ኦሪት ዘፍጥረት 41
41
1ከሁለት ዓመት በኍላም ፈርዖን ሕልምን አየ፥ እነሆም በወንዙ ዳር ቆሞ ነበረ። 2እነሆም መልካቸው ያማረ ሥጋቸውም የወፈረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጡ በውኃውም ዳር በመስኩ ይስማሩ ነበር። 3ከእነርሱም በኍላ እነሆ መልካቸው የከፋ ሥጋቸውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዝ ወጡ በእነዚያም ላሞች አጠገብ በወንዙ ዳር ይቆሙ ነበር። 4መልካቸው የከፋ ሥጋቸውም የከሳ እነዚያም ላሞች መልካቸው ያማረውን ሥጋቸው የወፈረውን ሰባቱን ላሞች ዋጡአቸው። ፈርዖንም ነቃ። 5ደግሞም ተኛ ሁለተኛም ሕልምን አየ እነሆም በአንድ አገዳ ላይ የነበሩ ያማሩና መልካም የሆኑ ሰባት እሸቶች ወጡ። 6እነሆም ከእነርሱ በኍላ የሰለቱና በምሥራቅ ነፋስ የተመቱ ሰባት እሸቶች ወጡ፤ 7የሰለቱትም እሽቶች ስባቱን ያማሩና የዳበሩ እሸቶች ዋጡአቸው። 8ፈርዖንም ነቃ እነሆም ሕልም ነበረ። በነጋም ጊዜ ነፍሱ ታወከችበት ወደ ሕልም ተርጕሚዎች ሁሉ ወድ ግብፅ ጠቢባንም ሁሉ ልኮ ወደ እርሱ ጠራቸው ፈርዖንም ሕልሙን ነገራቸው ነገር ግን ከእነርሱ ለፈርዖን የሚተረጕም አልተገኘም።
9የዚያን ጊዜ የጠጅ አሳላፈዎቹ አለቃ እንዲህ ብሎ ለፈርዖን ተናገረ፦ እኔ ኃጢአቴን ዛሬ አስባለሁ፤ 10ፈርዖን በባሪይዎቹ ላይ ተቆጣ እኔንም የእንጀራ አበዛዎቹንም አለቃ በግዞት ስፍራ በዘበኞች አለቃ ቤት አኖረን 11እኛም በአንዲት ሌሊት ሕልምን አለምን እኔና እርሱ እያንዳንዳችን እንደ ሕልማችን ትርጓሜ አለምን። 12በዚይም የዘበኞቹ አለቃ ባሪያ የሆነ አንድ ዕብራዊ ጕልማሳ ከእኛ ጋር ነበረ ለእርሱም ነገር ነው ሕልማችንንም፥ ተረጎመልን። 13እንዲህም ሆነ እንደ ተረጎመልን እንደዚያው ሆነ እኔ ወደ ሹመቴ ተመለስሁ እርሱም ተሰቀለ።
14ፈርዖንም ልኮ ዮሴፍን አስጠራ ከግዞት ቤትም አስቸኮሉት፤ እርሱም ተላጨ ልብሱንም ለወጠ፥ ወደ ፈርዖን ገባ። 15ፈርዖንም ዮሴፍን አለው፦ ሕልምን አየሁ የሚተረጕመውም አልተገኘም ሕልምን እንደ ሰማህ እንደ ተረጎምህም ስለ አንተ ሰማሁ። 16ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ ብሎ መለሰ፦ ይህ በእኔ አይደለም እግዚአብሔር ግን ለፈርዖን በደኅንነት ይመልስለታል። 17ፈርዖንም ለዮሴፍ እንዲህ አለው፦ እነሆ በሕልሜ በወንዝ ዳር ቆሜ ነበር፤ 18እነሆም ሥጋቸውም የወፈረ መልካቸውም ያማረ ሰባት ላሞች ወጡ በመስኩም ይስማሩ ነበር። 19ከእነርሱን በኍላ እነሆ የደከሙ መልካቸውም እጅግ የከፋ ሥጋቸውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ወጡ በግብፅም ምድር ሁሉ እንደ እነርሱ መልክ ከፍ ከቶ አላየሁም፤ 20የከሱትና መልከ ክፋዎቹ ላሞች የመጀመሪያዎቹን ወፍራሞቹን ስባት ላሞች ዋጡአቸው፥ 21በሆዳቸውም ተዋጡ አልታወቀም መልካቸውም በመጀመሪያ እንደ ነበረውም የከፋ ነበረ። 22በሕልሜም እነሆ የዳበሩና መልካም የሆኑ ሰባት እሸቶች በአንድ አገዳ ሲወጡ አየሁ 23ከእነርሱም በኍላ እነሆ የደረቁና የሰለቱ በምሥራቅ ነፋስ የተመቱ ስባት እሸቶች ወጡ 24የሰለቱት እሸቶች ያማሩትን ሰባቱን እሸቶች ዋጡአቸው። ለሕልም ተርጓሚዎችም ሕልሜን ነገርሁ የሚተረጕምልኝም አጣሁ።
25ዮሴፍም ፈርዖንን አለው፦ የፈርዖን ሕልሙ አንድ ነው እግዚአብሔር ሊያደርገው ያለውን ለፈርዖን ነግሮታል። 26ሰባቱ መልካካሞች ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፥ ሰባቱም መልካካሞች እሸቶች ሰባት ዓመታት ናቸው ሕልሙ አንድ ነው። 27ከእነርሱም በኍላ የወጡት የከሱትና መልከ ክፋዎቹ ሰባት ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፥ የሰለቱትና የምሥራቅ ነፋስ የመታቸው ሰባቱም እሽቶች እነርሱ ራብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ናቸው። 28ለፈርዖን የነገርሁት ነገር ይህ ነው እግዚአብሔር ሊያደርገው ያለውን ለፈርዖን አሳየው። 29እነሆ በግብፅ ምድር ሁሉ እጅግ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ 30ደግሞ ከዚህ በኍላ የሰባት ዓመት ራብ ይመጣል በግብፅ አገር የነበረውም ጥጋብ ሁሉ ይረሳል ራብም ምድርን በጣም ያጠፋል 31በኍላ ከሚሆነው ከዚያ ራብ የተነሣም በምድር የሆነው ጥጋብ አያታወቅም እጅግ ጽኑ ይሆናልና። 32ሕልሙም ለፈርዖን ደጋግሞ መታየቱ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቀረጠ ስለ ሆነ ነው እግዚአብሔር ፈጥኖ ያደርገዋል። 33አሁንም ፈርዖም ብልህና አዋቂ ሰውን ይፈልግ በግብፅ ምድር ላይም ይሹመው። 34ፈርዖን በምድር ላይ ሹማምትን ይሹም በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ፍሬ በግብፅ ምድር ሁሉ ከአምስት እጅ አንደኛውን ይውሰድ። 35የሚመጡትን የመልካሞቹን ዓመታት እህላቸውም ያከማቹ ስንዴውንም ከፈርዖን እጅ በታች ያኑሩ፥ እህሎችም በከተሞች ይጠበቁ 36በግብፅ ምድር ስለሚሆነው ስለ ስባቱ ዓመታት ራብ እህሉ ተጠብቆ ይኑር ምድሪቱም በራብ አትጠፋም።
37ነገሩም በፈርዖንና በሎሌዎቹ ፊት መልካም ሆነ፤ 38ፈርዖንም ሎሌዎቹን እንዲህ አላቸው፦ በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበትን እንደዚህ ያለ ሰው እናገኛለንን? 39ፈርዖንም ዮሴፍን አለው፦ እንደ አንተ ያለ ብልህ አዋቂም ሰው የለም እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ገልጦልሃልና። 40አንተ በቤቴ ላይ ተሾምክ ሕዝቤም ሁሉ ለቃልህ ይታዘዝ እኔ በዙፋኔ ብቻ ከአንተ እበልጣለሁ። 41ፈርዖንም ዮሴፍን፦ በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾምሁህ አለው። 42ፈርዖን ቀለበቱን ከእጁ አወለቀ በዮሴፍ እጅም አደረገው ነጭ የተልባ እግር ልብስንም አለበሰው በአንገቱም የወርቅ ዝርግፍን አደረገለት፤ 43የእርሱም በምትሆን በሁለተኛይቱ ሰረገላ አስቀመጠው አዋጅ ነጋሪም፦ ስገዱ እያለ በፊት በፊት ይጮኽ ነበር እርሱም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ተሾመ። 44ፈርዖንም ዮሴፍን አለው፦ እኔ ፈርዖን ነኝ በግብፅ አገር ሁሉ ያለ አንተ ማንም እጁንም እግሩንም አያንሣ። 45ፈርዖንም የዮሴፍን ስም ጸፍናት ፐዕናህ ብሎ ጠራው የሄልዮቱ ከተማ ካህን የዾጥፌራ ልጅ የምትሆን አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በግብፅ ምድር ሁሉ ወጣ።
46ዮሴፍም በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። 47ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጣ የግብፅ ምድርንም ሁሉ ዞረ። በሰባቱም በጥጋብ ዓመታት የምድሪቱ ፍሬ ክምር ሆነ። 48በግብፅ ምድር ሁሉ ያለውን የሰባቱን ዓመታ እህል ሁሉ ሰበሰበ እህልንም በከተማቹ አደለበ፤ በየከተማይቱ ዙሪያ ያለውን የእርሻውን እህል ሁሉ በዚያው ከተተ። 49ዮሴፍም እንደ ባሕር አሸዋ እጅግ ብዙ የሆነ ስንዴን አከማቸ መሰፈርን እስኪተው ድረስ ሊሰፈር አልተቻለምና።
50ለዮሴፍም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የዾጥፌራ ልጅ አስናት የወለደችለት ሁለት ልጆች የራብ ዘመን ገና ሳይመጣ ተወለዱለት። 51ዮሴፍም የበኵር ልጅን ስም ምናሴ ብሎ ጠራው እንዲህ ሲል እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ የአባቴንም ቤት አስረስኝ 52የሁለተኛውንም ስም ኤፍሬም ብሎ ጠራው እንዲህ ሲል፦ እግዚአብሔር በመከራዬ አገር አፈራኝ።
53በግብፅ ምድር የነበረውም የሰባቱ ዓመት ጥጋብ አለፈ፥ 54ዮሴፍም እንደ ተናገረ የሰባቱ ዓመት ራብ ጀመረ። በየአገሩም ሁሉ ራብ ሆነ በግብፅ ምድር ሁሉ ግን እህል ነበረ። 55የግብፅ ምድርም ሁሉ ተራበ ሕዝቡም ስለ እህል ወደ ፈርዖን ጮኽ ፈርዖንም የግብፅ ሰዎችን ሁሉ፦ ወደ ዮሴፍ ሂዱ፥ እርሱ ያላችሁንም ሁሉ አድርጉ አላቸው። 56በምድርም ሁሉ ላይ ራብ ሆነ ዮሴፍም እህል ያለበትን ጎተራ ሁሉ ከፍቶ ለግብፅ ሰዎች ሁሉ ይሸጥ ነበር፤ ራብም በግብፅ ምድር ጸንቶ ነበር። 57አገሮችም ሁሉ እህል ይገዙ ዘንድ ወደ ግብፅ ወደ ዮሴፍ መጡ በምድር ሁሉ ራብ እጅግ ጸንቶ ነበርና።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 41: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ