ኦሪት ዘፍጥረት 20
20
1አብርሃምም ከዚያ ተነሥቶ ወደ አዜብ ምድር ሄደ በቃዴስና በሱር መካከልም ተቀመጠ በጌራራም በእንግድነት ተቀመጠ። 2አብርሃምም ሚስቱን ሣራም፤ እኅቴ ናት አለ የጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክም ላከና ሣራን ወሰዳት። 3እግዚአብሔርም ሌሊት በሕልም ወደ አቢሜሌክ መጣ፥ እንዲህም አለው፤ እነሆ አንተ ስለ ወሰድሃት ሴት ምውት ነህ እርስዋ ባለ ባል ናትና። 4አቢሜሌክ ግን አልቀረባትም ነበር እንዲህም አለ፤ አቤቱ ጻድቁን ሕዝብ ደግሞ ታጠፋለህን? 5እኅቴ ናት ያለኝ እርሱ አይደለምን? እርስዋም ደግሞ ራስዋ ወንድሜ ነው አለች፤ በልቤ ቅንነትና በእጄ ንጽሕነት ይህንን አደረግሁ። 6እግዚአብሔርም በሕልም አለው፤ ይህን በልብህ ቅንነት እንዳደረግህ እኔ አወቅሁ፥ እኔም ደግሞ በፊቴ ኃጢአትን እንዳትሠራ ከለከልሁህ፤ ስለዚህም ትነካት ዘንድ አልተውሁም። 7አሁንም የሰውዩውን ሚስት መልስ ነቢይ ነውና፥ ስለ አንተም ይጸልያል፤ ትድናለህም። ባትመልሳት ግን አንተ እንድትሞት ለአንተ የሆነውም ሁሉ እንዲሞት በእርግጥ እወቅ።
8አቢሜሌክም በነገታው ማለደ፥ ባሪያዎቹንም ሁሉ ጠራ ይህንንም ነገር ሁሉ በጆሮአቸው ተናገረ ስዎቹም እጅግ ፈሩ። 9አቢሜሌክም አብርሃምን ጠርቶ አለው፤ ይህ ያደረግህብን ምንድር ነው? ምንስ ክፉ ሠራሁብህ? በእኔና በመንግሥቴ ላይ ትልቅ ኃጢአት አውርደሃልና የማይገባ ሥራ በእኔ ሠራህብኝ። 10አቢሜሌክም አብርሃምን አለው፤ ይህን ማድረግህ ምን አይተህ ነው? 11አብርሃምም አለ፤ በዚህ ስፍራ እግዚአብሔርን መፍራት በእውነት እንድሌለ ለሚስቴም ሲሉ እንደሚገድሉኝ ስላሰብሁ ነው። 12እርስዋም ደግሞ በእውነት እኅቴ ናት የእናቴ ልጅ አይደለችም እንጂ የአባቴ ልጅ ናት ለእኔም ሚስት ሆነች። 13እግዚአብሔርም ከአባቴ ቤት ባወጣኝ ጊዜ አልኍት በገባንበት አገር ሁሉ ለእኔ የምታደርጊው ወሮታ ይህ ነው፤ ወንድሜ ነው ብለሽ ስለእኔ ተናገሪ። 14አቢሜሌክም በጎችንና ላሞችን ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችን አመጣ፤ ለአብርሃምም ስጠው ሚስቱን ሣራንም መለሰለት። 15አቢሜሌክም፤ እነሆ ምድሬ በፊትህ ናት፤ በወደድኸው ተቀመጥ አለ። 16ሣራንም አላት እነሆ ለወንድምሽ ሺህ ሚዛን ብር ሰጠሁት ያም እነሆ ከአንቺ ጋር ባሉት ሁሉ ፊት የዓይኖች መሸፈኛ ይሁንሽ ጽድቅሽ ለሰዎች ሁሉ ተገልጦአልና። 17አብርሃምም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እግዚአብሔርም አቢሜሌክን ሚስቱንም ባሪያዎቹንምም ፈውሳቸው 18እነርሱም ወለዱ እግዚአብሔር በአብርሃም ሚስት በሣራ ምክንያት በአቢሜሌክ ቤት ማኅፀኖችን ሁሉ በፍጽም ዘግቶ ነበርና።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 20: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ