መዝሙረ ዳዊት 59
59
ለመዘምራን አለቃ የሶርያን ሁለቱን ወንዞችና የሶርያን ሶባልን ባቃጠለ ጊዜ ኢዮአብም ተመልሶ ከኤዶማውያን ሰዎች በጨው ሸለቆ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን በገደለ ጊዜ ለትምህርት የዳዊት ቅኔ።
1አቤቱ፥ ጣልኸን አፈረስኸንም፤
ገረፍኸን፥ ይቅርም አልኸን።
2ምድርን አናወጥሃት፥ አወክሃትም፤
ተናውጣለችና ቍስልዋን ፈወስኻት።#ዕብ. “ፈውስ” ይላል።
3ለሕዝብህ ጭንቅን አሳየሃቸው፥
አስደንጋጩንም ወይን አጠጣኸን።
4ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው፥
ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ።
5ወዳጆችህም፥ እንዲድኑ
በቀኝህ አድን፥ ስማኝም።
6እግዚአብሔር በመቅደሱ ተናገረ፤
ደስ ይለኛል፥ ምርኮንም#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሴኬምንም” ይላል። እካፈላለሁ፥
የሸለቆ ቦታዎችን እሰፍራለሁ።
7ገለዓድ የእኔ ነው፥ ምናሴም የእኔ ነው፤
ኤፍሬም የራሴ መጠጊያ ነው።
ይሁዳ ንጉሤ ነው፤
8ካህን ሞአብም ተስፋዬ ነው#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሞአብ የተስፋዬ አፍላል ነው” ሲል ዕብ. “ሞአብ መታጠቢያዬ ነው” ይላል።
በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እዘረጋለሁ፤
ፍልስጥኤምም ይገዙልኛል።
9ቅጥር ወደ አለባት ወደ ጽኑ ከተማ ማን ይወስደኛል?
ማንስ እስከ ኤዶምያስ ይመራኛል?
10አቤቱ፥ የጣልኸን አንተ አይደለህምን?
አምላካችን ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር አትወጣም።
11በመከራችን ረድኤትን ስጠን፥
በሰውም መታመን ከንቱ ነው።
12በእግዚአብሔር ኀይልን እናደርጋለን፤
እርሱም የሚያስጨንቁንን ያዋርዳቸዋል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 59: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 59
59
ለመዘምራን አለቃ የሶርያን ሁለቱን ወንዞችና የሶርያን ሶባልን ባቃጠለ ጊዜ ኢዮአብም ተመልሶ ከኤዶማውያን ሰዎች በጨው ሸለቆ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን በገደለ ጊዜ ለትምህርት የዳዊት ቅኔ።
1አቤቱ፥ ጣልኸን አፈረስኸንም፤
ገረፍኸን፥ ይቅርም አልኸን።
2ምድርን አናወጥሃት፥ አወክሃትም፤
ተናውጣለችና ቍስልዋን ፈወስኻት።#ዕብ. “ፈውስ” ይላል።
3ለሕዝብህ ጭንቅን አሳየሃቸው፥
አስደንጋጩንም ወይን አጠጣኸን።
4ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው፥
ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ።
5ወዳጆችህም፥ እንዲድኑ
በቀኝህ አድን፥ ስማኝም።
6እግዚአብሔር በመቅደሱ ተናገረ፤
ደስ ይለኛል፥ ምርኮንም#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሴኬምንም” ይላል። እካፈላለሁ፥
የሸለቆ ቦታዎችን እሰፍራለሁ።
7ገለዓድ የእኔ ነው፥ ምናሴም የእኔ ነው፤
ኤፍሬም የራሴ መጠጊያ ነው።
ይሁዳ ንጉሤ ነው፤
8ካህን ሞአብም ተስፋዬ ነው#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሞአብ የተስፋዬ አፍላል ነው” ሲል ዕብ. “ሞአብ መታጠቢያዬ ነው” ይላል።
በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እዘረጋለሁ፤
ፍልስጥኤምም ይገዙልኛል።
9ቅጥር ወደ አለባት ወደ ጽኑ ከተማ ማን ይወስደኛል?
ማንስ እስከ ኤዶምያስ ይመራኛል?
10አቤቱ፥ የጣልኸን አንተ አይደለህምን?
አምላካችን ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር አትወጣም።
11በመከራችን ረድኤትን ስጠን፥
በሰውም መታመን ከንቱ ነው።
12በእግዚአብሔር ኀይልን እናደርጋለን፤
እርሱም የሚያስጨንቁንን ያዋርዳቸዋል።