መጽ​ሐፈ ሲራክ 43

43
1የጠ​ራች ጠፈ​ርን በህ​ዋው ላይ አጸ​ናት፤
የሰ​ማ​ይም መታ​የት በክ​ብሩ ነው።
2ብር​ሃ​ኑን ያሳይ ዘንድ ፀሐ​ይን ያወ​ጣል፤
የሰ​ማ​ይም ብር​ሃን ሥር​ዐቱ ድንቅ ነው ።
3በዋ​ዕ​ዩም ሀገ​ሩን ያቃ​ጥ​ላል፤
ዋዕ​ዩ​ንስ ማን ይቋ​ቋ​መ​ዋል?
4ዋዕ​ዩ​ንም እሳት እን​ደ​ሚ​ነ​ድ​ድ​ባት ምድጃ ያደ​ር​ጋል፤
ፀሐይ ግን ከሦ​ስት ጊዜ በላይ የበ​ለጠ ተራ​ሮ​ችን ያቃ​ጥ​ላ​ቸ​ዋል።
ከእ​ርሱ የሚ​ወ​ጣው እሳ​ታዊ ዋዕይ፥ የሚ​ል​ከ​ውም ብር​ሃን ዐይን ያጨ​ል​ማል፤
5የፈ​ጠ​ረው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታላቅ ነው፤
በቃ​ሉም ፈጥኖ ይሄ​ዳል።
6ጨረ​ቃም ለሁሉ የዘ​መን መለ​ኪያ ናት፤
ለዓ​ለ​ምም ሁሉ ምል​ክት ናት፤ በእ​ር​ስ​ዋም ቀን ይለ​ያል።
7በጨ​ረ​ቃም የበ​ዓ​ላት ምል​ክት ይታ​ወ​ቃል፤
ሕፀፅ እያ​ደ​ረ​ገች የም​ታ​ልቅ ብር​ሃን እር​ስዋ ናት።
8ጨረ​ቃስ እንደ ስሟ ናት፤ ዕድ​ገ​ት​ዋም ድንቅ ነው፤
በሰ​ማይ ሠራ​ዊት ሥር​ዐ​ትም ሕፀ​ፅ​ንና ምላ​ትን ማፈ​ራ​ረ​ቅዋ ድንቅ ነው፤
በሰ​ማይ ሠራ​ዊት መካ​ከ​ልም ታበ​ራ​ለች።
9የሰ​ማ​ይም ጌጥ የከ​ዋ​ክ​ብት ብር​ሃን ነው።
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰማይ ለዓ​ለም ያበ​ራሉ።
10በቅ​ዱ​ሱም ቃል በየ​ሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ጸን​ተው ይኖ​ራሉ፤
ከሥ​ር​ዐ​ታ​ቸ​ውም ወጥ​ተው አያ​ል​ፉም።
11ብር​ሃኑ ፈጽሞ ያማረ ነውና፥
ቀስተ ደመ​ና​ውን አይ​ተህ ፈጣ​ሪ​ውን አመ​ስ​ግ​ነው።
12በሰ​ማይ ይከ​ፈ​ላል፤
ብር​ሃ​ኑም ይከ​በ​ዋል፤
የል​ዑ​ልም እጅ ይከ​ፍ​ለ​ዋል።
13በት​እ​ዛዙ በረድ ይዘ​ን​ባል፤
መብ​ረ​ቅም በፈ​ቃዱ ፈጥኖ ይወ​ር​ዳል።
14ስለ​ዚህ ነገር መዛ​ግ​ብ​ቱን ይገ​ል​ጣል፤
ደመ​ና​ትም እንደ ወፎች ይበ​ር​ራሉ።
15በገ​ና​ና​ነ​ቱም ደመ​ና​ትን ያጸ​ና​ቸ​ዋል፤
የበ​ረድ ድን​ጋ​ይም ይሰ​ባ​በ​ራል።
16በመ​ጐ​ብ​ኘ​ቱም ተራ​ሮች ይነ​ዋ​ወ​ጣሉ፤
በፈ​ቃ​ዱም የም​ሥ​ራቅ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የደ​ቡብ” ይላል። ነፋስ ይነ​ፍ​ሳል።
17የመ​ብ​ረ​ቁም ድምፅ ምድ​ርን ያስ​ፈ​ራ​ታል፤
የም​ዕ​ራ​ብም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሰ​ሜን” ይላል። ነፋስ ሰው​ነ​ትን ያደ​ር​ቃ​ታል፤
በረ​ድ​ንም እን​ደ​ሚ​በ​ርሩ ወፎች ይበ​ት​ነ​ዋል፤
አወ​ራ​ረ​ዱም እንደ አን​በጣ አወ​ራ​ረድ ነው።
18የን​ጣ​ቱም ውበት ለዐ​ይን ድንቅ ነው፤
መዝ​ነ​ቡም ለልብ ድንቅ ነው።
19በረ​ድን እንደ ጨው ያፈ​ስ​ሰ​ዋ​ልና፤
ጉም​ንም በም​ድር ላይ ይበ​ት​ነ​ዋል፤
ውር​ጭም ከረጋ በኋላ እንደ ሻፎ የብ​ርሌ ስባሪ ብልጭ ይላል።
20የቀ​ዘ​ቀ​ዘው የም​ሥ​ራቅ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሰ​ሜን” ይላል። ነፋ​ስም ይነ​ፍ​ሳል፤
ውር​ጩም በውኃ ላይ ይረ​ጋል፤
በው​ኃው መከ​ማቻ ላይም ይቆ​ማል፤
እንደ ብረት ልብ​ስም በውኃ ላይ ይኖ​ራል፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ውኃ​ውም እንደ ብረት ልብስ ይለ​ብ​ሰ​ዋል” ይላል። ይሸ​ፍ​ና​ታ​ልም።
21ተራ​ራ​ውን ይበ​ላል፤
ምድረ በዳ​ው​ንም ያቃ​ጥ​ላል፤
ሣሩ​ንም እንደ እሳት ያቃ​ጥ​ለ​ዋል።
22የሰው ሁሉ ፈውስ ፈጥኖ የሚ​መጣ ካፊያ ነው፤
ዝና​ብም ወደ ምድር በወ​ረደ ጊዜ ደስ ያሰ​ኛል።
23በእ​ር​ሱም ምክር ጥልቁ ይደ​ር​ቃል፤
በዚ​ያም ደሴ​ቶ​ችን ተከለ።
24በባ​ሕ​ርም የሚ​ሄዱ ሰዎች መከ​ራ​ዋን ይና​ገ​ራሉ፥
እኛም ሰም​ተን እና​ደ​ን​ቃ​ለን።
25በዚ​ያም ሥራው ፈጽሞ ድንቅ ነው።
ከብ​ትን መግ​ዛት በየ​ወ​ገኑ ነው።
26ለበጎ መዓ​ዛም ከእ​ርሱ መሥ​ዋ​ዕት ይሠ​ዋ​ለ​ታል፤
በቃ​ሉም ሁሉ ይደ​ረ​ጋል።
27ብዙ ነገ​ርን እን​ና​ገ​ራ​ለን፤ መፈ​ጸ​ምም አን​ች​ልም፤
ነገር ግን የነ​ገሩ ሁሉ መጨ​ረሻ እርሱ ብቻ ነው።
28ከፍ​ጥ​ረት ሁሉ እርሱ ይበ​ል​ጣ​ልና፤
እር​ሱን ማመ​ስ​ገን ምን ያህል እን​ች​ላ​ለን?
29እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ስ​ፈራ ነው፤
እጅ​ግም ታላቅ ነው፤ ኀይ​ሉም ድንቅ ነው።
30ጨር​ሳ​ችሁ ማመ​ስ​ገ​ንን አት​ጠ​ነ​ቅ​ቁ​ምና፤
የተ​ቻ​ላ​ች​ሁን ያህል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፤
እርሱ ግን ከዚህ ሁሉ በላይ ነው።
በፍ​ጹም ኀይ​ላ​ች​ሁም አግ​ን​ኑት፤
አት​ደ​ር​ሱ​በ​ት​ምና እር​ሱን ማመ​ስ​ገ​ንን ቸል አት​በሉ።
31እር​ሱን አይቶ የሚ​ነ​ግ​ረን ማን ነው?
እንደ ገና​ና​ነ​ቱስ መጠን ማን ያገ​ነ​ዋል?
32የማ​ይ​ታ​የው ከዚህ የሚ​በ​ል​ጠው ፍጥ​ረቱ ብዙ ነው፤
ነገር ግን ያየ​ነው ፍጥ​ረቱ ጥቂት ብቻ ነው።
33እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁሉን ፈጥ​ሯ​ልና፤
ለጻ​ድ​ቃ​ንም ጥበ​ብን ሰጣ​ቸው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ