩም።
6እኔ ግን ትል ነኝ፥ ሰውም አይ​ደ​ለ​ሁም፤
በሰው ዘንድ የተ​ና​ቅሁ፥ በሕ​ዝ​ብም ዘንድ የተ​ዋ​ረ​ድሁ ነኝ።
7የሚ​ያ​ዩኝ ሁሉ ይጠ​ቃ​ቀ​ሱ​ብ​ኛል፤
ራሳ​ቸ​ውን እየ​ነ​ቀ​ነቁ በከ​ን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸው እን​ዲህ ይላሉ፦
8“በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አመነ፥
እር​ሱ​ንም ያድ​ነው፤ ከወ​ደ​ደው ያድ​ነው።”
9አንተ ከሆድ አው​ጥ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥
በእ​ናቴ ጡት ሳለ​ሁም በአ​ንተ ታመ​ንሁ።
10ከማ​ኅ​ፀን ጀምሮ በአ​ንተ ላይ ተጣ​ልሁ፤
ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ጀም​ረህ አንተ አም​ላኬ ነህ።
11ልጨ​ነቅ ቀር​ቤ​አ​ለ​ሁና፥
የሚ​ረ​ዳ​ኝም የለ​ምና ከእኔ አት​ራቅ።
12ብዙ በሬ​ዎች ከበ​ቡኝ፥
የሰ​ቡ​ትም ፍሪ​ዳ​ዎች#ዕብ. “የባ​ሳን በሬ​ዎች” ይላል። ያዙኝ፤
13ለመ​ን​ጠቅ እን​ደ​ሚ​ያ​ሸ​ምቅ አን​በሳ#ዕብ. “እንደ ነጣ​ቂና እን​ደ​ሚ​ጮኽ...” ይላል።
በላዬ አፋ​ቸ​ውን ከፈቱ።
14እንደ ውኃ ፈሰ​ስሁ
አጥ​ን​ቶቼም ሁሉ ተለ​ያዩ፤
ልቤ እንደ ሰም ሆነ፥
በሆ​ዴም መካ​ከል ቀለጠ።
15ኀይሌ እንደ ገል ደረቀ፥
ምላ​ሴም በጕ​ሮ​ሮዬ ተጣጋ፥
ወደ ሞትም አፈር አወ​ረ​ድ​ኸኝ፤
16ብዙ ውሾ​ችም ከበ​ቡኝ፤
የክ​ፉ​ዎች ማኅ​በ​ርም ያዙኝ፤
እጆ​ቼ​ንና እግ​ሮቼን ቸነ​ከ​ሩኝ።
17አጥ​ን​ቶ​ቼን ሁሉ ቈጠሩ፤
እነ​ር​ሱም ዐው​ቀው ቸል አሉኝ።
18ልብ​ሶ​ቼን ለራ​ሳ​ቸው ተከ​ፋ​ፈሉ፥
በቀ​ሚ​ሴም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣሉ።
19አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ከእኔ አት​ራቅ፥
እኔን ለመ​ር​ዳት ተመ​ል​ከት።#ዕብ. “ፍጠን” ይላል።
20ነፍ​ሴን ከሰ​ይፍ አድ​ናት፥
ብቸ​ኝ​ነ​ቴ​ንም ከው​ሾች እጅ።
21ከአ​ን​በሳ አፍ አድ​ነኝ።
ብቸ​ኝ​ነ​ቴ​ንም ከቀ​ን​ዶች አንድ ቀንድ ካለው።
22ስም​ህን ለወ​ን​ድ​ሞቼ እነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፥
በጉ​ባ​ኤም መካ​ከል አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፤
23እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈሩ፥ አመ​ስ​ግ​ኑት፤
የያ​ዕ​ቆብ ዘር ሁላ​ችሁ፥ አክ​ብ​ሩት፥
የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘር ሁላ​ችሁ፥ ፍሩት።
24የድ​ሃ​ውን ልመና አል​ና​ቀ​ምና፥ ቸልም አላ​ለ​ምና፤
ፊቱ​ንም ከእኔ አል​መ​ለ​ሰ​ምና፥
ነገር ግን ወደ እርሱ በጮ​ኽሁ ጊዜ ሰማኝ።
25በታ​ላቅ ጉባኤ ክብሬ#ዕብ. “ምስ​ጋ​ናዬ” ይላል። ከአ​ንተ ዘንድ ነው፤
እር​ሱን በሚ​ፈ​ሩት ፊት ስእ​ለ​ቴን እሰ​ጣ​ለሁ።
26ችግ​ረ​ኞች ይበ​ላሉ፥ ይጠ​ግ​ባ​ሉም፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ሹት ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤
ልባ​ቸ​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕያው ይሆ​ናል።
27የም​ድር ዳር​ቻ​ዎች ሁሉ ያስቡ፥
ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ለሱ፤
የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ዶች ሁሉ በፊቱ ይሰ​ግ​ዳሉ፤
28መን​ግ​ሥት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና፥
እርሱ አሕ​ዛ​ብን ይገ​ዛል።
29የም​ድር ደን​ዳ​ኖች ሁሉ ይበ​ላሉ ይሰ​ግ​ዳ​ሉም፤#ግእዝ “ብልዑ ወስ​ግዱ” ይላል።
ወደ መሬት የሚ​ወ​ር​ዱት ሁሉ በፊቱ ይሰ​ግ​ዳሉ፤
ነፍ​ሴም ስለ እርሱ በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ለች።
30ዘሬም ይገ​ዛ​ለ​ታል፤
የም​ት​መ​ጣው ትው​ልድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትነ​ግ​ረ​ዋ​ለች፤
31ለሚ​ወ​ለ​ደው ሕዝብ
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ረ​ገ​ውን ጽድ​ቁን ይና​ገ​ራሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ