ኦሪት ዘጸአት 1
1
እስራኤላውያን በግብፅ የደረሰባቸው ግፍ
1ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት የእስራኤል ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፤ ሰው ሁሉ ከቤተ ሰቡ ጋር ገባ። 2ሮቤል፥ 3ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፥ 4ብንያም፥ ዳን፥ ንፍታሌም፥ ጋድ፥ አሴር። 5ከያቆብ ጉልበት የወጡት ሰዎች ሁሉ ሰባ ነፍሶች ነበሩ፤ ዮሴፍም አስቀድሞ በግብፅ ነበር። 6ዮሴፍም ሞተ፤ ወንድሞቹም፤ ያም ትውልድ ሁሉ። 7የእስራኤልም ልጆች ፍሬን አፈሩ፤ እጅግም በዙ፤ ተባዙም፤ እጅግም ጸኑ፤ ምድሪቱም በእነርሱ ሞላች።
8በግብም ዮሴፍን ያላወቀ አዲስ ንጉሥ ተነሣ። 9እርሱም ሕዝቡን፦ “እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ሕዝብ ከእኛ ይልቅ በዝተዋል በርትተውማል፤ 10እንዳይበዙ፥ ሰልፍም በተነሳብን ጊዜ ጠላቶቻችንን አግዘው እንዳይወጉን ከምድሪቱም እንዳይወጡ፥ ኑ! እንጠበብባቸው፤” አለ። 11በብርቱ ሥራም ያስጨንቁአቸው ዘንድ ግብር አስገባሪዎችን ሾመባቸው፤ ለፈርዖንም ፊቶምንና ራምሴን ጽኑ ከተሞች አድርገው ሠሩ። 12ነገር ግን እንዳስጨነቁአቸው መጠን እንዲሁ በዙ፤ እጅግም ጸኑ፤ ከእስራኤልም ልጆች የተነሣ ተጸይፈዋቸው ነበር። 13ግብፃውያንም የእስራኤልን ልጆች በመከራ ገዙአቸው። 14በጽኑ ሥራ፥ በጭቃ፥ በጡብም፥ በእርሻም ሥራ ሁሉ፥ በመከራም በሚያሠሩአቸው ሥራ ሁሉ፥ ሕይወታቸውን ያስመርሩአቸው ነበር።
15የግብፅም ንጉሥ አንዲቱ ሲፓራ ሁለተኛይቱም ፉሐ የሚባሉትን የዕብራውያንን አዋላጆች እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ 16“እናንተ የዕብራያንን ሴቶች ስታዋልዱ፥ ለመውለድ እንደደረሱ ባያችሁ ጊዜ፥ ወንድ ቢሆን ግደሉት፤ ሴት ብትሆን ግን በሕይወት ትኑር።” 17አዋላጆች ግን እግዚአብሔርን ፈሩ፤ የግብፅ ንጉሥም እንዳዘዛቸው አላደረጉም፤ ወንዶቹን ሕፃናትንም አዳኑአቸው። 18የግብፅም ንጉስ አዋ“ላጆችን ጠርቶ፦ “ለምን እንዲህ አደረጋችሁ?” ወንዶቹን ሕፃናትንስ ለምን አዳናችሁ?” አላቸው። 19አዋላጆቹም ፈርዖንን፦ “የዕብራውያን ሴቶች እንደ ግብፅ ሴቶች ስላልሆኑ፥ እነርሱ ጠንካሮች ናቸውና አዋላጆች ሳይገቡ ስለሚወልዱ ነው” አሉት። 20እግዚአብሔርም ለአዋላጆች መልካም አደረገላቸው፤ ሕዝቡም በዛ፤ እጅግም በረታ። 21እንዲህም ሆነ፤ አዋላጆች እግዚአብሔርን ስለ ፈሩ ቤተሰብን ሰጣቸው። 22ፈርዖንም፦ “የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ወንዝ ጣሉት፤ ሴትን ልጅ ሁሉ ግን በሕይወት አድኑአት፤” ብሎ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘጸአት 1: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ