መዝሙረ ዳዊት 7
7
ስለ ብንያማዊ ሰው ስለ ኩዝ ቃል ለእግዚአብሔር የዘመረው የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ አምላኬ፥ በአንተ ታመንሁ፥ አትጣለኝም፤
ከሚከብቡኝ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከሚያሳድዱኝ” ይላል። ሁሉ አድነኝና አውጣኝ፥
2ነፍሴን እንደ አንበሳ እንዳይነጥቋት፥
የሚያድንና የሚታደግ ሳይኖር።
3አቤቱ አምላኬ፥ እንዲህስ ካደረግሁ፥
ዐመፃም በእጄ ቢኖር፥
4ክፉ ላደረጉብኝም ክፉን መልሼላቸው ብሆን፥
ጠላቶቼ ዕራቁቴን ይጣሉኝ።
5ጠላት ነፍሴን ያሳድዳት፤ ያግኛትም፥
ሕይወቴን በምድር ላይ ይርገጣት፤
ክብሬንም በትቢያ ላይ ያዋርደው።
6አቤቱ፥ በመዓትህ ተነሥ፤
በጠላቶቼ ላይ ተነሣባቸው፤
አቤቱ፥ አምላኬ፥ ባዘዝኸው ሥርዐት ተነሥ።
7የአሕዛብም ጉባኤ ይከብብሃል፤
ስለዚህም ወደ አርያም ተመለስ።
8እግዚአብሔር በሕዝብ ላይ ይፈርዳል፤
አቤቱ አምላኬ፥ እንደ ጽድቅህ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እንደ ጽድቄ” ይላል። ፍረድልኝ፤
እንደ የዋህነቴም ይሁንልኝ።
9የኃጥኣን ክፋት ያልቃል፥
ጻድቃንን#ግሪክ ሰባ. ሊ. በነጠላ። ግን ታቃናቸዋለህ፤
እግዚአብሔር ልቡናንና ኵላሊትን ይመረምራል።
10እግዚአብሔር በእውነት ይረዳኛል#ዕብ. “የጽድቅ ጋሻዬ ነው” ይላል።
ልበ ቅኖችን የሚያድናቸው እርሱ ነው።
11እግዚአብሔር የእውነት ዳኛ ነው፤
ኀይለኛም ታጋሽም ነው፤
ሁልጊዜም ጥፋትን አያመጣም።
12ባትመለሱ ግን ሰይፉን ይመዝዛል፥#ዕብ. “ይስላል” ይላል።
ቀስቱን ገተረ አዘጋጀም፤
13የሚገድል መርዝንም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሞት መሣሪያን” ይላል። አዘጋጀበት፤
ፍላጻዎቹንም የሚቃጠሉ አደረገ።
14እነሆ፥ ዐመፀኛ በዐመፁ ተጨነቀ፤
ጭንቅን ፀነሰ፤ ኀጢአትንም ወለደ።
15ጕድጓድንም ማሰ፥ ቈፈረም።
ባደረገውም ጕድጓድ ይወድቃል።
16ጉዳቱ በራሱ ይመለሳል፥
ዐመፃውም በአናቱ ላይ ትወርዳለች።
17እግዚአብሔርን እንደ ጽድቁ መጠን አመሰግናለሁ፥
ለልዑል እግዚአብሔርም ስም እዘምራለሁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 7: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 7
7
ስለ ብንያማዊ ሰው ስለ ኩዝ ቃል ለእግዚአብሔር የዘመረው የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ፥ አምላኬ፥ በአንተ ታመንሁ፥ አትጣለኝም፤
ከሚከብቡኝ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከሚያሳድዱኝ” ይላል። ሁሉ አድነኝና አውጣኝ፥
2ነፍሴን እንደ አንበሳ እንዳይነጥቋት፥
የሚያድንና የሚታደግ ሳይኖር።
3አቤቱ አምላኬ፥ እንዲህስ ካደረግሁ፥
ዐመፃም በእጄ ቢኖር፥
4ክፉ ላደረጉብኝም ክፉን መልሼላቸው ብሆን፥
ጠላቶቼ ዕራቁቴን ይጣሉኝ።
5ጠላት ነፍሴን ያሳድዳት፤ ያግኛትም፥
ሕይወቴን በምድር ላይ ይርገጣት፤
ክብሬንም በትቢያ ላይ ያዋርደው።
6አቤቱ፥ በመዓትህ ተነሥ፤
በጠላቶቼ ላይ ተነሣባቸው፤
አቤቱ፥ አምላኬ፥ ባዘዝኸው ሥርዐት ተነሥ።
7የአሕዛብም ጉባኤ ይከብብሃል፤
ስለዚህም ወደ አርያም ተመለስ።
8እግዚአብሔር በሕዝብ ላይ ይፈርዳል፤
አቤቱ አምላኬ፥ እንደ ጽድቅህ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “እንደ ጽድቄ” ይላል። ፍረድልኝ፤
እንደ የዋህነቴም ይሁንልኝ።
9የኃጥኣን ክፋት ያልቃል፥
ጻድቃንን#ግሪክ ሰባ. ሊ. በነጠላ። ግን ታቃናቸዋለህ፤
እግዚአብሔር ልቡናንና ኵላሊትን ይመረምራል።
10እግዚአብሔር በእውነት ይረዳኛል#ዕብ. “የጽድቅ ጋሻዬ ነው” ይላል።
ልበ ቅኖችን የሚያድናቸው እርሱ ነው።
11እግዚአብሔር የእውነት ዳኛ ነው፤
ኀይለኛም ታጋሽም ነው፤
ሁልጊዜም ጥፋትን አያመጣም።
12ባትመለሱ ግን ሰይፉን ይመዝዛል፥#ዕብ. “ይስላል” ይላል።
ቀስቱን ገተረ አዘጋጀም፤
13የሚገድል መርዝንም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሞት መሣሪያን” ይላል። አዘጋጀበት፤
ፍላጻዎቹንም የሚቃጠሉ አደረገ።
14እነሆ፥ ዐመፀኛ በዐመፁ ተጨነቀ፤
ጭንቅን ፀነሰ፤ ኀጢአትንም ወለደ።
15ጕድጓድንም ማሰ፥ ቈፈረም።
ባደረገውም ጕድጓድ ይወድቃል።
16ጉዳቱ በራሱ ይመለሳል፥
ዐመፃውም በአናቱ ላይ ትወርዳለች።
17እግዚአብሔርን እንደ ጽድቁ መጠን አመሰግናለሁ፥
ለልዑል እግዚአብሔርም ስም እዘምራለሁ።