ኦሪት ዘጸአት 7
7
1እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ “እይ፤ እኔ ለፈርዖን አምላክ አድርጌሃለሁ፤ ወንድምህም አሮን ነቢይ ይሆንልሃል። 2ያዘዝሁህን ነገር ሁሉ አንተ ትነግረዋለህ፤ ወንድምህም አሮን የእስራኤልን ልጆች ከአገሩ ይለቅቅ ዘንድ ከፈርዖን ጋር ይናገራል። 3እኔም የፈርዖንን ልብ አጸናለሁ፤ በግብፅ ምድርም ድንቄንና ተአምራቴን አበዛለሁ። 4ፈርዖንም አይሰማችሁም፤ እጄንም በግብፅ ላይ አደርጋለሁ፤ ሠራዊቴንም የእስራኤልን ልጆች ሕዝቤን በታላቅ ፍርድ ከግብፅ አገር አወጣለሁ። 5ግብፃውያንም፥ እጄን በግብፅ ላይ በዘረጋሁ ጊዜ፥ የእስራኤልንም ልጆች ከመካከላቸው ባወጣሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆነሁ ያውቃሉ።” 6ሙሴና አሮንም እንዲህ አደረጉ፤ እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ። 7ፈርዖንንም በተናገሩት ጊዜ ሙሴ የሰማንያ ዓመት ሰው ነበር፤ አሮንም የሰማኒያ ሦስት ዓመት ሰው ነበር። 8እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ሲል ተናገራቸው፦ 9“ፈርዖን፦ ‘ተአምራትን አሳዩኝ፤’ ሲላችሁ፥ አሮንን፦ ‘በትርህን ወስደህ እባብ እንድትሆን በፈርዖን ፊት ጣላት’ በለው”። 10ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፤ እግዚአብሔርም እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ አሮንም በትሩን በፈርዖንና በባሮቹ ፊት ጣለ፤ እባብም ሆነች። 11ፈርዖንም ጠቢባንንና መተተኞችን ጠራ፤ የግብፅም ጠንቍዮች በአስማታቸው እንዲሁ ደግሞ አደረጉ። 12እያንዳንዳቸውም በትራቸውን ጣሉ፤ እባቦችም ሆኑ፤ የአሮን በትር ግን በትራቸውን ዋጠች። 13እግዚአብሔር እንደ ተናገረ፥ የፈርዖን ልብ ጸና፤ አልሰማቸውምም።
ግብፅ በተአምራዊ መቅሠፍት እንደተመታች
1) ውሃው ወደ ደም እንደተለወጠ
14እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ “የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ ሕዝቡንም ለመልቀቅ እንቢ አለ። 15ማልደህ ወደ ፈርዖን ሂድ፤ እነሆ ወደ ውኃ ይወጣል፤ ትገናኘውም ዘንድ አንተ በወንዝ ዳር ትቆማለህ፤ እባብም ሆና የተለወጠችውን በትር በእጅህ ትወስዳለህ። 16እንዲህም ትለዋለህ፦ ‘የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር፦ በምድረ በዳ እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ’ ብሎ ወደ አንተ ላከኝ፤ እነሆም እስከ ዛሬ አልሰማህም። 17እግዚአብሔር እንዲህ ይላል እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤ እነሆ እኔ የወንዙን ውኃ በእጄ ባለችው በትር እመታለሁ፤ ውኃውም ተለውጦ ደም ይሆናል። 18በወንዙም ያሉት ዓሦች ይሞታሉ፤ ወንዙም ይገማል፤ ግብፃውያንም የወንዙን ውኃ ለመጠጣት ይጠላሉ።’” 19እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “አሮንን፥ ‘በትርህን ውሰድ፤ ደምም እንዲሆኑ በግብፅ ውኆች በወንዞቻቸውም በመስኖቻቸውም በኩሬዎቻቸውም በውኃ ማከማቻዎቻቸውም ሁሉ ላይ እጅህን ዘርጋ’ በለው፤ በግብፅም አገር ሁሉ በእንጨት ዕቃና በድንጋይ ዕቃ ሁሉ ደም ይሆናል።”
20ሙሴና አሮንም እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ በትሩንም አነሣ፤ በፈርዖንና በባሪያዎቹም ፊት የወንዙን ውኃ መታ፤ የወንዙም ውኃ ሁሉ ተለውጦ ደም ሆነ። 21በወንዙም የነበሩ ዓሦች ሞቱ፤ ወንዙም ገማ፤ ግብፃውያንም ከወንዙ ውኃ ይጠጡ ዘንድ አልቻሉም፤ ደሙም በግብፅ አገር ሁሉ ነበረ። 22የግብፅም ጠንቍዮች በአስማታቸው እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔርም እንደተናገረ የፈርዖን ልብ ጸና፤ አልሰማቸውምም። 23ፈርዖንም ተመልሶ ወደ ቤቱ ገባ፤ ይህንም ደግሞ በልቡ አላኖረውም። 24ግብፃውያንም ሁሉ የወንዙን ውኃ ይጠጡ ዘንድ አልቻሉምና በወንዙ አጠገብ ውኃ ሊጠጡ ቆፈሩ። 25እግዚአብሔርም ወንዙን ከመታ በኋላ ሰባት ቀን ተፈጸመ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘጸአት 7: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ