መዝሙረ ዳዊት 82
82
የአሳፍ የምስጋና መዝሙር።
1አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው?
አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል።
2እነሆ፥ ጠላቶችህ ጮኸዋልና፥
ጠላቶችህም ራሳቸውን አንሥተዋልና።
3ሕዝብህን በምክር ሸነገሉአቸው፥
በቅዱሳንህም ላይ ተማከሩ።
4“ኑ ከሕዝብ ለይተን እናጥፋቸው፥
ከእንግዲህም ወዲህ የእስራኤልን ስም አያስቡ” አሉ።
5በአንድነት ተካክለው ተማክረዋልና፤
በአንተ ላይ ሤራ ቈረጡ፤
ቃል ኪዳንም አደረጉ፤
6የኤዶምያስ ወገኖች፥ እስማኤላውያንም፥
ሞዓባውያንም፥ አጋራውያንም፥
7ጌባል፥ አሞንም፥ አማሌቅም፥
ፍልስጥኤማውያንም ከጢሮስ ሰዎች ጋር፤
8አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፥
ለሎጥ ልጆችም ረዳት ሆኑአቸው።
9እንደ ምድያምና እንደ ሲሣራ፥
በቂሶንም ወንዝ እንደ ኢያቢስ አድርግባቸው።
10እንደ ዕንዶር ሰዎች ይጥፉ
እንደ ምድር ትቢያ ይሁኑ።
11አለቆቻቸውን እንደ ሔሬብና እንደ ዜብ፥
ታላላቆቻቸውንም ሁሉ እንደ ዛብሄልና እንደ ስልማና አድርጋቸው።
12የእግዚአብሔርን መሠዊያ እንወርሳለን የሚሉትን።
13አምላኬ ሆይ፥ እንደ መንኰራኵር፥
በእሳት#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በነፋስ ፊት” ይላል። ፊትም እንደ አለ ገለባ አድርጋቸው።
14እሳት ዱርን እንደሚያቃጥል፥
ነበልባልም ተራሮችን እንደሚያነድድ፥
15እንዲሁ በቍጣህ አሳድዳቸው፥
በመቅሠፍትህም አስደንግጣቸው።
16በፊታቸው እፍረትን ሙላ፥
አቤቱ፥ ስምህን ይወቁ።#ዕብ. “ይፈልጉ” ይላል።
17ይፈሩ፥ ለዘለዓለሙም ይታወኩ፤
ይጐስቍሉ፥ ይጥፉም።
18ስምህም እግዚአብሔር እንደ ሆነ፥
በምድር ሁሉ ላይም አንተ ብቻ ልዑል እንደ ሆንህ ይወቁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 82: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ