መዝሙረ ዳዊት 80
80
ለመዘምራን አለቃ በዋሽንት የአሳፍ መዝሙር።
1በረዳታችን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፥
ለያዕቆብም አምላክ እልል በሉ።
2ዝማሬውን አንሡ ከበሮውንም ስጡ፥
ደስ የሚያሰኘውን በገና ከመሰንቆ ጋር፤
3በመባቻ ቀን በታወቀችው በዓላችን ቀን
መለከትን ንፉ፤
4ለእስራኤል ሥርዐቱ ነውና፥
የያዕቆብም አምላክ ፍርድ ነውና።
5ወደ ግብፅ ሀገር በሄደ ጊዜ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከግብፅ በወጣ ጊዜ” ይላል። ለዮሴፍ ምስክርን አቆመ።
የማያውቀውን ቋንቋ ሰማ።#ዕብ. “ያላወቅኋትን ቋንቋ ሰማሁ” ይላል።
6ጀርባውን ከመስገጃቸው መለሰ፥
እጆቹም በቅርጫት ተገዙ።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ጫንቃውንም ከሸክም እጆቹንም በቅርጫት ከመገዛት አራቅሁ” ይላል።
7በመከራህ ጊዜ ጠራኸኝ፥ አዳንሁህም፥
በተሰወረ ዐውሎም መለስሁልህ፥
በክርክር ውኃ ዘንድም ፈተንሁህ።
8ሕዝቤ ሆይ፥ ስማኝ እነግርሃለሁም፤
እስራኤል ሆይ፥ እመሰክርልሃለሁ።
9አንተስ ብትሰማኝ የድንገት አምላክ አልሆንህም፥
ለሌላ አምላክም አትስገድ።
10ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝና፤
አፍህን አስፋ፥ እሞላዋለሁም።
11ሕዝቤ ግን ቃሌን አልሰሙኝም፥
እስራኤልም አላደመጡኝም።
12እንደ ሥራቸው ላክሁባቸው፥
በልባቸውም ዐሳብ ሄዱ።
13ሕዝቤስ ቃሌን ሰምተውኝ ቢሆን፥
እስራኤልም በመንገዴ ሄደው ቢሆን፤
14ጠላቶቻቸውን ፈጥኜ ባዋረድኋቸው ነበር፥
በሚያስጨንቋቸውም ላይ እጄን በጣልሁ ነበር፤
15የእግዚአብሔር ጠላቶችስ ዋሽተውት ነበር፥
ዘመናቸውም ለዘለዓለም ይሆናል፤
16ከስንዴም ስብ አበላቸው፥
ከዓለቱም ማር አጠገባቸው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 80: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መዝሙረ ዳዊት 80
80
ለመዘምራን አለቃ በዋሽንት የአሳፍ መዝሙር።
1በረዳታችን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፥
ለያዕቆብም አምላክ እልል በሉ።
2ዝማሬውን አንሡ ከበሮውንም ስጡ፥
ደስ የሚያሰኘውን በገና ከመሰንቆ ጋር፤
3በመባቻ ቀን በታወቀችው በዓላችን ቀን
መለከትን ንፉ፤
4ለእስራኤል ሥርዐቱ ነውና፥
የያዕቆብም አምላክ ፍርድ ነውና።
5ወደ ግብፅ ሀገር በሄደ ጊዜ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከግብፅ በወጣ ጊዜ” ይላል። ለዮሴፍ ምስክርን አቆመ።
የማያውቀውን ቋንቋ ሰማ።#ዕብ. “ያላወቅኋትን ቋንቋ ሰማሁ” ይላል።
6ጀርባውን ከመስገጃቸው መለሰ፥
እጆቹም በቅርጫት ተገዙ።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ጫንቃውንም ከሸክም እጆቹንም በቅርጫት ከመገዛት አራቅሁ” ይላል።
7በመከራህ ጊዜ ጠራኸኝ፥ አዳንሁህም፥
በተሰወረ ዐውሎም መለስሁልህ፥
በክርክር ውኃ ዘንድም ፈተንሁህ።
8ሕዝቤ ሆይ፥ ስማኝ እነግርሃለሁም፤
እስራኤል ሆይ፥ እመሰክርልሃለሁ።
9አንተስ ብትሰማኝ የድንገት አምላክ አልሆንህም፥
ለሌላ አምላክም አትስገድ።
10ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝና፤
አፍህን አስፋ፥ እሞላዋለሁም።
11ሕዝቤ ግን ቃሌን አልሰሙኝም፥
እስራኤልም አላደመጡኝም።
12እንደ ሥራቸው ላክሁባቸው፥
በልባቸውም ዐሳብ ሄዱ።
13ሕዝቤስ ቃሌን ሰምተውኝ ቢሆን፥
እስራኤልም በመንገዴ ሄደው ቢሆን፤
14ጠላቶቻቸውን ፈጥኜ ባዋረድኋቸው ነበር፥
በሚያስጨንቋቸውም ላይ እጄን በጣልሁ ነበር፤
15የእግዚአብሔር ጠላቶችስ ዋሽተውት ነበር፥
ዘመናቸውም ለዘለዓለም ይሆናል፤
16ከስንዴም ስብ አበላቸው፥
ከዓለቱም ማር አጠገባቸው።