መዝሙረ ዳዊት 57
57
ለመዘምራን አለቃ አታጥፋ። የዳዊት ቅኔ።
1በእውነት ጽድቅን ብትናገሩስ፥
የሰው ልጆች ሆይ፥ በቅን ትፈርዳላችሁ፤
2በልባችሁ በምድር ላይ ኀጢአትን ትሠራላችሁና፥
እጆቻችሁም ሽንገላን#ዕብ. “ግፍ” ይላል። ይታታሉና።
3ኀጥኣን ከማኅፀን ጀምረው ተለዩ፤
ከሆድም ጀምረው ሳቱ፥ ሐሰትንም ተናገሩ።
4ቍጣቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፥
ጆሮዋም እንደ ደነቈረ እባብ፥
5ዐዋቂ ሲደግምባት የአስማተኛውን ቃል እንደማትሰማ።
6እግዚአብሔር ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ይሰብራል፤
እግዚአብሔር የአንበሶቹን መንጋጋቸውን ያደቅቃል።
7እንደሚፈስስ ውኃ ይቀልጣሉ፤
እስከሚያደክማቸው ድረስ ፍላጻቹን ይገትራል።
8እንደሚቀልጥ ሰም ያልቃሉ፤
እሳት ወደቀች፥ ፀሐይንም አላየኋትም።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አላዩአትም” ይላል።
9እሾኻችሁ ሳይታወቅ በትር ሆነ፤
ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ይውጣችኋል።
10ጻድቅ በቀልን ባየ ጊዜ ደስ ይለዋል፤
በኀጢአተኛው ደምም እጁን ይታጠባል።
11ሰውም፥ “በእውነት ለጻድቅ ፍሬ አለው፤
በእውነት በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ” ይላል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 57: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 57
57
ለመዘምራን አለቃ አታጥፋ። የዳዊት ቅኔ።
1በእውነት ጽድቅን ብትናገሩስ፥
የሰው ልጆች ሆይ፥ በቅን ትፈርዳላችሁ፤
2በልባችሁ በምድር ላይ ኀጢአትን ትሠራላችሁና፥
እጆቻችሁም ሽንገላን#ዕብ. “ግፍ” ይላል። ይታታሉና።
3ኀጥኣን ከማኅፀን ጀምረው ተለዩ፤
ከሆድም ጀምረው ሳቱ፥ ሐሰትንም ተናገሩ።
4ቍጣቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፥
ጆሮዋም እንደ ደነቈረ እባብ፥
5ዐዋቂ ሲደግምባት የአስማተኛውን ቃል እንደማትሰማ።
6እግዚአብሔር ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ይሰብራል፤
እግዚአብሔር የአንበሶቹን መንጋጋቸውን ያደቅቃል።
7እንደሚፈስስ ውኃ ይቀልጣሉ፤
እስከሚያደክማቸው ድረስ ፍላጻቹን ይገትራል።
8እንደሚቀልጥ ሰም ያልቃሉ፤
እሳት ወደቀች፥ ፀሐይንም አላየኋትም።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አላዩአትም” ይላል።
9እሾኻችሁ ሳይታወቅ በትር ሆነ፤
ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ይውጣችኋል።
10ጻድቅ በቀልን ባየ ጊዜ ደስ ይለዋል፤
በኀጢአተኛው ደምም እጁን ይታጠባል።
11ሰውም፥ “በእውነት ለጻድቅ ፍሬ አለው፤
በእውነት በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ” ይላል።