መጽሐፈ ሲራክ 2
2
ለእግዚአብሔር ታማኝ ስለ መሆን
1ልጄ ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ትገዛ ዘንድ ብትሄድ
ሰውነትህን ለመከራ አዘጋጅ።
2ልብህን አቅና፥ ታገሥ፥ አታወላውልም፥
ብትጨነቅም አትጠራጠር።
3ነገር ግን ተከተለው፥
በፍጻሜህም ሕይወትህ ትበለጽግ ዘንድ አትተወው።
4የደረሰብህን ሁሉ ተቀበል፥
በችግርህም ወራት ታገሥ።
5ወርቅን በእሳት ይፈትኑታልና፥
ጻድቅንም ሰው በመከራ ይፈትኑታልና።
6ነገር ግን እግዚአብሔርን እመነው፤ እርሱም ይረዳሃል፤
መንገድህንም አቅና፥ በእርሱም እመን።
7እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሆይ፥ ቸርነቱን ደጅ ጥኗት፥
በመከራም እንዳትወድቁ ከእርሱ አትራቁ።
8እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሆይ፥
ዋጋችሁን እንዳታጡ እመኑት።
9እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሆይ፥
የዘለዓለም በጎነቱን ምሕረቱንና ደስታውን ተስፋ አድርጉ።
10በዘመን የቀደሙ ሰዎችን ተመልከቱ፤ ዕወቁም፥
በእግዚአብሔር አምኖ ያፈረ ማንነው?
እርሱን በመፍራት የታገሠና የተጣለ ማንነው?
ጠርቶትስ ቸል ያለው ማንነው?
11እግዚአብሔር መሓሪ ይቅር ባይም ነውና፥
ኀጢአትን ይቅር ይላል፥ በመከራ ቀንም ያድናል።
12ለሚጠራጠር ልቡና ወዮለት! ለጠማሞች እጆችም ወዮላቸው!
ሥራው ሁለት ለሆነ፥ በሁለትም መንገድ ለሚሄድ ኀጢአተኛ ወዮለት!
13ለሚጠራጠርና ለማያምንም ልብ ወዮለት!
ስለዚህም አያመልጥም።
14ትዕግሥታቸውን ላጡ ሰዎች ወዮላቸው!
እግዚአብሔር በተመለሰባቸው ጊዜ ምን ያደርጉ ይሆን?
15እግዚአብሔርን የሚፈሩ ቃሉን አይረሱም፥
የሚወዱትም ትእዛዙንና መንገዱን ይጠብቃሉ።
16እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ፈቃዱን ይሻሉ፤
የሚወዱትም በሕጉ ይረካሉ፤
17እግዚአብሔርን የሚፈሩ ልቡናቸውን ያዘጋጃሉ።
በፊቱም ሰውነታቸውን ያዋርዳሉ።
18በሰው እጅ ከምንወድቅ በእግዚአብሔር እጅ እንውደቅ፥
እንደ ልዕልናው የቸርነቱ ብዛት እንዲሁ ነውና።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 2: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ሲራክ 2
2
ለእግዚአብሔር ታማኝ ስለ መሆን
1ልጄ ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ትገዛ ዘንድ ብትሄድ
ሰውነትህን ለመከራ አዘጋጅ።
2ልብህን አቅና፥ ታገሥ፥ አታወላውልም፥
ብትጨነቅም አትጠራጠር።
3ነገር ግን ተከተለው፥
በፍጻሜህም ሕይወትህ ትበለጽግ ዘንድ አትተወው።
4የደረሰብህን ሁሉ ተቀበል፥
በችግርህም ወራት ታገሥ።
5ወርቅን በእሳት ይፈትኑታልና፥
ጻድቅንም ሰው በመከራ ይፈትኑታልና።
6ነገር ግን እግዚአብሔርን እመነው፤ እርሱም ይረዳሃል፤
መንገድህንም አቅና፥ በእርሱም እመን።
7እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሆይ፥ ቸርነቱን ደጅ ጥኗት፥
በመከራም እንዳትወድቁ ከእርሱ አትራቁ።
8እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሆይ፥
ዋጋችሁን እንዳታጡ እመኑት።
9እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሆይ፥
የዘለዓለም በጎነቱን ምሕረቱንና ደስታውን ተስፋ አድርጉ።
10በዘመን የቀደሙ ሰዎችን ተመልከቱ፤ ዕወቁም፥
በእግዚአብሔር አምኖ ያፈረ ማንነው?
እርሱን በመፍራት የታገሠና የተጣለ ማንነው?
ጠርቶትስ ቸል ያለው ማንነው?
11እግዚአብሔር መሓሪ ይቅር ባይም ነውና፥
ኀጢአትን ይቅር ይላል፥ በመከራ ቀንም ያድናል።
12ለሚጠራጠር ልቡና ወዮለት! ለጠማሞች እጆችም ወዮላቸው!
ሥራው ሁለት ለሆነ፥ በሁለትም መንገድ ለሚሄድ ኀጢአተኛ ወዮለት!
13ለሚጠራጠርና ለማያምንም ልብ ወዮለት!
ስለዚህም አያመልጥም።
14ትዕግሥታቸውን ላጡ ሰዎች ወዮላቸው!
እግዚአብሔር በተመለሰባቸው ጊዜ ምን ያደርጉ ይሆን?
15እግዚአብሔርን የሚፈሩ ቃሉን አይረሱም፥
የሚወዱትም ትእዛዙንና መንገዱን ይጠብቃሉ።
16እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ፈቃዱን ይሻሉ፤
የሚወዱትም በሕጉ ይረካሉ፤
17እግዚአብሔርን የሚፈሩ ልቡናቸውን ያዘጋጃሉ።
በፊቱም ሰውነታቸውን ያዋርዳሉ።
18በሰው እጅ ከምንወድቅ በእግዚአብሔር እጅ እንውደቅ፥
እንደ ልዕልናው የቸርነቱ ብዛት እንዲሁ ነውና።