ትንቢተ ሕዝቅኤል 10
10
1እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ በኪሩቤል ራስ ላይ ባለው ጠፈር በላያቸው እንደ ሰንፔር ድንጋይ ያለ እንደ ዙፋን የሚመስል መልክ ተገለጠ። 2በፍታም የለበሰውን ሰው፦ በመንኰራኵሮች መካከል ከኪሩብ በታች ግባ፥ ከኪሩቤልም መካከል ካለው እሳት ፍም እጆችህን ሙላ በከተማይቱም ላይ በትናት ብሎ ተናገረው። እኔም እያየሁ ገባ። 3ሰውዬውም ሲገባ ኪሩቤል በቤቱ ቀኝ በኩል ቆመው ነበር፥ ደመናውም ውስጠኛውን አደባባይ ሞላ። 4የእግዚአብሔር ክብርም ከኪሩቤል ወጥቶ በቤቱ መድረክ ላይ ቆመ ቤቱም በደመናው ተሞላ፥ አደባባዩም በእግዚአብሔር ክብር ፀዳል ተሞላ። 5ሁሉንም የሚችል አምላክ እንደሚናገረው ያለ ጽምፅ እንዲሁ የኪሩቤል ክንፎች ድምፅ እስከ ውጭው አደባባይ ድረስ ተሰማ። 6በፍታም የለበሰውን ሰው፦ ከመንኰራኵሮች ከኪሩቤል መካከል እሳት ውሰድ ብሎ ባዘዘው ጊዜ እርሱ ገብቶ በአንድ መንኰራኵር አጠገብ ቆመ። 7ኪሩብም ከኪሩቤል መካከል እጁን በኪሩቤል መካከል ወዳለው እሳት ዘርግቶ ከዚያ ወሰደ፥ በፍታም በለበሰው ሰው እጅ አኖረው፥ እርሱም ይዞ ወጣ። 8በኪሩቤልም ከክንፎቻቸው በታች የሰው እጅን መሳይ ታየ።
9እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ በኪሩቤል አጠገብ አራት መንኰራኵሮች ነበሩ፥ አንዱ መንኰራኵር በአንዱ ኪሩብ፥ አንዱ መንኰራኵር በአንዱ ኪሩብ አጠገብ ነበረ። የመንኰራኵሮቹም መልክ እንደ ቢረሌ ድንጋይ ነበረ። 10የአራቱም መልክ አንድ ይመስል ነበር፥ መልካቸውም በመንኰራኵር ውስጥ እንዳለ መንኰራኵር ነበር። 11ሲሄዱም በአራቱ ጐድናቸው ይሄዱ ነበር፥ ሲሄዱም አይገላመጡም ነበር፥ ራሱ ወደምታመለክትበት ስፍራ ወደዚያ ይከተሉ ነበር፥ ሲሄዱም አይገላመጡም ነበር። 12ገላቸውም ሁሉ ጀርባቸውም እጃቸውም ክንፋቸውም መንኰራኵሮቹም፥ ለአራቱ የነበሩ መንኰራኵሮች፥ በዙሪያቸው ዓይኖች ተሞልተው ነበር። 13መንኰራኵሮችም እኔ እየሰማሁ ጌልጌል ተብለው ተጠሩ። 14ለእያንዳንዱም አራት አራት ፊት ነበሩት፥ አንደኛው ፊት የኪሩብ ፊት፥ ሁለተኛውም የሰው ፊት፥ ሦስተኛው የአንበሳ ፊት፥ አራተኛውም የንስር ፊት ነበረ።
15ኪሩቤልም ከፍ ከፍ አሉ፥ ይህ በኮቦር ወንዝ ያየሁት እንስሳ ነው። 16ኪሩቤልም ሲሄዱ መንኰራኵሮቹ በአጠገባቸው ይሄዱ ነበር፥ ኪሩቤልም ከምድር ከፍ ከፍ ይሉ ዘንድ ክንፎቻቸውን ሲዘረጉ መንኰራኵሮች ደግሞ ከአጠገባቸው ፈቀቅ አይሉም ነበር። 17ሕይወት ያላቸው የእንስሶች መንፈስ በመንኰራኵሮች ውስጥ ነበረና እነዚህ ሲቆሙ እነዚያ ይቆሙ ነበር፥ እነዚህም ከፍ ከፍ ሲሉ እነዚያ ከእነርሱ ጋር ከፍ ከፍ ይሉ ነበር።
18የእግዚአብሔርም ክብር ከቤቱ መድረክ ላይ ወጥቶ በኪሩቤል ላይ ቆመ። 19ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ዘረጉ እኔም እያየሁ ከምድር ከፍ ከፍ አሉ፥ በወጡም ጊዜ መንኰራኵሮች በአጠገባቸው ነበሩ፥ በእግዚአብሔርም ቤት በምሥራቁ በር መግቢያ ቆሙ፥ የእስራኤልም አምላክ ክብር በላያቸው ላይ ነበረ።
20ይህ በኮበር ወንዝ ከእስራኤል አምላክ በታች ያየሁት እንስሳ ነው፥ ኪሩቤልም እንደ ነበሩ አስተዋልሁ። 21ለእያንዳንዱ አራት አራት ፊት፥ ለእያንዳንዱም አራት አራት ክንፍ ነበሩት፥ የሰውም እጅ አምሳያ ከክንፎቻቸው በታች ነበረ። 22ፊቶቻቸውም በኮበር ወንዝ ያየኋቸውን ፊቶች ይመስሉ ነበር፥ እነርሱና መልካቸውም እንዲሁ ነበረ፥ እያንዳንዱም አቅንቶ ወደ ፊት ይሄድ ነበር።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 10: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ