ወደ ሮሜ ሰዎች 2:6-11

ወደ ሮሜ ሰዎች 2:6-11 አማ2000

እርሱ በእ​ው​ነ​ተና ፍርዱ ለሁሉ እንደ ሥራው ይከ​ፍ​ለ​ዋ​ልና። በበጎ ምግ​ባር ጸን​ተው ለሚ​ታ​ገሡ፥ ምስ​ጋ​ናና ክብ​ርን፥ የማ​ይ​ጠፋ ሕይ​ወ​ት​ንም ለሚሹ እርሱ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል። ለሚ​ክ​ዱና እው​ነ​ትን ለሚ​ለ​ውጡ፥ ዐመ​ፅ​ንም ለሚ​ወ​ድዱ ሰዎች ዋጋ​ቸው ቍጣና መቅ​ሠ​ፍት ነው። መከ​ራና ጭን​ቀት አስ​ቀ​ድሞ በአ​ይ​ሁ​ዳዊ፥ ደግ​ሞም በአ​ረ​ማዊ፥ ሥራዉ ክፉ በሆነ ሰው ሁሉ ላይ ነው። ምስ​ጋ​ናና ክብር፥ ሰላ​ምም አስ​ቀ​ድሞ ለአ​ይ​ሁ​ዳዊ፥ ደግ​ሞም ለአ​ረ​ማዊ፥ ሥራዉ መል​ካም ለሆነ ሁሉ ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ፊት አያ​ዳ​ላ​ምና።