መጽ​ሐፈ ጥበብ 5

5
1ያን​ጊዜ ጻድቁ፦ መከራ ባጸ​ኑ​በ​ትና ድካ​ሙን በካዱ፥ ነገ​ሩ​ንም በናቁ ሰዎች ፊት በብዙ መገ​ለጥ ይቆ​ማል። 2በግ​ር​ማና በክፉ ማስ​ፈ​ራ​ራት ሆኖ ባዩት ጊዜ ይታ​ወ​ካሉ፤ ድንቅ ስለ​ሚ​ሆን ደኅ​ን​ነ​ቱም ይደ​ነ​ቃሉ። 3እየ​ተ​ጸ​ጸ​ቱና በተ​ጨ​ነቀ መን​ፈስ እየ​ጮኹ እርስ በር​ሳ​ቸው ይና​ገ​ራሉ፦ እን​ዲ​ህም ይላሉ፥ “ቀድሞ በኛ በሰ​ነ​ፎች ዘንድ መሣ​ቂ​ያና ማሽ​ሟ​ጠጫ የሆ​ነው፥ 4ሥራ​ውን ስን​ፍና፥ ሞቱ​ንም የተ​ናቀ ያደ​ረ​ግ​ን​በት ይህ ነውን? 5እን​ዴት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ሆነ? ርስ​ቱስ እን​ዴት ለቅ​ዱ​ሳን ሆነች? 6ስለ​ዚህ ከቀና መን​ገድ ወጥ​ተን ስተ​ናል፥ የጽ​ድቅ ብር​ሃ​ንም አል​ተ​ገ​ለ​ጠ​ል​ንም፥ ፀሐ​ይም አል​ወ​ጣ​ል​ንም። 7በደ​ል​ንና ጥፋ​ትን በመ​ን​ገ​ዳ​ችን ሞላን፤ በም​ድረ በዳም ሄድን፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መን​ገድ አላ​ወ​ቅ​ንም።
8“ትዕ​ቢት ምን ጠቀ​መን? ከት​ዕ​ቢት ጋር ያለ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትስ ምን አመ​ጣ​ልን? 9ይህ ሁሉ እንደ ጥላ ኀላፊ ነው፤ ፈጥ​ኖም እን​ደ​ሚ​ሄድ ወሬ ነው። 10በባ​ሕር ላይ እን​ደ​ሚ​ሄድ፥ ውኃም በማ​ዕ​በሉ እን​ደ​ሚ​ነ​ጥ​ቀው፥ ያለ​ፈ​በት ፍለ​ጋው እን​ደ​ማ​ይ​ገኝ፥ በማ​ዕ​በ​ሉም መካ​ከል አካሉ የሄ​ደ​በት መን​ገድ እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቅ መር​ከብ፥ 11በአ​የር ላይ የሚ​በ​ርር ዎፍ የሄ​ደ​በት ፍለ​ጋው እን​ደ​ማ​ይ​ገኝ፥ በበ​ረረ ጊዜ ቀላ​ሉን አየር እየ​ከ​ፈለ ፈጥኖ ይሄ​ዳ​ልና፥ ክን​ፉ​ንም እያ​ር​ገ​በ​ገበ፥ ፈጥኖ ይበ​ር​ራ​ልና ከሄ​ደም በኋላ በነ​ፋሱ ውስጥ ያለ​ፈ​በት ምል​ክቱ እን​ደ​ማ​ይ​ገኝ፥ 12ይህም ባይ​ሆን የተ​ወ​ረ​ወረ ፍላፃ ሰን​ጥ​ቆት ያለ​ፈው አየር ተመ​ልሶ እን​ደ​ሚ​ገ​ጥም፥ በአ​የር ውስጥ የሄ​ደ​በ​ትም እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቅ፥ 13እኛም እን​ዲሁ ነን፤ በተ​ወ​ለ​ድን ጊዜ ጠፋን። በክ​ፋ​ታ​ችን ጠፋን እንጂ በጎ ምል​ክ​ትን እና​ሳይ ዘንድ አል​ተ​ገ​ባ​ንም።”
14የክ​ፉ​ዎች ሰዎች ተስ​ፋ​ቸው ነፋስ እን​ደ​ሚ​በ​ት​ነው ትቢያ፥ በነ​ፋስ ቀልጦ እን​ደ​ሚ​ጠፋ ረቂቅ ውርጭ፥ በነ​ፋ​ስም ተበ​ትኖ እን​ደ​ሚ​ጠፋ ጢስ፥ አንድ ቀንም አድሮ እን​ደ​ሚ​ሄድ መጻ​ተኛ ስም አጠ​ራር ነው።
ጻድ​ቃን የሚ​ያ​ገ​ኙ​ት​ዋጋ
15ጻድ​ቃን ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራሉ፤ ዋጋ​ቸ​ውም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የጸና ነው፤ ጥበ​ቃ​ቸ​ውም በል​ዑል ዘንድ ነው። 16ስለ​ዚ​ህም የክ​ብር መን​ግ​ሥ​ት​ንና ጌጥ ያለው አክ​ሊ​ልን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ይቀ​በ​ላሉ፤ በቀኙ ይሰ​ው​ራ​ቸ​ዋ​ልና፥ በክ​ን​ዱም ይረ​ዳ​ቸ​ዋ​ልና። 17ፍጹም የሆነ የቅ​ን​ዐ​ቱን ጦር መሣ​ሪያ ይይ​ዛል፤ ጠላ​ቶ​ቹ​ንም ለመ​በ​ቀል ፍጥ​ረ​ቱን የጦር መሣ​ሪያ ያደ​ር​ጋ​ታል። 18የጽ​ድቅ ጥሩ​ር​ንም ይለ​ብ​ሳል፥ ማድ​ላት የሌ​ለ​በት የፍ​ርድ ራስ ቍር​ንም ይቀ​ዳ​ጃል። 19የማ​ይ​ሸ​ነፍ የእ​ው​ነት ጋሻ​ንም ይይ​ዛል። 20መዓ​ቱ​ንም እን​ደ​ሚ​ቈ​ርጥ ሰይፍ ይስ​ላል፤ ዓለ​ምም ከእ​ርሱ ጋር ሆኖ አላ​ዋ​ቂ​ዎ​ችን ይዋ​ጋል። 21ፈጥኖ ያገ​ኛ​ቸው ዘንድ በአ​ሳ​ቾች ሰዎች ላይ የመ​ብ​ረ​ቆቹ ድል ነጎድ በቀ​ጥታ ይሄ​ድ​ባ​ቸ​ዋል። መል​ካም ሆኖ ከተ​ገ​ተረ ቀስት እን​ደ​ሚ​ወ​ረ​ወር ፍላጻ ከደ​መ​ና​ዎች ውስጥ ወደ ዓላ​ማ​ቸው ይወ​ረ​ወ​ራሉ ። 22ከመ​ዓቱ ድል ነጎድ ደን​ጊ​ያም ፈጥኖ በረ​ዶን ያወ​ር​ዳል፤ የባ​ሕ​ሩም ውኃ በእ​ነ​ርሱ ላይ ይበ​ሳ​ጭ​ባ​ቸ​ዋል፤ ፈሳ​ሾ​ችም ይነ​ዋ​ወ​ጣሉ፤ ፈጥ​ነ​ውም ይከ​ቧ​ቸ​ዋል። 23ኀይል ያለው ነፋ​ስም ይቃ​ወ​ማ​ቸ​ዋል፤ እንደ ነፋ​ስም ያደ​ር​ቃ​ቸ​ዋል፤ ኀጢ​አት ምድ​ሩን ሁሉ ታጠ​ፋ​ለ​ችና፥ ክፉም መሥ​ራት የኀ​ያ​ላ​ኑን ዙፋን ይገ​ለ​ብ​ጣ​ልና ይበ​ት​ና​ቸ​ዋል።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ