መሓ​ልየ መሓ​ልይ ዘሰ​ሎ​ሞን 5

5
1እኅቴ ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥
ከር​ቤ​ዬን ከሽ​ቱዬ ጋር ለቀ​ምሁ፥
እን​ጀ​ራ​ዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥
የወ​ይን ጠጄን ከወ​ተቴ ጋር ጠጣሁ።
ባል​ን​ጀ​ሮች በሉ፥ ጠገ​ቡም፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. 2ኛ መደብ ነው።
የወ​ን​ድ​ሞች ልጆች ጠጡ፥
ሰከ​ሩም፥ ልባ​ቸው የጠፋ ነውና።
2እኔ ተኝቼ ነበር፥ ልቤ ግን ነቅታ ነበር፤
ልጅ ወን​ድሜ ቃል ደጅ እየ​መታ መጣ፥
እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደ​ም​ደ​ሚ​ያዬ ሆይ፥
በራሴ ጠል፥ በቍ​ን​ዳ​ላ​ዬም የሌ​ሊት ነጠ​ብ​ጣብ
ሞል​ቶ​በ​ታ​ልና ክፈ​ች​ልኝ።
3ቀሚ​ሴን አወ​ለ​ቅሁ፥ እን​ዴት እለ​ብ​ሰ​ዋ​ለሁ?
እግ​ሬን ታጠ​ብሁ፥ እን​ዴት አሳ​ድ​ፈ​ዋ​ለሁ?
4ልጅ ወን​ድሜ እጁን በቀ​ዳዳ ሰደደ፥
አን​ጀ​ቴም ስለ እርሱ ታወ​ከች።
5ለልጅ ወን​ድሜ እከ​ፍ​ት​ለት ዘንድ ተነ​ሣሁ፤
እጆች በደጁ መወ​ር​ወ​ሪያ ላይ ከር​ቤን አፈ​ሰሱ፥
ጣቶች ፈሳ​ሹን ከርቤ አን​ጠ​ባ​ጠቡ።
6ለልጅ ወን​ድሜ ከፈ​ት​ሁ​ለት፥
ልጅ ወን​ድሜ ግን ሂዶ ነበር።
ነፍሴ ከቃሉ የተ​ነሣ ደነ​ገ​ጠች፤
ፈለ​ግ​ሁት፥ አላ​ገ​ኘ​ሁ​ትም፤
ጠራ​ሁት፥ አል​መ​ለ​ሰ​ል​ኝም።
7ከተ​ማ​ዪ​ቱን የሚ​ዞ​ሩት ጠባ​ቂ​ዎች አገ​ኙኝ፤
መቱኝ፥ አቈ​ሰ​ሉ​ኝም፤
ቅጥር ጠባ​ቂ​ዎ​ችም የዐ​ይነ ርግብ መሸ​ፈ​ኛ​ዬን ከራሴ ላይ ወሰ​ዱት።
8እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥
በም​ድረ በዳ ኀይ​ልና ጽን​ዐት አም​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤
ልጅ ወን​ድ​ሜን ያገ​ኛ​ች​ሁት እንደ ሆነ፥
እኔ ከፍ​ቅር የተ​ነሣ መታ​መ​ሜን ትነ​ግ​ሩት ዘንድ።
9አንቺ በሴ​ቶች ዘንድ የተ​ዋ​ብሽ ሆይ፥
ከወ​ን​ድ​ሞች ልጆች ይልቅ ልጅ ወን​ድ​ምሽ ማን ነው?
ይህን ያህል መሐላ አም​ለ​ሽ​ና​ልና
ከወ​ን​ድ​ሞች ልጆች ይልቅ ልጅ ወን​ድ​ምሽ ማን ነው?
10ወን​ድሜ ነጭና ቀይ ነው፥
ከአ​እ​ላፍ የተ​መ​ረጠ ነው።
11ራሱ ምዝ​ምዝ ወርቅ ነው፤
ቈን​ዳ​ላው የተ​ዝ​ረ​ፈ​ረፈ ነው፥
እንደ ቍራ ጥቍ​ረ​ትም ጥቁር ነው።
12ዐይ​ኖቹ በሙሉ የውኃ ኵሬ አጠ​ገብ እን​ዳሉ
በወ​ተት እንደ ታጠቡ በኵሬ ውኃ አጠ​ገብ እንደ ተቀ​መጡ፥
እንደ ርግ​ቦች ናቸው።
13ጕን​ጮቹ ሽቱን የሚ​ያ​ፈ​ስሱ የሽቱ መደብ ናቸው።
ከን​ፈ​ሮቹ እንደ አበ​ቦች ናቸው፥
የሚ​ፈ​ስስ ከር​ቤ​ንም ያን​ጠ​ባ​ጥ​ባሉ።
14እጆቹ የተ​ር​ሴስ ፈርጥ እን​ዳ​ለ​ባ​ቸው እንደ ለዘቡ የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች ናቸው፤
ሆዱ በሰ​ን​ፔር ዕንቍ እን​ዳ​ጌጠ እንደ ዝሆን ጥርስ ነው፥
15እግ​ሮቹ በም​ዝ​ምዝ ወርቅ እንደ ተመ​ሠ​ረቱ
እንደ ዕብነ በረድ ምሰ​ሶ​ዎች ናቸው፤
መልኩ እንደ ሊባ​ኖ​ስና#ግእዝ “ስሂን” ይላል። እንደ ዝግባ ዛፍ የተ​መ​ረጠ ነው።
16ጕሮ​ሮው እጅግ ጣፋጭ ነው፥ ሁለ​ን​ተ​ና​ውም የተ​ወ​ደደ ነው፤
እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥
ልጅ ወን​ድሜ ይህ ነው፥ ወዳ​ጄም ይህ ነው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ