መጽ​ሐፈ ሲራክ 6

6
1ጠላት ከም​ት​ሆን ወዳጅ ሁን፤
የክፉ ስም ፍጻ​ሜው ስድ​ብና ውር​ደት ነውና፤
ምላሱ ሁለት የሆነ ኀጢ​አ​ተኛ ሰውም እን​ዲህ ነው።
2ከል​ቡ​ናህ ባነ​ቃ​ኸ​ውም ምክር ራስ​ህን ከፍ ከፍ አታ​ድ​ርግ፤
አን​በሳ ላምን እን​ደ​ሚ​ነ​ጣ​ጠቅ ሰው​ነ​ት​ህን እን​ዳ​ይ​ነ​ጥ​ቋት።
3ቅጠ​ል​ህን ይበ​ላ​ብ​ሃል፥ ፍሬ​ህ​ንም ታጣ​ለህ፤
እንደ ደረቅ እን​ጨ​ትም ይጥ​ል​ሃል።
4ክፉ ሰው​ነት ገን​ዘብ ያደ​ረ​ጋ​ትን ሰው ታጠ​ፋ​ዋ​ለች፤
ጠላ​ቱ​ንም በእ​ርሱ የጨ​ከነ ታደ​ር​ገ​ዋ​ለች።
እው​ነ​ተ​ኛና እው​ነ​ተኛ ያል​ሆነ ጓደ​ኝ​ነት
5ልዝብ አን​ደ​በት ወን​ድ​ማ​ማ​ች​ነ​ትን ያበ​ዛል፤
ልዝብ አፍም ወዳ​ጅን ያበ​ዛል።
6ብዙ ሰዎች ወዳ​ጆች ይሁ​ኑህ፤
ነገር ግን ከብ​ዙ​ዎቹ አንዱ ምክ​ር​ህን የም​ት​ገ​ል​ጥ​ለት ይሁን።
7ወዳጅ ብታ​በጅ በች​ግ​ርህ ወራት ወዳጅ አብጅ።
ፈጥ​ነ​ህም እም​ነት አት​ጣ​ል​በት፤
8ለጥ​ቂት ቀን የሚ​ሆን ወረ​ተኛ ወዳጅ አለና፤
በመ​ከ​ራ​ህም ጊዜ ከአ​ንተ ጋራ አይ​ታ​ገ​ሥም።
9ጠላት የሚ​ሆ​ን​ህና፥ የሚ​ሰ​ድ​ብህ፥
ሰው​ረህ የሠ​ራ​ኸ​ውን ኀጢ​አ​ት​ህ​ንም የሚ​ገ​ል​ጥ​ብህ ወዳጅ አለ።
10ስለ ማዕ​ድ​ህም የሚ​ወ​ድህ ወዳጅ አለ፤
እር​ሱም ከአ​ንተ ጋራ አይ​ኖ​ርም፥
በተ​ቸ​ገ​ር​ህም ጊዜ ይለ​ይ​ሃል።
11ባለ​ጸጋ በሆ​ንህ ጊዜ እን​ዳ​ንተ ይሆ​ናል፤
ቤተ ሰብ​ህ​ንም ይገ​ዛል።
12ብት​ቸ​ገር ግን እርሱ ባላ​ጋ​ራህ ይሆ​ናል፤
እን​ዳ​ታ​የ​ውም ይሰ​ወ​ር​ሃል።
13ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ራቅ፥
ወዳ​ጆ​ች​ህ​ንም ተጠ​ባ​በ​ቃ​ቸው።
14የታ​መነ ወዳጅ እንደ ጸና አላ​ባሽ አግሬ ጋሻ ነው፤
እር​ሱን ያገኘ ሰው ድልብ አገኘ።
15ለታ​መነ ወዳጅ ለውጥ የለ​ውም፤
ለደ​ግ​ነ​ቱም ሚዛን የለ​ውም።
16የታ​መነ ወዳጅ የሕ​ይ​ወት መድ​ኀ​ኒት ነው፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ፈሩ ያገ​ኙ​ታል።
17እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው ወዳ​ጅ​ነ​ቱን ያጸ​ናል፤
ባል​ን​ጀ​ራው እንደ እርሱ ይሆ​ነ​ዋ​ልና።
የጥ​በብ በረ​ከት
18ልጄ ሆይ፥ በሕ​ፃ​ን​ነ​ትህ ጥበ​ብን ምረ​ጣት፤
እስ​ክ​ታ​ረ​ጅም ድረስ ታገ​ኛ​ታ​ለህ።
19እን​ደ​ሚ​ያ​ር​ስና እን​ደ​ሚ​ዘራ ሰው ወደ እር​ስዋ ሂድ፤
የተ​ባ​ረከ ፍሬ​ዋ​ንም ጠብቅ፤
ስለ እር​ስዋ በመ​ሥ​ራት ጥቂት ትደ​ክ​ማ​ለህ፤
ነገር ግን ፈጥ​ነህ ፍሬ​ዋን ትበ​ላ​ለህ።
20በሰ​ነ​ፎች ዘንድ ፈጽማ ጐፃ​ጕፅ ናት፤
አእ​ምሮ በሌ​ለው ሰውም አታ​ድ​ርም።
21የፈ​ተና ድን​ጋይ አን​ሥ​ተው በተ​ሸ​ከ​ሙት ጊዜ እን​ዲ​ከ​ብድ፥
እን​ደ​ዚሁ ትከ​ብ​ደ​ዋ​ለች፤ ፈጥ​ኖም ይጥ​ላ​ታል።
22ጥበ​ብስ እንደ ስሟ ናት፤
ብዙ ሰዎ​ችም የሚ​ያ​ው​ቋት አይ​ደ​ሉም።
23ልጄ ሆይ፥ ስማኝ፥ በም​ክ​ሬም ጽና፤
ምክ​ሬ​ንም አታ​ቃ​ልል።
24እግ​ሮ​ች​ህን ወደ ቀም​በ​ርዋ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ወደ እግር ብረቷ” ይላል። አግባ፤
ዛን​ጅ​ር​ዋ​ንም ባን​ገ​ትህ እሰር።
25ጫን​ቃ​ህን ዝቅ አድ​ር​ገህ ተሸ​ከ​ማት፤
በእ​ግር ብረ​ት​ዋም አት​በ​ሳጭ።
26በፍ​ጹም ነፍ​ስህ ወደ እርሷ ተሰ​ማራ፥
በፍ​ጹም ኀይ​ል​ህም መን​ገ​ድ​ዋን ጠብቅ።
27ፍለ​ጋ​ዋን ተከ​ተል፥ ፈል​ጋት፤ ታገ​ኛ​ታ​ለ​ህም።
ያዛት፥ አት​ተ​ዋ​ትም።
28በፍ​ጻ​ሜ​ህም ዕረ​ፍ​ትን ታገ​ኛ​ለህ፤
ደስ​ታም ይሆ​ን​ሃል።
29እግር ብረ​ት​ዋም እንደ ጽኑ ጋሻ ይሆ​ን​ል​ሃል፤
ዛን​ጅ​ር​ዋም የክ​ብር ልብስ ወደ መሆን ይመ​ለ​ስ​ል​ሃል።
30የዘ​ለ​ዓ​ለም ወርቅ በእ​ርሷ ዘንድ አለና፤
ማሰ​ሪ​ያ​ዋም የሰ​ማ​ያዊ ሐር ጌጥ ይሆ​ን​ሃል።
31እንደ ክብር ልብስ ትለ​ብ​ሳ​ታ​ለህ፥
የደ​ስታ ዘው​ድ​ንም ታቀ​ዳ​ጅ​ሃ​ለች።
32ልጄ ሆይ፥ ብልህ ትሆን ዘንድ ብት​ወ​ድድ፥
ትማ​ርም ዘንድ በል​ቡ​ናህ ብት​ጨ​ክን፥
33ትሰማ ዘንድ ብት​ወ​ድም ታገሥ፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ዕው​ቀ​ትን ታገ​ኛ​ለህ” ይላል።
ጆሮ​ህ​ንም ብታ​ዘ​ነ​ብል ብልህ ትሆ​ና​ለህ።
34በብዙ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ዘንድ ቁም፤
ከእ​ነ​ር​ሱም ዐዋቂ ሰው ብታይ ተከ​ተ​ለው።
35የመ​ጽ​ሐ​ፉን ነገር ሁሉ ፈጥ​ነህ ስማ፤
የጥ​በ​ብም ምሳሌ አይ​ዘ​ን​ጋህ።
36ብልህ ሰው ብታይ ፈጥ​ነህ ወደ እርሱ ሂድ፤
እግ​ር​ህም በደ​ጃፉ መድ​ረክ ይመ​ላ​ለስ።
37የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ዐስብ፤
መጻ​ሕ​ፍ​ቱ​ንም ሁል​ጊዜ አን​ብብ፥
እር​ሱም ልቡ​ና​ህን ያጸ​ና​ዋል፤
ጥበ​ብ​ንም ትወ​ዳት ዘንድ ይሰ​ጥ​ሃል።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ