ኦሪት ዘፍጥረት 48
48
1ከዚህም ነገር በኍላ እንዲህ ሆነ እነሆ አባትህ ታምሞአል ብለው ለዮሴፍ ነገሩት እርሱም ሁለትን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ሄደ። 2ለያዕቆብም፦ እነሆ ልጅህ ዮሴፍ መጥቶልሃል ብለው ነገሩች እስራኤልም ተጠነካከረ በአልጋውም ላይ ተቀመጠ። 3ያዕቆብ ዮሴፍን አለው፤ ሁሉን የሚችል አምላክ በከነዓን ምድር በሎዛ ተገለጠልኝ ባረከኝም እንዲህም አለኝ፦ 4እነሆ ፍሬያማ አደርግሃለሁ አበዛሃልሁም ለብዙም ሕዝብ ጉባኤ አደርግሃለው ይህችንም ምድር ከአንተ በኍላ ለዘላለም ርስት ለዘርህ እሰጣታለሁ። 5አሁንም እኔ ወደ አንተ ከመምጣቴ በፊት በግብፅ ምድር የተወለዱልህ ሁለቱ ልጆችን ለእኔ ይሁኑ ኤፍሬምን ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤል እንደ ስምዖን ናቸው። 6ከእነርሱም በኍላ የምትወልዳቸው ልጆች ለአንተ ይሁኑ በርስታቸው በወንድሞቻቸው ስም ይጠሩ። 7እኔም ከመስዼጦምያ በመጣሁ ጊዜ ወደ ኤፍራታ ለመግባት ጥቂት ቀርቶኝ በመንገድ ሳለሁ ራሔል በከነዓን ምድር ሞተችብኝ በዚያም በኤፍራታ መንገድ ላይ እርስዋም ቤተ ልሔም ናት ቀበርኍት።
8እስራኤልም የዮሴፍን ልጆችን አይቶ፦ እነዚህ እነማን ናችው? አለው። 9ዮሴፍም ለአባቱ፦ እግዚአብሔር በዚህ የሰጠኝ ልጆቼ ናቸው አለ። እርሱም፦ እባርካቸው ዘንድ ወደዚህ አቅርብልኝ አለ። 10የእስራኤልም ዓይኖች ከሸምግልና የተነሣ ከብደው ነበር። ማየትም አይችልም ነበር ወደ እርሱም አቀረባቸው ሳማቸውም አቀፋቸውም። 11እስራኤልም ዮሴፍን፦ ፊትህን አያለሁ ብዬ አላሰብሁም ነበር እነሆም እግዚአብሔር ዘርህን ደግሞ አሳየኝ አለው። 12ዮሴፍም ከጕልበቱ ፈቀቅ አደረጋቸው ወደ ምድርም በግምባሩ ሰገደ። 13ዮሴፍም ሁለቱን ልጆቹን ወሰደ ኤፍሬምንም በቀኙ በእስራኤል ቀኝ አደረገው ወደ እርሱም አቀረባቸው። 14እስራኤልም ቀኝ እጁን ዘርግቶ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረው እርሱም ታናሽ ነበረ ግራውንም በምናሴ ራስ ላይ አኖረ እጆቹንም አስተላለፈ፥ ምናሴ ራስ ላይ አኖረ፤ እጆቹንም አስተላለፈ ምናሴ በኵር ነበርና 15ያዕቆብም ዮሴፍን ባረከው እንዲህም አለ፦ አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ የሄዱለት እርሱ ዛሬ ድርስ እኔን የመገባኝ እግዚአብሔር ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር ከክፋ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እርሱ 16እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምን የይስሐቅም ስም በእነርሱ ይጠራ በምድርም መካከል ይብዙ። 17ዮሴፍም አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ጭኖ ባየ ጊዜ አሳዘነው የአባቱንም እጅ በምናሴ ራስ ላይ ይጭነው ዘንድ ከኤፍሬም ራስ ላይ አነሣው። 18ዮሴፍም አባቱን፦ አባቴ ሆይ እንዲህ አይደለም፥ በኵሩ ይህ ነውና ቀኝህን በራሱ ላይ አድርግ አለው። 19አባቱም እንቢ አለ እንዲህ ሲል፦ አወቅሁ ልጄ ሆይ አወቅሁ ይህም ደግሞ ሕዝብ ይሆናል ታላቅም ይሆናል ነገር ግን ታናሽ ወንድሙ ከእርሱ ይበልጣል ዘሩም የአሕዛብ ሙላት ይሆናል። 20በዚያም ቀን እንዲህ ብሎ ባረካቸው፦ በእናንተ እስራኤል እንዲህ ብሎ ይባርካል፦ እግዚአብሔር እንደ ኤፍሬምና እንደ ምናሴ ያድርግህ። ኤፍሬምንም ከምናሴ ፊት አደረገው። 21እስራኤልም ዮሴፍን፦ እነሆ እኔ እሞታለሁ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ይሆናል፥ ወደ አባቶቻችሁም ምድር ይመልሳችኍል፤ 22እኔም ከአሞራውያን በሰይፌና በቀስቴ የውስድሁትን ለአንተ ከወንድሞችህ አንድ እጅ አብልጬ ሰጠሁህ አለው።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 48: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ