መዝሙረ ዳዊት 90
90
የዳዊት የምስጋና መዝሙር።
1በልዑል ረድኤት#ዕብ. “መጠጊያ” ይላል። የሚያድር፥
በሰማይ አምላክ ጥላ ውስጥ የሚቀመጥ፥
2እግዚአብሔርን፥ “አንተ መጠጊያዬና አምባዬ#“አምባዬ” የሚለው በዕብ. እና በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ነህ፤
አምላኬና ረዳቴ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ” ይለዋል።
3እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ፥
ከሚያስደነግጥም ነገር ያድነኛልና።
4በላባዎቹ ይጋርድሃል፥
በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤
እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል።
5ከሌሊት ግርማ፥
በመዓልት ከሚበርር ፍላጻ፥
6በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ሥራ፥
ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም።
7በአጠገብህ ሺህ፥ በቀኝህም ዐሥር ሺህ ይወድቃሉ፤
ወደ አንተ ግን አይቀርቡም።
8በዐይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥
የኃጥኣንንም ፍዳ ታያለህ።
9አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፤
ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ።
10ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥
መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።
11በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ
መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤
12እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል
በእጆቻቸው ያነሡሃል።
13በተኵላና በእባብ ላይ ትጫናለህ፤#ዕብ. “እጫማለሁ” ይላል።
አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።
14በእኔ ተማምኖአልና አድነዋለሁ
ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።
15ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥
በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ፤
አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።
16ረዥም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፥
ማዳኔንም አሳየዋለሁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 90: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ