ኦሪት ዘፍጥረት 33
33
1ያዕቆብም ዓይኑን አነሣ እነሆም ዔሳውን ሲመጣ አየው ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች ነበሩ፤ ልጆቹንም ከፍሎ ወደ ልያና ወደ ራሔል ወደ ሁለቱም ባሪያዎች አደረጋቸው፤ 2ባሪያዎችንና ልጆቻቸውንም በፊት አደረገ ልያንና ልጆችዋንም በኋለኛው ስፍራ ራሔልንና ዮሴፍንም ከሁሉ በኍላ አደረገ። 3እርሱም በፊታቸው አለፈ ወደ ወንድሙም እስኪደርስ ድረስ ወደ ምድር ሰባት ጊዜ ሰገደ። 4ዔሳውም ሊገናኘው ሮጠ አንገቱንም አቅፎ ሳመው ተላቀሱም። 5ዓይኑንም አነሣና ሴቶችንና ልጆችን አየ እንዲህም አለ፦ እነዚህ ምኖችህ ናቸው? እርሱም፦ እግዚአብሔር ለእኔ ለባሪያህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው አለ። 6ሴቶች ባሪያዎችም ከልጆቻቸው ጋር ቀርበው ሰገዱ 7ደግሞም ልያና ልጆችዋ ቀረበው ሰገዱ ከዚይም በኍላ ዮሴፍና ራሔል ቀርበው ሰገዱ። 8እርሱም፦ ያገኘሁት ይህ ሠራዊት ሁሉ ምንህ ነው? አለ። እርሱም፦ በጌታዬ ፊት ሞገስን አገኝ ዘንድ ነው አለ። 9ዔሳውም፦ ለእኔ ብዙ አለኝ ወንድሜ ሆይ የአንተ ለአንተ ይሁን አለ። 10ያዕቆብም አለ፦ እንደዚህ አይደለም ነገር ግን በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆንሁ እጅ መንሻዬን ተቀበለኝ የእግዚአብሔርን ፊት እንደሚያይ ፊትህን አይቼአለሁና በቸርነትም ተቀብለኸኛልና። 11ይህችንም ያመጣሁልህን በረከቴን ተቀበል እግዚአብሔር በቸርነት ስጥቶኛልና ለእኔም ብዙ አለኝና። እስኪቀበለውም ድረስ ዘበዘበው። 12እርሱም፦ ተነሣና እንሂድ እኔም በፊትህ እሄዳለሁ አለ። 13እርሱም አለው፦ ጌታዬ ሆይ ልጆቹ ደካሞች እንደ ሆኑ ታውቃለህ በጎችና ላሞችም ግልገሎቻቸውን ያጠባሉ ሰዎችም አንድ ቀን በችኮላ የነዱአቸው እንደ ሆን ከብቶቹ ሁሉ ይሞታሉ። 14ጌታዬ ከባሪያው ፊት ቀድሞ ይለፍ እኔም ወደ ሴይር ከጌታዬ ዘንድ እስክደርስ ድረስ ከፊቴ ባሉት በእንስሳቱ እርምጃና በሕፃናቱ እርምጃ መጠን በዝግታ እከተላለሁ። 15ዔሳውም፦ ከእኔ ጋር ካሉት ሰዎች ከፍዬ ልተውልህን? አለ። እርሱም፦ ይህ ለምንድር ነው? በጌታዬ ዘንድ ሞገስን ማግኘት ይበቃኛል አለ። 16ዔሳውም በዚያን ቀን ወደ ሴይር መንገዱን ተመለሰ። 17ያዕቆብ ግን ወደ ሱኮት ሄደ በዚያም ለእርሱ ቤትን ሠራ ለከብቶች ዳሶችን አደረገ፤ ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም ሱኮት ብሎ ጠራው።
18ያዕቆብም ከሁለት ወንዞች መካከል በተመለሰ ጊዜ በከንዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሴኬም ከተማ በደኅንነት መጣ በከተማይቱም ፊት ሰፈረ። 19ድንኳኑን ተክሎበት የነበረውንም የእርሻውን ክፍል ከሴኬም አባት ከኤሞር ልጆች በመቶ በጎች ገዛው። 20በዚያም መሠውያውን አቆመ ያንም፥ ኤል ኤሎሄ እስራኤል ብሎ ጠራው።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 33: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ