ትንቢተ ኢሳይያስ 38
38
1በዚያም ወራት ሕዝቅያስ ለሞት እስኪደርስ ታመመ። ነቢዩም የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ እርሱ መጥቶ፦ እግዚአብሔር እንዲሁ ይላል፦ ትሞታለህ እንጂ በሕይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል አለው። 2ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳው መልሶ እንዲህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፦ 3አቤቱ፥ በፊትህ በእውነትና በፍጹም ልብ እንደ ሄድሁ ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግሁ ታስብ ዘንድ እለምንሃለሁ። ሕዝቅያስም እጅግ አድርጎ አለቀሰ። 4የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኢሳይያስ እንዲህ ሲል መጣ፦ 5ሂድ፥ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፦ የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ እንባህንም አይቻለሁ፥ እነሆ፥ በዕድሜህ ላይ አሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ። 6አንተንና ይህችንም ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፥ ይህችንም ከተማ እጋርዳታለሁ። 7እግዚአብሔርም የተናገረውን ነገር እንዲፈጽመው ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክቱ ይህ ይሆንልሃል። 8እነሆ፥ በአካዝ የጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ ከፀሐይ ጋር የወረደውን በደረጃዎች ያለውን ጥላ አሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደርጋለሁ። ፀሐይም በጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ የወረደበት አሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመለሰ። 9የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ታምሞ ከደዌው በተፈወሰ ጊዜ የጻፈው ጽሕፈት ይህ ነው፦ 10እኔ፦ በሕይወት ዘመኔ መካከል ወደ ሲኦል በሮች እገባለሁ፥ የቀረው ዘመኔ ጐደለብኝ አልሁ። 11ደግሞም፦ በሕያዋን ምድር እግዚአብሔርን አላይም፥ በዓለምም ከሚኖሩ ጋር ሰውን እንግዲህ አልመለከትም አልሁ። 12ማደሪያዬ ተነቀለች፥ እንደ እረኛ ድንኳንም ከእኔ ዘንድ ተወገደች፥ ሕይወቴንም እንደ ሸማኔ ጠቀለልሁ፥ እርሱም ከመጠቅለያው ይቈርጠኛል፥ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ታጠፋኛለህ። 13እስኪነጋ ድረስ ቈይቼ ነበር፥ እርሱ እንደ አንበሳ አጥንቴን ሁሉ ሰበረ፥ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ታጠፋኛለህ። 14እንደ ጨረባና እንደ ሽመላ ተንጫጫሁ፥ እንደ ርግብም አጕረመረምሁ፥ ዓይኖቼ ወደ ላይ ከማየት ደከሙ። ጌታ ሆይ፥ ተጨንቄአለሁና መከታ ሁነኝ። 15ምን እላለሁ? እርሱ ተናግሮኛል፥ እርሱ ራሱም ይህን አድርጎአል፥ በዘመኔ ሁሉ ስለ ነፍሴ ምሬት ቀስ ብዬ እሄዳለሁ። 16ጌታ ሆይ፥ በዚህ ነገር ሰዎች በሕይወት ይኖራሉ፥ በዚህም ሁሉ የመንፈሴ ሕይወት ነው፥ አንተም ፈወስኸኝ ወደ ሕይወትም መለስኸኝ። 17እነሆ፥ ታላቅ ምሬት ለደኅንነቴ ሆነ፥ አንተም ነፍሴን ከጥፋት ጕድጓድ አዳንሃት፥ ኃጢአቴንም ሁሉ ወደ ኋላህ ጣልህ። 18ሲኦል አያመሰግንህምና፥ ሞትም አያከብርህምና፥ ወደ ጕድጓዱ የሚወርዱ እውነትህን ተስፋ አያደርጉም። 19እኔ ዛሬ እንደማደርግ ሕያዋን እነርሱ ያመሰግኑሃል፥ አባት ለልጆች እውነትህን ያስታውቃል። 20እግዚአብሔር ያድነኛል፥ ስለዚህ በዕድሜያችን ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ቅኔዎችን አውታር ባለው ዕቃ እንዘምራለን። 21ኢሳይያስም፦ የበለስ ጥፍጥፍ አምጥተው በእባጩ ላይ ይለብጡት፥ እርሱም ይፈወሳል ብሎ ነበር። 22ሕዝቅያስም፦ ወደ እግዚአብሔር ቤት እወጣ ዘንድ ምልክቱ ምንድር ነው? ብሎ ነበር።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 38: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ