የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ሮሜ ሰዎች 8

8
የኦ​ሪት ሕግ ሰውን ማዳን እንደ ተሳ​ነው
1እን​ግ​ዲህ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ላሉት በመ​ን​ፈስ እንጂ በሥጋ ለማ​ይ​መ​ላ​ለሱ ፍርድ የለ​ባ​ቸ​ውም። 2በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የተ​ሰ​ጠን ሕይ​ወት የሚ​ገ​ኝ​በት የመ​ን​ፈስ ሕግ እርሱ ከኀ​ጢ​አ​ትና ከሞት ሕግ ነጻ አው​ጥ​ቶ​ና​ልና።#አን​ዳ​ንድ የግ​ሪ​ክና ምን​ባብ “ነጻ አው​ጥ​ቶ​ናል” ይላል። 3ስለ ሥጋ ደካ​ማ​ነት የኦ​ሪት ሕግ ከሞት ማዳን በተ​ሳ​ነው ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኀ​ጢ​ኣ​ተና ሥጋ ምሳሌ ልጁን ላከ፤ ያች​ንም ኀጢ​አት በሥ​ጋው ቀጣት። 4እናን ያጸ​ድ​ቀን ዘንድ፥ የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ ሠርቶ እንደ ፈጸመ ሰው ያደ​ር​ገን ዘንድ፤ ይህም በመ​ን​ፈ​ሳዊ ሕግ ጸን​ተው ለሚ​ኖሩ ነው እንጂ በሥጋ ሕግ ለሚ​ሠሩ አይ​ደ​ለም። 5እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚ​ኖሩ የሥ​ጋን ነገር ያስ​ባ​ሉና፤ እንደ መን​ፈስ ፈቃድ የሚ​ኖሩ ግን የመ​ን​ፈ​ስን ነገር ያስ​ባሉ። 6የሥጋ ዐሳብ ሞትን ያመ​ጣ​ብ​ናል፤ የመ​ን​ፈስ ዐሳብ ግን ሰላ​ም​ንና ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጠ​ናል። 7የሥጋ ዐሳብ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላቱ ነውና፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ ስለ​ማ​ይ​ገዛ፥ መፈ​ጸም አይ​ቻ​ለ​ውም። 8ለሥ​ጋዊ ፈቃ​ዳ​ቸው የሚ​ሠሩ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ ማሰ​ኘት አይ​ች​ሉም።
9እና​ንተ ግን ለመ​ን​ፈ​ሳዊ ሕግ እንጂ ለሥ​ጋ​ችሁ ፈቃድ የም​ት​ሠሩ አይ​ደ​ላ​ች​ሁም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በእ​ና​ንተ አድሮ ይኖ​ራ​ልና፤ የክ​ር​ስ​ቶስ መን​ፈስ ያላ​ደ​ረ​በት ግን እርሱ የእ​ርሱ ወገን አይ​ደ​ለም። 10ክር​ስ​ቶስ ካደ​ረ​ባ​ችሁ ግን ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ከኀ​ጢ​አት ሥራ ለዩ፤ መን​ፈ​ሳ​ች​ሁ​ንም ለጽ​ድቅ ሥራ ሕያው አድ​ርጉ። 11#1ቆሮ. 3፥16። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ካደ​ረ​ባ​ችሁ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣው እርሱ አድ​ሮ​ባ​ችሁ ባለ መን​ፈሱ ለሟች ሰው​ነ​ታ​ችሁ ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ታል።
ሥጋዊ ሥራን ማዘ​ው​ተር የማ​ይ​ገባ ስለ መሆኑ
12ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ አሁ​ንም በሥ​ጋ​ችን ሳለን በሥጋ ፈቃድ እን​ኖር ዘንድ አይ​ገ​ባም። 13እንደ ሥጋ ፈቃድ ብት​ኖሩ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን በመ​ን​ፈ​ሳዊ ሥራ የሥ​ጋ​ች​ሁን ፈቃድ ብት​ገ​ድሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ላ​ችሁ። 14በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ የሚ​ሠሩ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ናቸው። 15#ማር. 14፥36፤ ገላ. 4፥6። ዳግ​መ​ናም አባ አባት ብለን የም​ን​ጮ​ህ​በ​ትን የል​ጅ​ነት መን​ፈስ ተቀ​በ​ላ​ችሁ እንጂ እንደ ገና ለፍ​ር​ሀት የባ​ር​ነት መን​ፈ​ስን አል​ተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁ​ምና። 16እና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች እን​ደ​ሆን ለል​ቡ​ና​ችን ምስ​ክሩ እርሱ መን​ፈስ ቅዱስ ነው። 17#ገላ. 4፥5-7። እና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ከሆን ወራ​ሾቹ ነን፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወራ​ሾች ከሆ​ንም የክ​ር​ስ​ቶስ ወራ​ሾቹ ነን፤ በመ​ከራ ከመ​ሰ​ል​ነ​ውም በክ​ብር እን​መ​ስ​ለ​ዋ​ለን።
ስለ መን​ግ​ሥተ ሰማ​ያት
18ነገር ግን የዚህ ዓለም መከራ ለእና ሊገ​ለጥ ከአ​ለው ክብር ጋር እን​ደ​ማ​ይ​ተ​ካ​ከል ዐስቡ። 19የዓ​ለም ተስ​ፋው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ#ግሪኩ“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች” ይላል። መም​ጣት ይጠ​ባ​በቅ ነበ​ርና። 20#ዘፍ. 3፥17-19። ዓለም ባለ​ማ​ወቅ ለከ​ንቱ ነገር ተገ​ዝ​ቶ​አ​ልና በተ​ስፋ ስለ አስ​ገ​ዛው ነው እንጂ በፈ​ቃዱ አይ​ደ​ለም። 21ነገር ግን አስቶ በባ​ር​ነት ከሚ​ገ​ዛው ከዚህ ወጥቶ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ወደ አገ​ኙ​አት የነ​ጻ​ነት ክብር ይገባ ዘንድ ተስፋ አለው። 22እስ​ካ​ሁን ዓለም ሁሉ ያዘ​ነና የተ​ከዘ እንደ ሆነ እና​ው​ቃ​ለን። 23#2ቆሮ. 5፥2-4። ነገር ግን የሚ​ተ​ክዝ ዓለም ብቻ አይ​ደ​ለም፤ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ፈለማ የተ​ቀ​በ​ል​ነው እናም ደግሞ እና​ዝ​ና​ለን እንጂ፤ የነ​ፍ​ሳ​ች​ንን ድኅ​ነት እና​ገኝ ዘንድ የል​ጅ​ነ​ትን ክብር ተስፋ እና​ደ​ር​ጋ​ለ​ንና፤ በእ​ም​ነ​ትም ድነ​ና​ልና። 24የሚ​ታ​የ​ውን ተስፋ ማድ​ረግ ተስፋ አይ​ደ​ለም፤ የሚ​ያ​የ​ው​ንማ እን​ዴት ተስፋ ያደ​ር​ጋል? እን​ዴ​ትስ ይጠ​ብ​ቃል?#“እን​ዴ​ትስ ይጠ​ብ​ቃል” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። 25የማ​ይ​ታ​የ​ውን ተስፋ ብና​ደ​ርግ ግን እር​ሱን ተስፋ አድ​ር​ገን በእ​ርሱ እንደ ጸናን መጠን#“እር​ሱን ተስፋ አድ​ር​ገን በእ​ርሱ እንደ ጸናን መጠን” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ትዕ​ግ​ሥ​ታ​ችን ይታ​ወ​ቃል። 26መን​ፈስ ቅዱ​ስም ከድ​ካ​ማ​ችን ይረ​ዳ​ናል፤ እን​ግ​ዲ​ያስ ተስ​ፋ​ች​ንን ካላ​ወ​ቅን ጸሎ​ታ​ችን ምን​ድ​ነው? ነገር ግን እርሱ ራሱ መን​ፈስ ቅዱስ ስለ መከ​ራ​ች​ንና ስለ ችግ​ራ​ችን ይፈ​ር​ድ​ል​ናል።#ምዕ. 8 ቍ. 26 በግ​እ​ዙና በግ​ሪኩ ሰፊ ልዩ​ነት አለ። 27እር​ሱም ልባ​ች​ንን ይመ​ረ​ም​ራል፤ ልብ የሚ​ያ​ስ​በ​ው​ንም እርሱ ያው​ቃል፤ ስለ ቅዱ​ሳ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይፈ​ር​ዳል።#ግሪኩ “ልብ​ንም የሚ​መ​ረ​ም​ረው የመ​ን​ፈስ ዐሳብ ምን እን​ደ​ሆነ ያው​ቃል፤ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈቃድ ስለ ቅዱ​ሳን ይማ​ል​ዳ​ልና” ይላል። 28እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ዱ​ትን ምር​ጦ​ቹን በበጎ ምግ​ባር ሁሉ እን​ደ​ሚ​ረ​ዳ​ቸው እና​ው​ቃ​ለን። 29ልጁ በብ​ዙ​ዎች ወን​ድ​ሞች መካ​ከል በኵር ይሆን ዘንድ አስ​ቀ​ድሞ ያወ​ቃ​ቸ​ው​ንና የመ​ረ​ጣ​ቸ​ውን እነ​ር​ሱን ልጁን ይመ​ስሉ ዘንድ አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​አ​ቸ​ዋል። 30ያዘ​ጋ​ጃ​ቸ​ውን እነ​ር​ሱን ጠራ፤ የጠ​ራ​ቸ​ው​ንም እነ​ር​ሱን አጸ​ደቀ፤ የአ​ጸ​ደ​ቃ​ቸ​ው​ንም እነ​ር​ሱን አከ​በረ።
31እን​ግ​ዲህ ስለ​ዚህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእና ጋር ከሆነ ማን ይች​ለ​ናል?#ግሪኩ “ማን ይቃ​ወ​መ​ናል” ይላል። 32ለልጁ ስንኳ አል​ራ​ራም፤ ስለ ሁላ​ችን ቤዛ አድ​ርጎ አሳ​ልፎ ሰጠው እንጂ፥ እን​ግ​ዲህ እርሱ ሁሉን እን​ዴት አይ​ሰ​ጠ​ንም? 33እን​ግ​ዲህ እርሱ ራሱ ካጸ​ደቀ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ረ​ጣ​ቸ​ውን ሰዎች የሚ​ቃ​ወ​ማ​ቸው ማነው? 34የሚ​ፈ​ር​ድስ ማነው? የሞ​ተው፥ ይል​ቁ​ንም ከሙ​ታን ተለ​ይቶ የተ​ነ​ሣው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀኝ የተ​ቀ​መ​ጠው፥ ደግሞ ስለ እና የሚ​ፈ​ር​ደው#ግሪኩ “የሚ​ማ​ል​ደው” ይላል። ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነው። 35ከክ​ር​ስ​ቶስ ፍቅር ማን ይለ​የ​ናል? መከራ ነውን? ኀዘን ነውን? ስደት ነውን? ራብ ነውን? መራ​ቆት ነውን? ጭን​ቀት ነውን? ሾተል ነውን? 36#መዝ. 43፥22። መጽ​ሐፍ እን​ዳለ፥ “ስለ አንተ ዘወ​ትር ይገ​ድ​ሉ​ናል፤ እን​ደ​ሚ​ታ​ረዱ በጎ​ችም ሆነ​ናል።” 37ነገር ግን በወ​ደ​ደን በእ​ርሱ ሁሉን ድል እን​ነ​ሣ​ለን። 38ነገር ግን ሞትም ቢሆን፥ ሕይ​ወ​ትም ቢሆን፥ መላ​እ​ክ​ትም ቢሆኑ፥ አለ​ቆ​ችም ቢሆኑ፥ ያለ​ውም ቢሆን፥ የሚ​መ​ጣ​ውም ቢሆን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ካለ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍቅር ሊለ​የን እን​ደ​ማ​ይ​ችል አም​ና​ለሁ። 39ኀይ​ልም ቢሆን፥ ከፍ​ታም ቢሆን፥ ዝቅ​ታም ቢሆን፥ ሌላ ፍጥ​ረ​ትም ቢሆን ከክ​ር​ስ​ቶስ ፍቅር ሊለ​የን የሚ​ችል የለም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ