መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን 6
6
1አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥
ከአንቺ ጋር እንፈልገው ዘንድ ልጅ ወንድምሽ ወዴት ሄደ?
ልጅ ወንድምሽስ ወዴት ፈቀቅ አለ?
2ልጅ ወንድሜ በገነቱ መንጋውን ይጠብቅ ዘንድ፥
አበባውንም ይሰበስብ ዘንድ
ወደ ሽቱ መደብ ወደ ገነቱ ወረደ።
3እኔ የልጅ ወንድሜ ነኝ፥ ልጅ ወንድሜም የእኔ ነው፤
በሱፍ አበባ መካከል መንጋውን ያሰማራል።
4ወዳጄ ሆይ፥ እንደ ቴርሳ ውብ ነሽ፥
እንደ ኢየሩሳሌምም ያማርሽ ነሽ፤
ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት ታስፈርያለሽ።
5ዐይኖችሽን ከፊቴ መልሺ፤ እነርሱ አስፈርተውኛልና፤
ጠጕርሽ ከገለዓድ እንደ ታየ እንደ ፍየል መንጋ ነው።
6ጥርሶችሽ ታጥበው እንደ ወጡ
ሁሉም መንታ እንደ ወለዱ
ከእነርሱም መካን እንደሌለባቸው መንጎች ናቸው።
ከንፈሮችሽ እንደ ቀይ ሐር ናቸው፥
ቃልሽ ያማረ ነው።
7ከዝምታሽ በቀር ጕንጮችሽ
እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው።
8ስድሳ ንግሥታት፥ ሰማንያም ቁባቶች
ቍጥር የሌላቸውም ቈነጃጅት አሉ።
9ርግቤ መደምደሚያዬም አንዲት ናት፤
ለእናቷ አንዲት ናት፥ ለወለደቻትም የተመረጠች ናት።
ቈነጃጅትም አይተው አሞገሱአት፥
ንግሥታትና ቁባቶችም አመሰገኑአት።
10ይህች እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ፥
እንደ ጨረቃ የተዋበች እንደ ፀሓይም የጠራች፥
ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ማን ናት?
11ልጅ ወንድሜ#“ልጅ ወንድሜ” የሚለው በዕብ. እና በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።የወንዙን ዳር ልምላሜ ያይ ዘንድ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አይ ዘንድ ... ወረድሁ” ይላል።
ወይኑ አብቦ ሮማኑም አፍርቶ እንደ ሆነ ይመለከት ዘንድ
ወደ ገውዝ ገነት ወረደ።
12በዚያ ጡቶችን እሰጥሃለሁ፥
ሰውነቴም አላወቀችም፥
እንደ አሚናዳብ ሰረገላ አደረገኝ አለች። ብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “አይ ዘንድ ... ወረድሁ” ይላል።
ወይኑ አብቦ ሮማኑም አፍርቶ እንደ ሆነ ይመለከት ዘንድ
ወደ ገውዝ ገነት ወረደ።
13በዚያ ጡቶችን እሰጥሃለሁ፥
ሰውነቴም አላወቀችም፥
እንደ አሚናዳብ ሰረገላ አደረገኝ አለች።
Currently Selected:
መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን 6: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ