ወደ ሮሜ ሰዎች 3
3
ስለ አይሁዳዊነት ጥያቄ
1እንግዲህ አይሁዳዊ የመባል ትርፉ ምንድን ነው? የግዝረትስ ጥቅምዋ ምንድን ነው? 2በሁሉ ነገር ብዙ ነው፤ ነገር ግን ከዚያ አስቀድሞ የእግዚአብሔር ቃል አደራ ተሰጣቸው። 3የማያምኑ ቢኖሩስ የእነርሱ አለማመን ሌላውን በእግዚአብሔር እንዳያምን ይከለክላልን? አይከለክልም። 4#መዝ. 50፥4። መጽሐፍ፥ “በነገርህ ትጸድቅ ዘንድ፥ በፍርድህም ታሸንፍ ዘንድ” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር እውነተና ነውና፥ ሰውም ሁሉ ሐሰተና ነውና። 5በእኔ ኀጢአት#ግሪኩ በእና ኀጢአት ...” ይላል። የእግዚአብሔር ጽድቅ ከጸና እንግዲህ ምን እንላለን? እግዚአብሔር በሰው ላይ ቅጣትን ቢያመጣ ይበድላልን? አይበድልም፤ የምናገረውንም በሰው ልማድ እናገራለሁ። 6እንዲህማ ከሆነ እግዚአብሔር በዓለም እንደምን ይፈርዳል? 7የእግዚአብሔር እውነት በእኔ ሐሰተናነት ለክብሩ ከፍ ከአለ እንግዲህ እኔን እንደ ኀጢአተና ለምን ይፈርድብናል? 8በውኑ እና መልካም ነገር እናገኝ ዘንድ ክፉ ነገር እናድርግ እንደምንል አስመስለው የሚጠረጥሩንና የሚነቅፉን ሰዎች እንደሚሰድቡን ነን? ለእነርሱስ ቅጣታቸው ተዘጋጅቶላቸዋል።
9እንግዲህ ምን እንላለን? ከእነርሱ እንበልጣለን? አይደለም፤ አይሁዳዊንም፥ አረማዊንም እነሆ፥ አስቀድመን ነቅፈናቸዋል፤ ሁሉም ስተዋልና። 10መጽሐፍ እንዲህ እንዳለ “አንድ ስንኳ ጻድቅ የለም። 11አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚሻው የለም። 12#መዝ. 13፥1-3፤ 52፥1-3። ሁሉም ተባብሮ በደለ፤ በጎ ሥራንም የሚሠራ የለም፤ አንድ ስንኳ ቢሆን የለም። 13#መዝ. 5፥9፤ 139፥3። ጕረሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በአንደበታቸውም ሸነገሉ፤ ከከንፈሮቻቸውም በታች የእባብ መርዝ አለ፤ 14#መዝ. 10፥7። አፋቸው መራራ ነው፤ መርገምንም የተሞላ ነው። 15እግሮቻቸውም ደምን ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው። 16በመንገዳቸው ጥፋትና ጕስቍልና አለ። 17#ኢሳ. 59፥7-8። የሰላምን መንገድ አያውቋትም። 18#መዝ. 35፥1። በዐይኖቻቸውም ፊት እግዚአብሔርን መፍራት የለም።”
19አንደበት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚናገረው ሁሉ በኦሪት ላሉት እንደ ተነገረ እናውቃለን። 20#መዝ. 142፥2፤ ገላ. 2፥16። ከኦሪት የተነሣ ኀጢአት ስለ ታወቀች ሰው ሁሉ የኦሪትን ሥርዐት በመፈጸም በእግዚአብሔር ፊት አይጸድቅም።
21አሁን ግን በኦሪትና በነቢያት የተመሰከረላት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ኦሪት ተገለጠች። 22#ገላ. 2፥16። የሚያምኑበት ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን በእግዚአብሔር ዘንድ ይጸድቃሉ። 23በዚህም ልዩነት የለም፤ ሁሉም ፈጽመው በድለዋልና፤ እግዚአብሔርን ማክበርንም ትተዋልና። 24ጽድቅ ግን በኢየሱስ ክርስቶስም ቤዛነት ያለ ዋጋ በእርሱ ቸርነት ሆነ። 25እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ፥ በደሙም የሆነ ማስተስረያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም ከጥንት ጀምሮ በበደሉት ላይ ጽድቁን ይገልጥ ዘንድ ነው። 26እግዚአብሔር ታጋሽ በመሆኑ፥ እሺ በማለቱም እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስም የሚያምኑትን እንደሚያጸድቃቸው ዛሬ ያውቁ ዘንድ ነው። 27ትምክሕት ወዴት አለ? እርሱ ቀርቶአል፤ በየትናውስ ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፤ በእምነት ሕግ ነው እንጂ። 28ሰው የኦሪትን ሥራ ሳይሠራ በእምነት እንዲጸድቅ እናውቃለንና። 29በውኑ እግዚአብሔር ለአይሁድ ለብቻቸው ነውን? ለአሕዛብስ አይደለምን? 30#ዘዳ. 26፥4፤ ገላ. 3፥20። አዎን፥ ለአሕዛብም ነው፤ የተገዘረውን በእምነት የሚያጸድቅ፥ ያልተገዘረውንም በእምነት የሚያጸድቀው እርሱ አንዱ እግዚአብሔር ነውና። 31እንግዲህ በእምነት ኦሪትን እንሽራለን? አንሽርም፤ ኦሪትን እናጸናለን እንጂ።
Currently Selected:
ወደ ሮሜ ሰዎች 3: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ