የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 32

32
የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1ጻድ​ቃን ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤
ለቅ​ኖ​ችም ክብር ይገ​ባል።
2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በመ​ሰ​ንቆ አመ​ስ​ግ​ኑት፥
ዐሥር አው​ታ​ርም ባለው በገና ዘም​ሩ​ለት።
3አዲስ ምስ​ጋ​ና​ንም አመ​ስ​ግ​ኑት፥
በእ​ል​ል​ታም መል​ካም ዝማሬ ዘም​ሩ​ለት፤
4የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እው​ነት ነውና
ሥራ​ውም ሁሉ በእ​ም​ነት ነውና።
5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቅ​ንና#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ፍር​ድን” ይላል። ምጽ​ዋ​ትን ይወ​ድ​ዳል፤
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታው ምድ​ርን ሞላ።
6በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሰማ​ዮች ጸኑ፥
ሠራ​ዊ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ በአፉ እስ​ት​ን​ፋስ፤
7የባ​ሕ​ሩን ውኃ እንደ ረዋት የሚ​ሰ​በ​ስ​በው፥
በቀ​ላ​ዮ​ችም መዝ​ገ​ቦች የሚ​ያ​ኖ​ረው።
8ምድር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትፈ​ራ​ዋ​ለች፥
በዓ​ለም የሚ​ኖሩ ሁሉም ከእ​ርሱ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።
9እርሱ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና፥ ሆኑ፤
እርሱ አዘዘ፤ ተፈ​ጠ​ሩም።
10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ሕ​ዛ​ብን ምክር ይመ​ል​ሳል፥
የሕ​ዝ​ቡ​ንም ዐሳብ ይመ​ል​ሳል።
የአ​ለ​ቆ​ችን ምክ​ራ​ቸ​ውን ያስ​ረ​ሳ​ቸ​ዋል።
11የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክር ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል፥
የል​ቡም ዐሳብ ለልጅ ልጅ ነው።
12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኩ የሚ​ሆ​ን​ለት ሕዝብ ብፁዕ ነው፥
እርሱ ለር​ስቱ የመ​ረ​ጠው ሕዝብ።
13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ተመ​ለ​ከተ፥
የሰ​ው​ንም ልጆች ሁሉ አየ።
14ከተ​ዘ​ጋ​ጀው የመ​ቅ​ደሱ አዳ​ራሽ ሆኖ
በም​ድር ወደ​ሚ​ኖሩ ሁሉ ተመ​ለ​ከተ፤
15እርሱ ብቻ​ውን ልባ​ቸ​ውን የሠራ፥
ሥራ​ቸ​ው​ንም ሁሉ የሚ​ያ​ውቅ እርሱ ነው።
16ንጉሥ በሠ​ራ​ዊቱ ብዛት አይ​ድ​ንም፥
ኀያ​ልም በኀ​ይሉ ብዛት አይ​ድ​ንም።
17ፈረ​ስም ከንቱ ነው፥ አያ​ድ​ንም፤
በኀ​ይ​ሉም ብዛት አያ​መ​ል​ጥም።
18እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖች ወደ​ሚ​ፈ​ሩት ናቸው፤
በም​ሕ​ረ​ቱም ወደ​ሚ​ታ​መኑ፥
19ነፍ​ሳ​ቸ​ውን ከሞት ያድ​ና​ታል፥
በራ​ብም ጊዜ ይመ​ግ​ባ​ቸ​ዋል።
20ነፍ​ሳ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተስፋ ታደ​ር​ገ​ዋ​ለች፥
ረዳ​ታ​ች​ንና መጠ​ጊ​ያ​ችን እርሱ ነውና።
21ልባ​ችን በእ​ርሱ ደስ ይለ​ዋ​ልና፥
በቅ​ዱስ ስሙም ታም​ነ​ና​ልና።
22አቤቱ፥ በአ​ንተ እንደ ታመ​ንን፥
ምሕ​ረ​ትህ በላ​ያ​ችን ትሁን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ