የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 27

27
1ይስሐቅ ሸምግሎ ዓይኖቹ ከማየት በፈዘዙ ጊዜ ታላቁን ልጁን ዔሳውን ጠርቶ፦ ልጄ ሆይ አለው እርሱም፦ እነሆ አለሁ አለው። 2እርሱም አለው፦ እነሆ እኔ አረጀሁ የምሞትበትን ቀን አላውቅም። 3አሁንም ማደኛህን የፍላጻህን አፎትና ቀስትህን ውሰድ ወደ ምድረ በዳም ውጣ አደንም አድንልኝ፤ 4ሳልሞትም ነፍሴ እንድትባርክህ የጣፈጠ መብል እኔ እንደምወደው አዘጋጅትህ እበላ ዘንድ አምጣልኝ።
5ርብቃም ይስሐቅ ለልጁ ለዔሳው ሲነግር ትሰማ ነበር። ዔሳውም አደን አድኖ ሊያመጣ ወደ ምድረ በዳ ሄደ። 6ርብቃም ልጅዋን ያዕቆብን እንዲይ አለችው፦ እነሆ አባትህ 7ለወንድምህ ለዔሳው፦ አደን አድነህ አምጣልኝ ሳልሞትም በልቼ በእግዚአብሔር ፊት እንድባርክህ የጣፈጠ መብል አድርግልኝ ብሎ ሲነግረው ሰማሁ። 8አሁንም ልጄ ሆይ እኔ በማዝዝህ ነገር ስማኝ ወደ መንጋ ሄደህ ሁለት መልካካም ጠቦቶች አምጣልኝ 9እነርሱን፥ ጣፋጭ መብል ለአባትህ እንደሚወደው አደርጋለሁ፤ 10ለአባትህም ሳይሞት እንዲባርክህ ይበላ ዘንድ ታገባለታለህ። 11ያዕቆብም ርብቃን እናቱን አላት፦ እነሆ ዔሳው ወንድሜ ጠጕራ፥ ሰው ነው እኔ ግን ለስላሳ ነኝ አባቴ ቢዳስሰኝ 12በፊቱ እንደሚዘብት እሆናለሁ መርገምንም በላዬ አመጣለሂ በረከትን አይደለም። 13እናቱም አለችው፦ ልጄ ሆይ፥ መርገምህ በእኔ ላይ ይሁን ቃሌን ብቻ ስማኝ ሂድና አምጣልኝ። 14ሄዶም አመጣ ለእናቱም ሰጣት እናቱም የጣፈጠውን መብል አባቱ እንደሚወደው አደረገች። 15ርብቃም ከእርስዋ ዘንድ በቤት የነበረውን የታላቁን ልጅውን የዔሳውን መልካሙን ልብስ አመጣች ታናሹን ልጅዋን ያዕቆብንም አለበሰችው፤ 16የጠቦቶችንም ለምድ በእጆቹን በለስላሳው አንገቱ ላይ አደረገች 17የሠራችውን ጣፋጭ መብልና እንጀራውን ለልጅዋ ለያዕቆብ በእጁ ሰጠችው።
18ወደ አባቱም ገብቶ፦ አባቴ ሆይ አለው እርሱም፦ እነሆኝ፤ ልጄ ሆይ አንተ ማን ነህ? አለ። 19ያዕቆብም አባቱን አለው፦ የበኵር ልጅህ እኔ ዔሳው ነኝ እንዳዘዝኽኝ አደረግሁ፤ ነፍስህ ትባርከኝ ዘንድ ቀና በልና ተቀመጥ ካደንሁትም ብላ። 20ይስሐቅም ልጁን፦ ልጄ ሆይ እንዴት ፈጥነህ አገኘኸው? አለው እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላክህ ወደ እኔ ስለ አቀረበው ነው አለ። 21ይስሐቅም ያዕቆብን፦ ልጄ ሆይ አንተ ልጄ ዔሳ እንደ ሆንህ ወይም እንዳልሆንህ እዳስስህ ዘንድ ቅረበኝ አለው። 22ያዕቆብም ወደ አባቱ ወደ ይስሕቅ ቀረበ፤ ዳሰሰውም እንዲህም ይህ ድምፅ የያዕቆብም ድምፅ ነው እጆች ግን የዔሳው እጆች ናቸው አለው። 23እርሱም አላወቀውም ነበር እጆች ጠጕራ፥ ነበሩን፤ ስለዚህም ባረከው። 24አለውም፦ አንተ ልጄ ዔሳው ነህን? እርሱም፦ እኔ ነኝ አለ። 25እርሱም፦ ከልጄ አደን እንድበላና ነፍሴ እንድትባርክህ አቅርብልኝ አለ። አቀረበለትም፥ በላም የወይን ጠጅ አመጣለት እርሱም ጠጣ። 26አባቱ ይስሐቅም ልጄ ሆይ ወደ እኔ ቅረብ ሳመኝም አለው። 27ወደ እርሱም ቀረበ ሳመውም የልብሱንም ሽታ አሸተት ባረከውም እንዲህም አለ፦ የልጄ ሽታ እግዚአብሔር እንደ ባረከው እርሻ ሽታ ነው፤ 28እግዚአብሔርም ከሰማይ ጠል ከምድርም የእህልንም የወይንንም ብዛት ይስጥህ አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም ይስገዱልህ 29ለወንድሞችህ ጌት ሁን የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን የሚባርክህም ቡሩም ይሁን።
30ይስሐቅም ያዕቆብን ባርኮ ከፈጸመ በኍላ ያዕቆብም ከአባቱ ለይስሕቅ ፊት ከወጣ በኍላ ወዲያው በዚያው ጊዜ ዔሳው ከአደኑ መጥቶ ገባ። 31እርሱም ደግሞ ጣፋጭ መብል አዘጋጀ ለአባቱም አገባ አባቱንም፦ አባቴ ይነሣ ነፍስህም ትባርከኝ ዘንድ ከልጁ አደን ይብላ አለው። 32አባቱ ይስሐቅም፦ አንተ ማን ነህ? አለው፤ እርሱም፦ እኔ የበኵር ልጅህ ዔሳው ነኝ አለው። 33ይስሐቅም እጅግ ደነገጠ እንዲህም አለ፦ ያደነውን አደን ወደ እኔ ያመጣ ማን ነው? አንተ ሳትመጣም ከሁሉ በላሁ ባረክሁትም እርሱም የተባረከ ሆኖ ይኖራል። 34ዔሳውም የአባቱን ቃል በሰማ ጊዜ ታላቅ እጅግም መራራ ጩኸት ጮኸ አባቱንም፦ አባቴ ሆይ እኔንም ደግሚ ባርከኝ አለው። 35እርሱም፦ ወንድምህ በተንኮል ገብቶ በረከትህን ወሰደብህ አለ። 36እርሱም አለ፦ በእውነት ስሙ ያዕቆብ ተባለ ሁለት ጊዜ አሰናክሎኛልና፤ ብኵርናዬን ወሰደ አሁንም እነሆ በረከቴን ወሰደ። ደግሞም፦ ለእኔ በረከትን አላስቀረህልኝምን? አለ። 37ይስሐቅም መለሰ ዔሳውንም አለው፦ እነሆ ጌታህ አደረግሁት ወንድሞቹንም ሁሉ ለእርሱ ተገዦች ይሆኑ ዘንድ ሰጠሁት በእህልም በወይንም አበረታሁት ለአንተ ግን ልጄ ሆይ ምን ላድርግ? 38ዔሳውም አባቱን አለው፦ አባቴ ሆይ እኔንም ደግሞ ባርከኝ። ዔሳውም ቃሉን አንሥቶ አለቀሰ። 39አባቱ ይስሐቅም መለሰ አለውም፦ እነሆ መኖሪያህ ከምድር ስብ ከላይ ከሚገኝ ከሰማይም ጠል ይሆናል፤ 40በሰይፍህም ትኖራለህ፥ ለወንድምህም ትገዛለህ ነገር ግን በተቃወምኸው ጊዜ ቀንበሩን ከአንገትህ ትጥላለይ።
41ዔሳው፥ አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት ዔሳውም በልቡ አለ፦ ለአባቴ የልቅሶ ቀን ቀርቦአል ከዚያም በኍላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ። 42ለርብቃም ይህ የታላቁ ልጅዋ የዔሳው ቃል ደረሰላት፤ ታናሹን ልጅዋን ያዕቆብንም አስጠርታ አስመጣችው አለችውም፦ እነሆ ወንድምህ ዔሳ ሊገድልህ ይፈቅዳል። 43አሁንም ልጄ ሆይ ቃሌን ስማ ተነሣና ወደ ካራን ምድር ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሂድ፤ 44በእርሱም ዘንድ ጥቂት ቀን ተቀመጥ የወንድምህ ቍጣ እስኪበርድ 45የወንድምህ ቍጣ ከአንተ እስኪመለስ ድረስ፥ ያደረግህባትንም እስኪረሳው ድረስ ከዚይም ልኬ አስመጣሃለሁ በአንድ ቀን ሁለታችሁን ለምን አጣለሁ?
46ርብቃም ይስሐቅን አለችው፦ ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተነሣ ሕይወቴን ጠላሁት ያዕቆብ ከዚህ አገር ሴቶች ልጆች ሚስትን የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለምኔ ነው?

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ