መጽሐፈ መሳፍንት 10
10
1ከአቤሜሌክም በኋላ ከይሳኮር ነገድ የሆነ የዱዲ ልጅ የፎሓ ልጅ ቶላ እስራኤልን ለማዳን ተነሣ፥ በተራራማውም በኤፍሬም አገር ባለችው በሳምር ተቀምጦ ነበር። 2በእስራኤልም ላይ ሀያ ሦስት ዓመት ፈረደ፥ ሞተም፥ በሳምርም ተቀበረ።
3ከእርሱም በኋላ ገለዓዳዊው ኢያዕር ተነሣ፥ በእስራኤልም ላይ ሀያ ሁለት ዓመት ፈረደ። 4በሠላሳ የአህያ ግልገሎች ይቀመጡ የነበሩ ሠላሳ ልጆችም ነበሩት፥ ለእነርሱም እስከ ዛሬ ድረስ የኢያዕር መንደሮች የተባሉ በገለዓድ ምድር ያሉ ሠላሳ ከተሞች ነበሩአቸው። 5ኢያዕርም ሞተ፥ በቃሞንም ተቀበረ።
6የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ በኣሊምንና አስታሮትን የሶርያንም አማልክት፥ የሲዶናንም አማልክት፥ የሞዓብንም አማልክት፥ የአሞንንም ልጆች አማልክት፥ የፍልስጥኤማውያንንም አማልክት አመለኩ፥ እግዚአብሔርንም ተዉ፥ አላመለኩትምም። 7የእግዚአብሔርም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ በፍልስጥኤማውያንና በአሞን ልጆች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። 8በዚያም ዓመት የእስራኤልን ልጆች ሥቃይ አበዙባቸው፥ በዮርዳኖስ ማዶ በአሞራውያን አገር በገለዓድ ውስጥ ያሉትን የእስራኤልን ልጆች ሁሉ አሥራ ስምንት ዓመት ተጋፉአቸው። 9የአሞንም ልጆች ከይሁዳ ከብንያምና ከኤፍሬም ቤት ጋር ደግሞ ሊዋጋ ዮርዳኖስን ተሻገሩ፥ እስራኤልም እጅግ ተጨነቁ።
10የእስራኤልም ልጆች፦ አምላካችንን ትተን በኣሊምን አምልከናልና አንተን በድለናል ብለው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። 11-12እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልጆች አላቸው፦ ግብፃውያን፥ አሞራውያንም፥ የአሞንም ልጆች፥ ፍልስጥኤማውያንም፥ ሲዶናውያንም፥ አማሌቃውያንም፥ ማዖናውያንም አላስጨነቋችሁምን? ወደ እኔም ጮኻችሁ፥ እኔም ከእጃቸው አዳንኋችሁ። 13እናንተ ግን ተዋችሁኝ ሌሎችንም አማልክት አመለካችሁ፥ ስለዚህም ደግሞ አላድናችሁም። 14ሄዳችሁ የመረጣችኋቸውን አማልክት ጥሩ፥ እነርሱም በመከራችሁ ጊዜ ያድኑአችሁ። 15የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔርን፦ እኛ ኃጢአትን ሠርተናል፥ አንተ ደስ የሚያሰኝህን አድርግብን፥ ዛሬ ግን፥ እባክህ፥ አድነን አሉት። 16ሌሎችንም አማልክት ከመካከላቸው አስወገዱ፥ እግዚአብሔርንም አመለኩ፥ ነፍሱም ስለ እስራኤል ጉስቁልና አዘነች።
17የአሞንም ልጆች ተሰብስበው በገለዓድ ሰፈሩ። የእስራኤልም ልጆች ተሰብስበው በምጽጳ ሰፈሩ። 18ሕዝቡም፥ የገለዓድ አለቆች፥ እርስ በእርሳቸው፦ ከአሞን ልጆች ጋር መዋጋት የሚጀምር ማን ነው? እርሱ በገለዓድ ሰዎች ሁሉ ላይ አለቃ ይሆናል አሉ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መሳፍንት 10: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ