መጽ​ሐፈ ሲራክ 48

48
ነቢዩ ኤል​ያስ
1ነቢዩ ኤል​ያ​ስም እንደ እሳት ተነሣ፥
ቃሉም እንደ ነበ​ል​ባል ያቃ​ጥል ነበር።
2ረኃ​ብ​ንም አመ​ጣ​ባ​ቸው፤
በቅ​ን​ዓ​ቱም አሳ​ነ​ሳ​ቸው።
3በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ሰማ​ይን ዘጋው፤
ከሰ​ማ​ይም እሳ​ትን ሦስት ጊዜ አወ​ረደ።
4ኤል​ያስ ሆይ፥ በተ​አ​ም​ራ​ትህ እን​ዴት ከበ​ርህ!
እን​ዳ​ን​ተስ የተ​መካ ማን​ነው?
5በል​ዑል ቃል ከሞቱ ሰዎች ለይቶ ምው​ትን ከመ​ቃ​ብር ያስ​ነሣ ማን​ነው?
6ነገ​ሥ​ታ​ቱን ወደ ሞት፥
የከ​በሩ ሰዎ​ቹ​ንም ከአ​ል​ጋ​ቸው ያወ​ረ​ዳ​ቸው ማን​ነው?
7በሲና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተግ​ሣጽ፥
በኮ​ሬ​ብም የበ​ቀ​ልን ፍርድ የሰማ ማን​ነው?
8ይበ​ቀሉ ዘንድ ነገ​ሥ​ታ​ቱን፥
ከእ​ር​ሱም ቀጥሎ ይተኩ ዘንድ ነቢ​ያ​ትን የቀ​ባ​ቸው ማን​ነው?
9በእ​ሳት ሠረ​ገ​ላና በእ​ሳት ፈረስ
ወደ ሰማይ የወጣ ማን​ነው?
10መቅ​ሠ​ፍቱ ከመ​ው​ረዱ አስ​ቀ​ድሞ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቍጣ ይመ​ልስ ዘንድ፥
የአ​ባ​ት​ንም ልብ ወደ ልጅ ይመ​ልስ ዘንድ፤
የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንም ወገ​ኖች ያጸ​ና​ቸው ዘንድ በተ​ወ​ሰነ ዘመን የተ​ጻ​ፈ​ለት ማን​ነው?
11የሚ​ያ​ው​ቁ​ህና በፍ​ቅ​ርህ ያጌጡ#አን​ዳ​ንድ የግ​ሪክ ዘርዕ “በፍ​ቅ​ርህ የሞቱ” ይላል። ሰዎች ብፁ​ዓን ናቸው፥
እኛም ስለ አንተ በሕ​ይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን።
ነቢዩ ኤል​ሳዕ
12በእ​ሳት ሠረ​ገላ ወደ ላይ የወጣ ኤል​ያስ ነው፤
ከእ​ር​ሱም መን​ፈስ የተ​መላ ኤል​ሳዕ ነበረ፤
በዘ​መ​ኑም አለ​ቆች አላ​ስ​ደ​ነ​ገ​ጡ​ትም፤
ማንም እር​ሱን የተ​ቋ​ቋ​መው አል​ነ​በ​ረም።
13ከነ​ገ​ሩም ሁሉ የተ​ሳ​ነው አል​ነ​በ​ረም፤
ከሞ​ተም በኋላ በድኑ ትን​ቢ​ትን ተና​ገረ።
14በሕ​ይ​ወ​ቱም ሳለ ድንቅ ተአ​ም​ራ​ትን አደ​ረገ፤
በሞ​ቱም ሥራው ድንቅ ነበረ።
15ከዚ​ህም ሁሉ ጋር ሕዝቡ ንስሓ አል​ገ​ቡም፤
ከሀ​ገ​ራ​ቸ​ውም ተማ​ር​ከው እስ​ኪ​ሄዱ ድረስ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን አል​ተ​ዉም፤
በሀ​ገ​ሩም ሁሉ ተበ​ተኑ፤
ከሕ​ዝ​ቡም ጥቂት ሰዎች ቀሩ፤
ገዢም ከዳ​ዊት ቤት ቀረ።
16ከእ​ነ​ር​ሱም ደግ ሥራ የሠሩ ነበሩ፤
ኀጢ​አ​ት​ንም ያበ​ዟት ነበሩ።
ንጉሡ ሕዝ​ቅ​ያስ
17ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ከተ​ማ​ውን አጸና
በመ​ካ​ከ​ል​ዋም ውኃን አስ​ገባ፤
ዓለ​ቱ​ንም በብ​ረት ቈፈረ፤ የውኃ መስኖ አሠራ።
18ሰና​ክ​ሬ​ምም በዘ​መኑ ዘመተ፤
ራፋ​ስ​ቂ​ስ​ንም ላከው፤
ወደ እር​ሱም ሄዶ በጽ​ዮን ላይ እጁን አነሣ፤ ታበየ፤
አፉ​ንም ከፍ ከፍ አድ​ርጎ ተና​ገረ።
19ያን ጊዜም ልቡ​ና​ቸው ደነ​ገ​ጠ​ባ​ቸው፤
እጃ​ቸ​ውም ዛለ፤ እን​ደ​ም​ት​ወ​ልድ ሴትም ምጥ ያዛ​ቸው።
20ይቅር ባይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ለመ​ኑት፤
እጃ​ቸ​ው​ንም ወደ እርሱ አነሡ፤
ቅዱ​ሱም ከሰ​ማይ ፈጥኖ ሰማ​ቸው፤
በኢ​ሳ​ይ​ያ​ስም እጅ አዳ​ና​ቸው።
21የአ​ሦ​ር​ንም#ግእዝ “ፋርስ” ይላል። ሠራ​ዊት አጠፋ፤
መል​አ​ኩም አጠ​ፋ​ቸው።
22ሕዝ​ቅ​ያስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘው ሥራ ሠር​ት​ዋ​ልና፤
በራ​እዩ ታላ​ቅና ታማኝ የነ​በ​ረው ነቢዩ ኢሳ​ይ​ያ​ስም እን​ዳ​ዘ​ዘው
የአ​ባቱ የዳ​ዊ​ትን መን​ገድ አጽ​ን​ት​ዋ​ልና።
23ፀሐ​ይም በዘ​መኑ ከመ​ሄድ ወደ ኋላ ተመ​ለ​ሰች፤
ለን​ጉ​ሡም ዘመን ጨመ​ረ​ለት።
24በታ​ላቅ መን​ፈ​ስም በመ​ጨ​ረሻ የሚ​ሆ​ነ​ውን አየ፤
በጽ​ዮን የሚ​ያ​ለ​ቅ​ሱ​ት​ንም አጽ​ና​ና​ቸው።
25ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ የሚ​ሆ​ነ​ውን፥
የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም ሳይ​ሆን ተና​ገረ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ