መዝሙረ ዳዊት 28
28
ከድንኳን በመውጣት ጊዜ የዳዊት መዝሙር።
1የአማልክት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የአምላክ ልጆች” ይላል። ልጆች ሆይ፥ ለእግዚአብሔር አምጡ፥
የጊደሮችን ጥጃ ለእግዚአብሔር አምጡ።#“የጊደሮችን ጥጃ ለእግዚአብሔር አምጡ” የሚለው በዕብ. የለም።
ክብርንና ምስጋናን ለእግዚአብሔር አምጡ፥
2የስሙን ክብር ለእግዚአብሔር አምጡ፥
በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
3የእግዚአብሔር ቃል በውኆች ላይ ነው።
የክብር አምላክ አንጐደጐደ፥
እግዚአብሔር በብዙ ውኆች ላይ ነው።
4የእግዚአብሔር ቃል በኀይል ነው፤
የእግዚአብሔር ቃል በታላቅ ክብር ነው።
5የእግዚአብሔር ቃል ዝግባን ይሰብራል፤
እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይቀጠቅጣል።
6እንደ ሊባኖስ ላም ያከሳዋል።#ዕብ. “እንደ ጥጃ ሊባኖስን ያዘልለዋል” ይላል።
ተወዳጅ ግን አንድ ቀንድ እንዳለው ርኤም ልጅ ነው።
7የእግዚአብሔር ቃል የእሳቱን ነበልባል ይቈርጣል።
8የእግዚአብሔር ቃል ምድረ በዳውን ያናውጣል፥
እግዚአብሔር የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል።
9የእግዚአብሔር ቃል ዋሊያዎችን ያጠነክራቸዋል፥
ዛፎችንም ይገልጣል፤ ሁሉም በመቅደሱ፦ ምስጋና ይላል።
10እግዚአብሔር የጥፋት ውኃን ሰብስቦአል፤
እግዚአብሔር ለዘለዓለም ንጉሥ ሆኖ ይቀመጣል።
11እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኀይልን ይሰጣል፤
እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካቸዋል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 28: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 28
28
ከድንኳን በመውጣት ጊዜ የዳዊት መዝሙር።
1የአማልክት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የአምላክ ልጆች” ይላል። ልጆች ሆይ፥ ለእግዚአብሔር አምጡ፥
የጊደሮችን ጥጃ ለእግዚአብሔር አምጡ።#“የጊደሮችን ጥጃ ለእግዚአብሔር አምጡ” የሚለው በዕብ. የለም።
ክብርንና ምስጋናን ለእግዚአብሔር አምጡ፥
2የስሙን ክብር ለእግዚአብሔር አምጡ፥
በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
3የእግዚአብሔር ቃል በውኆች ላይ ነው።
የክብር አምላክ አንጐደጐደ፥
እግዚአብሔር በብዙ ውኆች ላይ ነው።
4የእግዚአብሔር ቃል በኀይል ነው፤
የእግዚአብሔር ቃል በታላቅ ክብር ነው።
5የእግዚአብሔር ቃል ዝግባን ይሰብራል፤
እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይቀጠቅጣል።
6እንደ ሊባኖስ ላም ያከሳዋል።#ዕብ. “እንደ ጥጃ ሊባኖስን ያዘልለዋል” ይላል።
ተወዳጅ ግን አንድ ቀንድ እንዳለው ርኤም ልጅ ነው።
7የእግዚአብሔር ቃል የእሳቱን ነበልባል ይቈርጣል።
8የእግዚአብሔር ቃል ምድረ በዳውን ያናውጣል፥
እግዚአብሔር የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል።
9የእግዚአብሔር ቃል ዋሊያዎችን ያጠነክራቸዋል፥
ዛፎችንም ይገልጣል፤ ሁሉም በመቅደሱ፦ ምስጋና ይላል።
10እግዚአብሔር የጥፋት ውኃን ሰብስቦአል፤
እግዚአብሔር ለዘለዓለም ንጉሥ ሆኖ ይቀመጣል።
11እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኀይልን ይሰጣል፤
እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካቸዋል።